Tender Detail

Tender Details

  • Company የአምቦ እግር ኳስ ማሰልጠኛ ማዕከል ጎል ፊፋ
  • Address አዲስ አበባ ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 0112609010
  • Website
  • Deadline01 Oct 2025, 12:00 AM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document PriceNot stated in the notice
  • Bid Securityጠቅላላ ዋጋ የኢትዮጵያ ብር 1%
  • opening date2025-10-01 00:00:00
  • Categories Sport Materials And Sportswear

የአምቦ እግር ኳስ ማሰልጠኛ ማዕከል ጎል ፊፋ በማዕከሉ ለሚያሠለጥናቸው ሠልጣኞችና አሠልጣኞች የተለያዩ የስፖርት ትጥቆችና የሥልጠና ቁሳቁሶች የክልሉ መንግሥት ባወጣው የግዢ አዋጅ ቁጥር157/2002 በመከተል በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡

የአምቦ እግር ኳስ ማሰልጠኛ ማዕከል ጎል ፊፋ


 

የጨረታ ማስታወቂያ

 

የአምቦ እግር ኳስ ማሰልጠኛ ማዕከል ጎል ፊፋ በማዕከሉ ለሚያሠለጥናቸው ሠልጣኞችና አሠልጣኞች የተለያዩ የስፖርት ትጥቆችና የሥልጠና ቁሳቁሶች የክልሉ መንግሥት ባወጣው የግዢ አዋጅ ቁጥር157/2002 በመከተል በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡

ዝርዝር ሁኔታዎች፡-

ይህ ጨረታ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ስለ ስፖርት ትጥቆች የሚገልጽ ዝርዝር ሰነድ (ዶክመንት/ የማይመለስ አንድ መቶ (100) የኢትዮጵያ ብር በመክፈል ዘወትር በሥራ ሰዓት በአምቦ እግር ኳስ ማሠልጠኛ ማዕከል ጎል ፊፋ ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ የሥራ ቀናቶች ውስጥ በጽ/ቤቱ ቢሮ ቁጥር 6 ድረስ በመምጣት የጨረታ ሰነዱን መግዛት ይችላሉ፡፡

የተጫራቾች ግዴታ፡-

  1. በዘመኑ የታደሰ የንግድ ፍቃድ ያላቸው፤ የዘመኑን ግብር የከፈሉና ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  2. የተጨማሪ እሴት ታክስ /VAT/ ተመዝጋቢ ከሆኑ፤ ተመዝጋቢ ስለ መሆናቸው የሚገልጽ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  3. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (TIN) ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  4. የታደሰ የምዝገባ የምስክረ ወረቀት ያላቸውና ለዚህ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  5. ተጫራቾች ከሚያቀርቡት ጠቅላላ ዋጋ የኢትዮጵያ ብር 1% በCPO በ ሲንቄ ባንከ በማስገባት፣ የጨረታ ዋስትና ከጨረታ ሰነዱ ጋር ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
  6. በአገልግሎት አቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ በአቅራቢነት የተመዘገቡና ሰርተፍኬት ያላቸው እና ኮፒውን ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  7. ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን ዋጋ በጨረታ ሰነዱ ላይ በመሙላት በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ በማድረግ ኮፒና ዋናውን ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ የሥራ ቀናት 4/13/97 እስከ 20/01/2018ዓ.ም ዘወትር በሥራ ሰዓት በአምቦ እግር ኳስ ማሠልጠኛ ማዕከል ጎል ፊፋ ቢሮ ቁጥር 6 ለዚሁ በተዘጋጀው ሳጥን የጨረታ ሰነዱን ማስገባት ይችላሉ፡፡ ከላይ በተገለጸው መሥሪያ ቤት አዳራሽ ውስጥ በ16ኛው ቀን በ21/01/2018 ዓ.ም ከረፋዱ 4፡00 ሰዓት ተዘግቶ ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት (ባይገኙበትም) በ4፡30 ሰዓት ይከፈታል፡፡
  8. አሸናፊው ድርጅት ማናቸውንም አስፈላጊ ወጪዎች ችሎ ያሸነፈባቸውን የስፖርት ትጥቆችና ቁሳቁሶች በሰዓቱ በማዕከሉ ቅጥር ጊቢ ውስጥ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
  9. ማዕከሉ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር 0112609010፣ 0911061618 ወይም 0112602341

አምቦ እግር ኳስ ማሰልጠኛ ማዕከል ጎል ፊፋ ደውለው መጠየቅ ይችላሉ፡፡

 

የአምቦ እግር ኳስ ማሰልጠኛ ማዕከል ጎል ፊፋ

 

Save Tender