በኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት በደቡብ ምዕራብ ሸዋ ዞን የቀርሳ ማሊማ ወረዳ ፍ/ቤት ለፍርድ ቤቱ የሚያስፈልገው የኤሌክትሮኒክስ፤ የጽህፈት መሳሪያዎችን፤ የህትመት መሳሪዎችን፤ የንጽህና መሳሪያዎችን፤ አላቂ የቢሮ ውስጥ እቃዎችን፤ የተለያዩ ፈርኒቸሮችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
በደቡብ ምዕራብ ሸዋ ዞን የቀርሳና ማሊማ ወረዳ ፍ/ቤት
የግዢ ጨረታ ማስታወቂያ
በኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት በደቡብ ምዕራብ ሸዋ ዞን የቀርሳ ማሊማ ወረዳ ፍ/ቤት ለፍርድ ቤቱ የሚያስፈልገው የኤሌክትሮኒክስ፤ የጽህፈት መሳሪያዎችን፤ የህትመት መሳሪዎችን፤ የንጽህና መሳሪያዎችን፤ አላቂ የቢሮ ውስጥ እቃዎችን፤ የተለያዩ ፈርኒቸሮችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል። መሟላት ያለባቸው መስፈርቶች፡-
- እቃዎችን በጥራት በማቅረብ የሚያስችል ህጋዊ በ2018 ዓ/ም የታደሰ የንግድ ፍቃድ ያላቸው፤
- በገ/ኢ/ልማት ሚኒስቴር ወይም በሌላ በሚመለከተው ፍቃድ ሰጪ አካል በአቅራቢዎች ዝርዝር ስለመመዝገባቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችል ፤
- ተወዳዳሪዎቹ መንግስት ባወጣው ህግ መሰረት የተጨማሪ እሴት ታክስ 15% (VAT) ተመዝጋቢ በመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችል ፤
- የግብር ከፋይነትና የአመቱን ግብር ስለመክፈላቸው ማስረጃ የሚያቀርብ
- የውጪ ሀገር ተወዳዳሪ ከሆነ ከተቋቋመበት ሀገር የምስክር ወረቀት ወይም የታደሰ የንግድ ፍቃድ ማቅረብ አለበት።
- ተወዳዳሪው ከሙስናና ከማጭበርበር ተግባር የጸዳ ስለመሆኑና ህገራዊና ክልላዊ ደንቦችን በማክበር ጨረታውን ካሸነፈ ውሉን ለማስፈረም የተዘጋጀ መሆን አለበት።
- ተወዳዳሪው በሚያቀርበው እቃ ዝርዝር የአምራች ሀገር፤ የእቃው ስም፤ የሞዴል ቁጥርና የተመረተበት ዘመን ተዘርዝሮ መቅረብ አለበት፡፡
- ጨረታው ከተከፈተ በኋላ ማንኛውም ተወዳዳሪ ማሻሻያ ወይም ለውጥ ማድረግ እንዲሁም ከጨረታ መውጣት አይቻልም።
- ተወዳዳሪው የእቃ ናሙና በሙሉ ወይም በከፊል ሲጠየቅ እስከ ወረዳው ፍ/ቤት ማቅረብ ይኖርበታል። ናሙና ማቅረብ የማይቻሉ እቃዎች የአምራች ሀገር፤ የእቃው ስም፤ የሞዴል ቁጥርና የተመረተበት ዘመን በመዘርዘር እንዲሁም የፎቶ ግራፋቸውን አልበም ማቅረብ አለበት። ለናሙና የቀረበው ዕቃ አስፈላጊው ግምገማ ከተከናወነ በኋላ ለባለቤቱ ይመለሳል።
- ተጫራቾች በጨረታው ማስከበሪያ ብር 2000 (ሁለት ሺህ ብር) በጥሬ ወይም በባንክ በተረጋገጠ C.P.O ከጨረታ ሰነድ ጋር ማቅረብ የሚችል።
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ጀምሮ ለ15 ተከታታይ የስራ ቀናት የማይመለስ 200 ብር (ሁለት መቶ ብር) በመክፈል በወረዳው ፍ/ቤት ቢሮ ቁጥር 8 በመቅረብ መግዛት ይችላሉ።
- የጨረታ ሰነዱን በአንድ በተዘጋጀ ኤንቨሎፕ በሰም በማሸግ በንግድ ድርጅቱ ስልጣን ባለው አካል ተፈርሞና ማህተሙ አርፎበት መቅረብ አለበት።
- ጨረታው በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰአት ተዘግተው በዚህ እለት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ከጠዋቱ 4፡30 ሰአት ላይ በወረዳው ፍ/ቤት ይከፈታል። እለቱ በዓል ወይም ዝግ ከሆነ በቀጣዩ የስራ ቀን ጨረታው ይከፈታል።
- ጨረታውን ያሸነፈ ተወዳዳሪ ጨረታውን መሸነፉ ተገልጾለት እስከ 5 ቀናት ድረስ ቀርቦ የግዢውን ጠቅላላ ዋጋ 10% በገንዘብ በማስያዝ ውሉን መፈረም አለበት። ያስያዙት ብር ተመላሽ የሚሆነው እቃውን ሙሉ በሙሉ ካቀረቡ በኋላ ይሆናል።
- ጨረታው ጋዜጣ ላይ ከወጣ ቀን አንስቶ እስከ 5 (አምስት) ቀናት ማንኛውም ተወዳዳሪ በጨረታው ሰነድ ላይ መግለጫ ወይም ማሻሻያ ጥያቄ ማቅረብ ይችላል።
- ይህን ጨረታ ለማደናቀፍ የሚሞክር ተወዳዳሪ ከጨረታ ውጪ በመሆን ለወደፊትም መንግስት በሚያወጣው ጨረታ ላይ እንዳይካፈልና የጨረታው ማስከበሪያው የማይመለስለት ይሆናል።
- ፍ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
- የጨረታው አሸናፊ ዕቃዎቹን እስከ ወረዳ ፍ/ቤት የማቅረብ ግዴታ አለበት።
- አድራሻችን ከአ/አበባ ወደ ቡታጅራ በሚወስደው መንገድ ላይ 60 ኪ/ሜትር ርቀት ላይ ሌመን ከተማ ይገኛል።
- ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 011 3630 078፤ 113630028፣ 0927834645 ደውለው መጠየቅ ይቻላል፡፡
በደቡብ ምዕራብ ሸዋ ዞን የቀርሳና ማሊማ ወረዳ ፍ/ቤት
