በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር አቃቂ ቃሊቲ ክ/ከተማ የወረዳ 2 አስተዳደር ጽ/ቤት የጨረታ ቁጥር01/2018 በጀት አመት በስሩ ለሚገኙት የተለያዩ ጽ/ቤቶች መገልገያ የሚሆኑ ዕቃዎች ለመግዛት ይፈልጋል።
አቃቂ ቃሊቲ ክ/ከተማ የወረዳ 2 አስተዳደር ጽ/ቤት
የግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር አቃቂ ቃሊቲ ክ/ከተማ የወረዳ 2 አስተዳደር ጽ/ቤት የጨረታ ቁጥር01/2018 በጀት አመት በስሩ ለሚገኙት የተለያዩ ጽ/ቤቶች መገልገያ የሚሆኑ ዕቃዎች ለመግዛት በጨረታ ቁጥር:- 01/2018 የወጣው የጨረታ ማስታወቂያ፡-
ሎት 1 አላቂ የቢሮ ዕቃዎች የጨረታ ማስከበሪያ ብር - 20,000.00
ሎት 2 -የጽዳት ዕቃዎች. -የጨረታ ማስከበሪያ ብር 40,000.00
ሎት 3- የደንብ ልብሶች- የጨረታ ማስከበሪያ ብር 35.000
ሎት 4- ቋሚ እታ— የጨረታ ማስከበሪያ ብር 30,000.00
ሎት -5-የደንብ ልብስ ማሰፊያ አገልግሎት—የጨረታ ማስከበሪያ ብር 2,000.00
በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ስለሚፈልግ
በጨረታው መሳተፍ የምትፈልጉ ተጫራቾች ማሟላት ያለባቸው
1. በመጀመሪያ ደረጃ ሰነዱን መግዛት የሚችሉት ፤ የንግድ ምዝገባ የምስከር ወረቀት ያላቸው፤ የዘመኑን የታደሰ የንግድ ፍቃድ ማቅረብ የሚችሉ፤ ቲን ነበር ያላቸውና ቫት ተመዝጋቢ የሆኑ በአቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ የተመዘገቡ መሆን ይኖርባቸዋል፤
2 የጨረታውን ሰነድ ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ የሥራ ቀናት ውስጥ በወረዳ 2 አስተዳደር ፋይናንስ ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 203 2ኛ ፎቅ በሚገኘው ቢሯችን በመገኘት ከጠዋቱ 2፡30 -11:30 ሰዓት በብር 250.00 /ሁለትመቶ ሃምሳ ብር/በካሽ በመግዛት መጫረት ይችላሉ፡፡ የገዙትንም ሰነድ በእነዚሁ ቀናት ውስጥ ሞልተው በተጠቀሰው ቢሮ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ እስከ 11ኛው ቀን 3፡30 ሰአት ማስገባት ይኖርባችኋል፡፡
3. ተጫራቾች የሚያቀርቡት የመወዳደሪያ ሃሳብ የዕቃውን ዓይነት፤ ስም የተመረተበት ሀገር፤ የሞዴሉን ቁጥር የተመረተበትን ጊዜ ያካተተ መሆን ይገባዋል፤
4. ተጫራቾች የዕቃውን ናሙና ከየዓይነቱ እንዳንድ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፤ ከተጠየቀው ናሙና በላይያስገባ ተጫራች ከውድድር ውጭ ይደረጋል፡፡ የጨረታው ውጤት ከታወቀ በኋላ ያቀረቡት ናሙናዎች ለተሸናፊዎች ሲመለሱ የአሸናፊዎቹ ተጫራቾች ናሙና ግን አይመለስም ፤
5. ጨረታው ከተከፈተ በኋላ ተጫራቾች ባቀረቡት የመወዳደሪያ ሃሳብ ላይ ለውጥ ወይም ማሻሻያ ማድረግ ወይም እራሳቸውን ማግለል አይችሉም ፡፡
6. ግዥ ፈጻሚው አካል አሸናፊ ተጫራቾች በሚያቀርቡት እቃ ወይም አገልግሎት ላይ እንደአስፈላጊነቱ 20% መቀነስ ወይም መጨመር ይቻላል ፤
