Tender Detail

Tender Details


የካ ም/ጮራ አፀደ ህፃናት የመጀመሪያ ደረጃ ት/ቤት የ2017 በጀት ዓመት ለት/ቤቱ አገልግሎት የሚውል አላቂ የቢሮ እቃ፤ የፅህፈት እቃዎች፤ የሰራተኛ የደንብ ልብስ፤ አላቂ የፅዳት እቃዎች፤ የስፖርት እቃዎች የኮምፒዩተር የፎቶ ኮፒ እና ቋሚ እቃ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።

የካ ም/ጮራ አፀደ ህፃናት የመጀመሪያ ደረጃ ት/ቤት


 

የጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ ቁጥር 02/2017

 

  1. የካ ም/ጮራ አፀደ ህፃናት የመጀመሪያ ደረጃ ት/ቤት የ2017 በጀት ዓመት ለት/ቤቱ አገልግሎት የሚውል አላቂ የቢሮ እቃ፤ የፅህፈት እቃዎች፤ የሰራተኛ የደንብ ልብስ፤ አላቂ የፅዳት እቃዎች፤ የስፖርት እቃዎች፤ የኮምፒዩተር የፎቶ ኮፒ እና ቋሚ እቃ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል። ስለሆነም በጨረታው መሳተፍ የሚፈልጉ ህጋዊ ተጫራቾች የሚከተሉትን መስፈርቶች አሟልተው በጨረታው መሳተፍ ይችላሉ።
  2. በዘርፉ የታደሰ የንግድ ፈቃድ እና የዘመኑን ግብር የከፈሉበት ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ
  3. በተጨማሪ እሴት ታክስ /VAT/ እና የግብር ከፋይ መለያ /TIN NO/ የምስክር ወረቀት ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ
  4. ተጫራቾች የሚያቀርቡት ዋጋ 5,000.00 /አምስት ሺህ ብር/ በባንክ የተሰራበት ሲፒኦ /CPO/ የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ከሰነዱ ጋር ማቅረብ የሚችሉ። /በየካ ምስራቅ ጮራ አፀደ ህፃናትና የመጀመሪያ ደረጃ ት/ቤት ስም ያሰሩ/
  5. ተጫራቾች የተጫራች መመሪያ ዋጋ ማቅረቢያ ሰነድ የማይመለስ 200 /ሁለት መቶ ብር/ በመክፈል ከት/ቤት ፋይናንስ ክፍል ቢሮ ቁጥር 6 ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ጊዜ ጀምሮ ባሉት ተከታታይ 10 የስራ ቀናት መግዛት ይችላሉ።
  6. ተጫራቾች በዋጋ ማቅረቢያ ሰነዱ መሰረት የሚወዳደሩበትን ዋጋ በፖስታ በማሸግ ለጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ማስገባት ይችላሉ።
  7. ተጫራቾች ለሚወዳደሩበት እቃዎች ፖስታውን ለማስገባት ሲመጡ ናሙና ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
  8. የጨረታ አሸናፊዎች እቃዎቹን ት/ቤቱ ድረስ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
  9. ጨረታው ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ተከታታይ 10 የስራ ቀናቶች በመጨረሻም በ11ኛው ቀን 4፡00 ሰዓት ተዘግቶ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በ11ኛው የስራ ቀን ከጠዋቱ 4፡30 ላይ በት/ቤቱ ፋይናንስ ግዢንን/አስ/ጠ/አገ ደጋፊ የስራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 04 ይከፈታል።
  10. ት/ቤቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታዎች
  11. በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

ለበለጠ መረጃ ስልክ ቁጥር፡- 0116 18 17 68 ወይም 09 10 32 89 95 በመደወል እንዲሁም በአካል ለሚመጡ በእንግሊዝ ኤምባሲ ዋና በር ወደ ባልደራስ ኮንዶሚኒየም በሚወስደው መንገድ 200ሜ ገባ ብሎ

  1. በየካ ክ/ከተማ በወረዳ 7 የካ ምስራቅ ጮራ አፀደ ሕፃናትና የመጀመሪያ ደረጃ ት/ቤት

 

የካ ም/ጮራ አፀደ ህፃናት የመጀመሪያ ደረጃ ት/ቤት

 

Save Tender