የኢትዮጵያ አማኑኤል ባፕቲስት ቤተ ክርስቲያን የልማት ድርጅት በትግራይ ክልላዊ መንግስት በአዲግራት ከተማ ላይ ከታች የተዘረዘሩትን አቅርቦቶች ለማግኘት ህጋዊ ፈቃድ ያላቸውን አቅራቢዎች ማወዳደር ይፈልጋል።
የኢትዮጵያ አማኑኤል ባፕቲስት ቤተ ክርስቲያን የልማት ድርጅት
የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር 01/2017
የኢትዮጵያ አማኑኤል ባፕቲስት ቤተ ክርስቲያን የልማት ድርጅት በትግራይ ክልላዊ መንግስት በአዲግራት ከተማ ላይ ከታች የተዘረዘሩትን አቅርቦቶች ለማግኘት ህጋዊ ፈቃድ ያላቸውን አቅራቢዎች ማወዳደር ይፈልጋል። በዚህም መሰረት ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የሚያሟሉ እና ከታች በተጠቀሰው መዳረሻ ከተማ ድረስ የተዘረዘሩትን የምግብ ዓይነቶች ማቅረብ የሚችሉ የጨረታ ሰነዶቻቸውን ማቅረብ ይችላሉ፡፡
የመወዳደሪያ መስፈርቶች
- አግባብነት ያለው የታደሰ የንግድ አቅራቢነት ፈቃድ
- የግብር ከፋይነት ሰርተፊኬት (TIN Certificate) ማቅረብ የሚችል
- የዓመቱን ግብር የከፈሉበትን/ታክስ ክሊራንስ ማስረጃ
- ከዚህ በፊት ተመሳሳይ አቅርቦት ያደረጉበት ልምድ (ካለ)
- ሌሎች ህጋዊ ደጋፊ ማስረጃዎች (ካሉ)
|
ተ.ቁ |
የአቅርቦት አይነት |
ብዛት በኪሎ ግራም |
መዳረሻ ቦታ |
|
1 |
1ኛ ደረጃ በቆሎ |
237,000 ኪ.ግ |
አዲግራት ከተማ |
|
2 |
1ኛ ደረጃ ሺምብራ |
23,700 ኪግ |
አዲግራት ከተማ |
|
3 |
የምግብ ዘይት |
7,900 ሊትር |
አዲግራት ከተማ |
|
4 |
ፋፋ የልጆች ምግብ |
24,885 ኪ.ግ |
አዲግራት ከተማ |
ተጫራቾች የጨረታው ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 የስራ ቀናት ቅዳሜን ጨምሮ የባንክ ከአጠቃላይ ዋጋው 2 በመቶ የማያንስ የባንክ ዋስትና ማሲያዣ (ሲፒኦ) ለእያንዳንዱ ዕቃ የጨረታ ሰነድ በብር 300 (ሶስት መቶ) በመግዛት የመወዳደሪያ ሰነዳችሁን እስከ መስከረም 07 ቀን 2018 ድረስ ማስገባት ትችላላችሁ። ጨረታው በማግስቱ መስከረም 08 ቀን 2018 ዓ.ም ከረፋዱ 4፡30 ሰዓት ላይ ተጫራቾች በተገኙበት ይከፈታል፡፡
አድራሻ፡- ቂርቆስ ክፍለ ከተማ ወረዳ 08 ካዛንቺስ በቅርቡ የፈረሰው ቶታል ማደያ ፊት ለፊት ኦሜጋ ታወር ጀርባ በኢትዮጵያ አማኑኤል ባፕቲስት ቤተክርስቲያን የአዲስ አበባ አማኑኤል ባፕቲስት ቤተክርስቲያን ግቢ ውስጥ፡፡
ስ.ቁ 011-550-37-84/0911-10-21-80/0911-17-18-74/0913-72-55-06::
ማሳሰቢያ፡- ተጫራቾች የሚያቀርቡት ዕቃ ወይም ምርት ጥራቱን የጠበቀ መሆን አለበት። በተጨማሪ የሚያቀርቡት ዋጋ የተ.እ.ታን እና የማድረሻ ዋጋውን ያካተተ መሆን አለበት፡፡ የኢትዮጵያ አማኑኤል ባፕቲስት ቤተክርስቲያን የልማት ድርጅት ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው፡፡
የኢትዮጵያ አማኑኤል ባፕቲስት ቤተ ክርስቲያን የልማት ድርጅት
