Tender Detail

Tender Details


በኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር የደ/ማርቆስ መንገድ ጥገና ዲስትሪክት ለመንገድ ጥገና አገልግሎት የሚውል ጋቢዮን ቦክስ (ጋቢዮን ሳጥን) በሀገር ውስጥ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት በአቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ የተመዘገቡ ተጫራቾችን ይጋብዛል፡፡

በኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር የደ/ማርቆስ መንገድ ጥገና ዲስትሪክት


 

በድጋሚ የወጣ የጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ ቁጥር ጨ-06-2017

 

በኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር የደ/ማርቆስ መንገድ ጥገና ዲስትሪክት ለመንገድ ጥገና አገልግሎት የሚውል ጋቢዮን ቦክስ (ጋቢዮን ሳጥን) በሀገር ውስጥ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት በአቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ የተመዘገቡ ተጫራቾችን ይጋብዛል፡፡

በአቅራቢዎች ዝርዝር ያልተመዘገቡ ተጫራች ለሚመለከተው መንግስት መ/ቤት በማመልከት የምዝገባ ሰርተፍኬት ማግኘት ይቻላል፡፡

  1. የዕቃ ማስረከቢያ ቦታ ደ/ማርቆስ መንገድ ጥገና ዲስትሪከት ዕቃ ግምጃ ቤት ይሆናል፡፡ ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ የሚያስችላቸውን የዘመኑን ግብር የከፈሉበትን ከሚፈለገው አገልግሎት ጋር የተዛመደ ንግድ ሥራ ፈቃድ፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ ከፋይ መሆናቸውን ማረጋገጫ ሰርተፍኬት እና ተያያዥ ሰነዶችን በማቅረብ የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ ዘወትር በሥራ ሰዓት የማይመለስ ብር 300.00 (ሶስት መቶ) በኢ.መ.አ. ንግድ ባንክ አካውንት ቁጥር 1000322269165 በመክፈል ደ ማርቆስ መንገድ ጥገና ዲስትሪክት ግዥና አቅርቦት ቡድን ቢሮ በመቅረብ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ መግዛት ይቻላል፡፡
  2. የጨረታ አሸናፊ የሚሆነው በጨረታ ሰነድ ውስጥ በተመለከቱት መስፈርቶች መሠረት ሲሆን ጨረታው ዜግነትን ሳይመለከት ለማንኛውም አቅራቢ ክፍት ነው። የጨረታ ሠነድ የተዘጋጀው በአማረኛ ቋንቋ ነው።
  3. ተጫራቾች የሚጫረቱበትን የጨረታ ሰነድ የዋጋ (የፋይናንሻል) እና የቴክኒካል ጉዳዮች ለየብቻ በፖስታ በጥንቃቄ በማሸግ በዲስትሪክቱ ግዥና አቅርቦት ቡድን ቢሮ ለዚህ ተግባር በተዘጋጀው ሳጥን ገቢ የሚያደርጉት ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ 15 ቀናት አየር ላይ የሚውል ሲሆን በ16ኛው ቀን እስከ ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ድረስ ብቻ ነው።
  4. ተጫራቾች ከብር 50,000.00 ያላነሰ የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ በተረጋገጠ ቼክ ወይም በገንዘብ ያዥ በተፃፈ ቼክ ወይም የባንክ ዋስትና ሲ.ፒ.ኦ ከሰነዶቻቸው ጋር በማያያዝ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡ ከዚህ ውጭ በኢንሹራንስ ወይ በሌላ መልክ የሚቀርብ የጨረታ ማስከበሪያ ተቀባይነት የለውም፡፡
  5. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ጀምሮ በ16ኛው ቀን 2017 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡15 ሰዓት በደ/ማርቆስ መንገድ ጥገና ዲስትሪክት ቅጥር ግቢ ከሚገኘው የስብሰባ አዳራሽ ይከፈታል፡፡ ሆኖም ቀኑ በበዓል ወይም በእሑድ ምክንያት ዝግ ከሆነ በቀጣዩ የሥራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ይከፈታል፡፡
  6. ተጫራቾች በጨረታ ደንብና መመሪያ መሠረት ጨረታውን ማቅረብ አለባቸው። ከጨረታው መመሪያ ውጭ የሚቀርብ ማንኛውም ጨረታ ተቀባይነት የለውም፡፡
  7. መ/ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  8. ለበለጠ መረጃ ተጫራቾች የሚከተለውን አድራሻ መጠቀም ይቻላል፡፡

በኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር የደ/ማርቆስ መንገድ ጥገና ዲስትሪክት ግዥና አቅርቦት ቡድን

ስልክ ቁጥር- 0587713052/0911984416/0912049751

 

በኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር የደ/ማርቆስ መንገድ ጥገና ዲስትሪክት

 

Save Tender