Tender Detail

Tender Details


ቦንጋ ማረሚያ ተቋም በሕግ ጥላ ስር ለምገኙ የሕግ ታራሚዎች መኖ ዝግጅትና ለተቋም ስራ አገልግሎት የሚውል ከዚህ በታች በዝርዝር የተቀመጡትን ነገሮች ሕጋዊ ንግድ ፈቃድ ካላቸው አቅራቢ ነጋዴዎች /ጥቃቅንና አነስተኛ ሕብረት ስራ/ የተደራጁ ማህበራት በአዲስ ዘመን ጋዜጣ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡

በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልላዊ መንግሥት ማረሚያ ፖሊስ የቦንጋ ማረሚያ ተቋም


 

የጨረታ ማስታወቂያ

 

ቦንጋ ማረሚያ ተቋም በሕግ ጥላ ስር ለምገኙ የሕግ ታራሚዎች መኖ ዝግጅትና ለተቋም ስራ አገልግሎት የሚውል፡፡

1ኛ. የምግብ ማብሰያ የማገዶ እንጨት (ለኛ2 ጊዜ ጨረታ)

2ኛ. አላቂ የቢሮ ጽህፈት መሳሪያዎች

3ኛ. የቢሮ ጽዳት ዕቃዎች

4ኛ. የቢሮ ቋሚ ዕቃዎች

5ኛ. የግንባታ ቁሳቁሶች

6ኛ. የሙያ ስልጠና ቁሳቁሶች

7ኛ. የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎችና ኮምፒዩተሮች

8ኛ. ሞተር ሳይክሎች

ሕጋዊ ንግድ ፈቃድ ካላቸው አቅራቢ ነጋዴዎች /ጥቃቅንና አነስተኛ ሕብረት ስራ/ የተደራጁ ማህበራት በአዲስ ዘመን ጋዜጣ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡

ስለዚህ ተጫራቾች ማሟላት የምገባቸው ግዴታዎች ፡-

1ኛ. በዘርፉ ሕጋዊ ንግድ ፈቃድ ያላቸው ሆኖ ቫት ተመዝጋቢ የሆኑ፣ በአቅራቢነት ዝርዝር ውስጥ የተመዘገቡና የዘመኑን የመንግሥት ግብር በመክፈል ንግድ ፈቃዳቸውን ያሳደሱ ሆኖ ኦርጅናል ንግድ ፈቃድ አቅርቦ ማመሳከር የሚችል፡፡

2ኛ. የጨረታ ማስከበሪያ የሚመለስ ለማገዶ እንጨት ብር 100,000.00 /አንድ መቶ ሺህ ብር/ እና ለሌሎች የቢሮ ቁሳቁሶች ብር 50,000 /ሃምሳ ሺህ/ ብር CPO ማስያዝ የሚችል፡፡

3ኛ. ለማገዶ እንጨት የ01 ዓመት የውል ማስከበሪያ ብር 200,000.00 /ሁለት መቶ ሺህ ብር/ CPO ማስያዝ የሚችል፡፡

4ኛ. በራሱ ትራንስፖርት እስከ ማረሚያ ተቋም ቅጥር ግቢ መድረስ የሚችል፡፡

ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከታወጀበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በሥራ ሰዓት እስከ 10ኛ ቀን ድረስ የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ በማይመለስ ብር 50.00 /ሃምሳ ብር/ መግዛት ይችላሉ፡፡ ተጫራቾች በገዙት የጨረታ ሰነድ መሰረት ዋጋ ገልጸው በታሸገ ፖስታ እስከ 15ኛ የሥራ ቀናት ድረስ በተዘጋጀ የጨረታ ሳጥን ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡

ጨረታው በ16ኛው ቀን እስከ ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት በማረሚያ ግቢ ተጫራቾች) ሕጋዊ ወኪሎቻቸው/ ባሉበት ይከፈታል፡፡

ማረሚያ ተቋሙ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

የተጫራቾች ያለመገኘት የጨረታውን መከፈት አያስተጓጉልም ፡፡

 

ቦንጋ ማረሚያ ተቋም

Save Tender