Tender Detail

Tender Details


በአዲስ አበባ አስተዳደር የጉለሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 6 ፋይናንስ ጽ/ቤት ከዚህ በታች በሎት የተዘረዘሩትን እቃዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡

በአዲስ አበባ አስተዳደር የጉለሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 6 ፋይናንስ ጽ/ቤት


 

የጨረታ ማስታወቂያ

የግዥው መለያ ቁጥር 002/2018

 

በአዲስ አበባ አስተዳደር የጉለሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 6 ፋይናንስ ጽ/ቤት ከዚህ በታች በሎት የተዘረዘሩትን እቃዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡

ሎት -1 /አንድ/ አላቂ የጽዳት እቃዎች፤ የጨረታ ማስከበሪያ በብር መጠን 109,900 ብር (አንድ መቶ ዘጠኝ ሺህ ዘጠኝ መቶ ብር)።

ሎት-2 /ሁለት/ የጽህፈት መሳሪያ፣ አላቂ የቢሮ እቃዎች እና የተሽከርካሪ እቃዎች፤ የጨረታ ማስከበሪያ በብር መጠን 110,000.00 ብር (አንድ መቶ አስር ሺህ ብር)።

ሎት-3 /ሶስት/ የደንብ ልብስ፤ የጨረታ ማስከበሪያ በብር መጠን 80,000.00 ብር (ሰማንያ ሺህ ብር)፡፡

ሎት-4 /አራት/ የቢሮ ቋሚ እቃዎች፤ የጨረታ ማስከበሪያ በብር መጠን 20,000.00 ብር (ሃያ ሺህ ብር)።

ሎት-5 /አምስት/ የደንብ ልብስ ስፌት፤ ጨረታ ማስከበሪያ በብር መጠን 10,000.00 ብር (አስር ሺህ ብር)

ሎት-6 /ስድስት/ የኮምፒውተር ፕሪንተር እና የፎቶ ኮፒ ማሽን ጥገና፤ ጨረታ ማስከበሪያ በብር መጠን 20,000.00 (ሃያ ሺህ ብር)

በጨረታው ለመካፈል ተጫራቾች፡-

  1. ሕጋዊ የታደስ ንግድ ፈቃድ እና የንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት በስማቸው ያላቸው፣ የዘመኑን ግብር የመክፈል ግዴታቸውን የተወጡ መሆኑን የሚያረጋግጥ በግብር ግዴታቸውን በግብር አስገቢ በባለስልጣን የተሰጠ ማስረጃ የሚያቀርቡ፡፡
  2. ተጫራቾች የግብር መክፈያ መለያ ቁጥር /TIN number/ VAT ተመዝጋቢ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት የሚያቀርቡ መሆን አለባቸው፡፡ የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ወይም ቲኦቲ ተመዝጋቢ መሆናቸውን የሚያሳይማስረጃ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
  3. ተጫራቾች ለጨረታ የተዘጋጀውን ሰነድ ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ የማይመለስ በብር 200 /ሁለት መቶ ብር/ በመክፈል የፋይናንስ ጽ/ቤት 3ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 14 የጨረታ ሰነድ መግዛት ይችላሉ።
  4. ተጫራቾች የሚወዳደሩበት ዋጋ ኦርጅናል ሰነድ እና ፎቶ ኮፒ ሰነድ በተናጠል ለየብቻ በታሸገ ኢንቨሎፕ ላይ የድርጅቱ ስም፣ ማህተም፣ ስልክ ቁጥር እና ፊርማ መኖር አለበት። ተጫራቾች የሚጫረቱበትን የዕቃ አይነት በመጥቀስ ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ10 የሥራ ቀናት በስራ ሰዓት በቢሮ ቁጥር 14 ለጨረታው በተዘጋጀው ሳጥን ማስገባት ይኖርባቸዋል ፡፡
  5. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ጨረታው ባበቃ በመጨረሻ ቀን 10፡30 ይታሸግና እና በማግስቱ 3፡00 ሰዓት ይከፈታል፡፡
  6. ተጫራቾች የጨረታውን ማስከበሪያ ዋስትና በባንክ በተመሰከረለት ሲፒኦ /CPO/ ማስያዝ አለባቸው። የጨረታው አሸናፊ 10% የጨረታው ውል ማስከበሪያ ዋስትና ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
  7. አሸናፊው ተጫራች ዘወትር በሥራ ሰዓት 2፡30 እስከ 11፡30 ንብረቶችን በራሱ በመጓጓዝ ማስጫኛና ማውረጃውን ጨምሮ በጉለሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 06 አስተዳደር ጽ/ቤት ግቢ ውስጥ ማውረድ ይኖርበታል።
  8. ጽ/ቤቱ የዕቃ ብዛት 20 ፐርሰንት መቀነስና መጨመር ይቻላል፡፡
  9. መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው። ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር፡- 0111-22-67-04 እና 0118-12-24-04 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ፡፡
  10. ተጫራቾች ለሚጫረቱበትን እቃ ናሙና ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡ ማቅረብ የማይችል ከሆነ ገላጭ ስፔሲፊኬሽን ማምጣት ወይም እቃውን የሚያሳይ ጥራት ያለው ፎቶ ማምጣት ይኖርባቸዋል፡፡
  11. ማንኛምው ተጫራች የመንግስት ግዥ አቅራቢነት ዝርዝር (supplier list) የተመዘገበ ሆኖ ከጨረታ ሰነድ ጋር አያይዞ ማቅረብ የሚችል መሆን አለበት፡፡

አድራሻ፡- ሽሮሜዳ ከስላሴ ቤተክርስቲያን በታች ባለው በግራ በኩል መታጠፊያ 500 ሜትር ገባ ብሎ

 

በአዲስ አበባ አስተዳደር የጉለሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 6 ፋይናንስ ጽ/ቤት

 

Save Tender