7. የጨረታው ሰነድ በሁለት ኤንቨሎፖች የሚቀርብ ሆኖ ዋና እና ፎቶ ኮፒ የጨረታው ሰነድ መቅረብ አለባቸው፤ እነዚህም ሰነዶች በጨረታው ሲቀርቡ ድርጅቶቹ ወይም ሕጋዊ ውከልና ባለው አካል መፈረም አለባቸው፤ በሰነዶቹ እና ፖስታዎቹ ላይ የድርጅቱ /አቅራቢው ማህተም መኖር ይገባል ፤ ሰነዱ በሚሞላበት ወቅት ስርዝ ድልዝ (ለማንበብ አስቸጋሪ) ከሆነ ከውድድር ውጪ ያስደርጋል፡፡
8. የጨረታው ሰነዱ በራሱ አንድ የጨረታ መመሪያና ውል መሆኑን ተጫራቾች መረዳት ይገባቸዋል፤
9. ተጫራቾች በኢትዮጵያ ሕግ ስለሙስና እና ጉቦ በተደነገገው መሰረት ሕጉን በማከበር ለመፈጸም ግዴታ መግባት ይኖርባቸዋል፤
10. የጨረታው ማስከበሪያ በሎት በተጠየቀው መሰረት በሲፒኦ (CPO) ዋስትና በወረዳ 02 አስተዳደርጽ/ቤት /woreda 02 administration office/ በሚል በማሠራት በዋናው ሰነድ ውስጥ ማቅረብ አለባቸው፤
11. የጨረታውን አካሂድ ለማዛባት የሚሞክር ማንኛውም ተጫራች ከጨረታው ውጪ እንደሚሆን እና ለወደፊቱም በመንግሥት ጨረታ እንደማይሳተፍ፤ ያስያዘው የጨረታ ማስከበሪያ /ሲፒኦ/እንደሚወረስ ማወቅ ይኖርበታል፤
12. ከፍያን በተመለከተ አቅራቢው ዕቃውን ሙሉ በሙሉ በጥራት እና በናሙና መሰረት ማቅረቡ በቴከኒክ ኮሚቴ ተረጋግጦ ወደ ንብረት ከፍል ገቢ ሲሆን የሚከፈል ይሆናል፤
13. ጨረታው በ11ኛው ቀን ከጠዋቱ 3፡30 ተዘግቶ በ4፡00 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በወረዳ 2 ህዳሴ አድራሽ ይከፈታል፡፡ 11ኛው ቀን የሥራ ቀን ላይ ካልዋለ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ይከፈታል፤
14. ተጫራቾች በጨረታው ሰነድ ላይ የማብራሪያ ወይም የማሻሻያ ጥያቄ ካላቸው የጨረታው ሰነድ የመከፈቻ ጊዜ ከአራት ቀናት በፊት ማቅረብ ይችላሉ፡፡
15. ተጫራቾች በጨረታው አፈፃፀም ሂደት ላይ ቅሬታ ካላቸው ለግዥ ቅሬታ ሰሚ ኮሚቴ በጽሑፍ ማቅረብ ይችላሉ ፤
16. አሸናፊዎች ያሸነፉበት እቃዎች ከጠቅላላው ዋጋ 10% ለውል ማስከበሪያ ውል በሚገቡበት ወቅት ማስያዣ ይጠበቅባቸዋል፡፡
17 በሚቀርበው የናሙና እቃ ላይ ልዩ ምልከት፣ የድርጅቱ ማህተም ማድረግ የተከለከለ ነው። ይህን አድርጎ የተገኘ ተጫራች ከውድድር ውጪ ይደረጋል፡፡ ናሙናዎችን ለመለየት ወረቀት ላይ ማህተም በማድረግ መለጠፍ ይቻላል።
18. ወረዳ 2 አስተዳደሩ ጨረታውን በከፊል ወይም በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፤
አድራሻ፡- አቃቂ ቃሊቲ ከ/ከተማ ቆርቆሮ ፋብሪካ ሳይደርሱ ወረዳ 2 አስተዳደር ሕንጻ ፋይናንስ ጽ/ቤት
2ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 203 ይገኛል ፤
ስተጨማሪ መረጃ የስልክ ቁጥር ፦ 0912122379 /0114351419/ ደውለው ማረጋገጥ ይችላሉ፡፡
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር አቃቂ ቃሊቲቲ ክ/ከተማ የወረዳ 2 አስተዳደር ጽ/ቤት
