Tender Detail

Tender Details

  • Company በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ወረዳ 12 የዕውቀቴ ወገኔ ቅድመ መደበኛ ፣ አንደኛ ደረጃ እና መካከለኛ ደረጃ ት/ቤት
  • Address አዲስ ከተማ / ክ/ከ/ወረዳ 12 የዕውቀቴ ወገኔ ቅድመ መደበኛ ፣ አንደኛ ደረጃ እና መካከለኛ ደረጃ ት/ቤት ከአጠና ተራ ወደ አስራ ስምንት በሚወስደው መንገድ 18 አደባባይ ሳይሻገር ድልድዩ ስር ፡ አዲስ አበባ ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 011-2-73-90-66
  • Website
  • Deadline18 Sep 2025, 12:00 AM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document Price200.00
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening date2025-09-18 00:00:00
  • Categories Textile, Garment & Leather , Catering And Cafeteria Services , Construction Works

በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ወረዳ 12 የዕውቀቴ ወገኔ ቅድመ አንደኛ፣ አንደኛ እና መካካለኛ ደረጃ ት/ቤት በ2018 ዓ.ም የስራ ዘመን የሰራተኛ ክበብ እና ለቢሮ የሚሆኑ ክፍሎች እና የደንብ ልብስ ስፌት ማለትም ከሎት 1 እስከ ሎት 2 በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል።

በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ወረዳ 12 የዕውቀቴ ወገኔ ቅድመ መደበኛ ፣ አንደኛ ደረጃ እና መካከለኛ ደረጃ ት/ቤት


 

ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ መለያ ቁጥር፡- 002/2018

 

በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ወረዳ 12 የዕውቀቴ ወገኔ ቅድመ አንደኛ፣ አንደኛ እና መካካለኛ ደረጃ ት/ቤት በ2018 ዓ.ም የስራ ዘመን የሰራተኛ ክበብ እና ለቢሮ የሚሆኑ ክፍሎች እና የደንብ ልብስ ስፌት ማለትም ከሎት 1 እስከ ሎት 2 በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል።

ሎች 1 (አንድ) - (ለመሰረተ ልማት ዕድሳት/ ወጪ መደብ 6244 2% ብር 47,973፤

ሎት 2 (ሁለት) - የደንብ ልብስ ስፌት/ 6211 0.5% ብር 9,000

  1. ተጫራቾች በአቅራቢዎች ዝርዝር /supplier list/ በአላየን መመዝገባቸውን ማቅረብ አለባቸው።
  2. ተጫራቾች የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያላቸው እንዲሁም የዘመኑን ግብር የከፈሉ እና ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው።
  3. የተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) ሰርተፊኬት እና የታክስ ከፋይነት ቲን ቁጥር ሊኖራቸው ይገባል።
  4. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 200 (ሁለት መቶ ብር ብቻ) በመክፈል ዘወትር በስራ ሰዓት አዲስ ከተማ ክ/ከ/ ወረዳ 12 የዕውቀቴ ወገኔ ቅድመ መደበኛ፣ አንደኛ ደረጃ እና መካካለኛ ደረጃ ት/ቤት ከአጠና ተራ ወደ አስራ ስምንት በሚወስደው መንገድ 18 (አስራ ስምንት) ሳይሻገር ድልድዩ ስር ይገኛል። የዕውቀቴ ወገኔ ቅድመ መደበኛ፣ አንደኛ ደረጃ እና መካካለኛ ደረጃ ት/ቤት ቢሮ ቁጥር 5 ክፍያና/ሂ/አስተዳደር ቢሮ ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 (አስር) የስራ ቀናት ከ2፡30 - 11፡30 ከምሳ ሰዓት ውጪ ሰነድ መግዛት ይችላሉ።
  5. በጨረታ ሰነዱ ላይ ያለውን በሎች ሁለት (2) የደንብ ልብስ ስፌት ናሙና ማሳየት ግዴታ አለባቸው።
  6. አንዱ በሰጠው ዋጋ ላይ ሌላው ተንተንተርሶ መስጠት አይችልም።
  7. ተወዳዳሪዎች የሚያቀርቡትን ሰነድ ዋናውን (ፋይናንሻል) እና ፎቶ ኮፒውን (ቴክኒካል) ሰነዶችን ለየብቻ በፖስታ በማሸግ ከላይ በተጠቀሰው አድራሻ ወይም ቢሮ ለዚህ ጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ዘወትር በስራ ሰዓት እስከ 11፡30 ሰዓት ድረስ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
  8. ጨረታው የሚከፈተው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በ11ኛው ቀን በ4፡00 ሰዓት ታሽጎ በእለቱ በ4፡30 ሰዓት ይከፈታል። በአስራ አንደኛው ቀን ምንም አይነት የጨረታ ሰነድ የማንቀበል ይሆናል።
  9. የሚቀርበው የመወዳደሪያ ሀሳብ ላይ የድርጅቱ ሀላፊ ስምና ፊርማ፣ የድርጅቱ አድራሻ እና ስልከ ቁጥር መኖር አለበት።
  10. ለአሸናፊ ተጫራቾች በሰነዱ ውስጥ የተመለከተውን የጊዜ ገደብ ውስጥ ማለትም እስከ 7ኛ ቀን ድረስ ቀርበው የውል ማስከበሪያ ያሸነፉበትን የእቃ ዋጋ 10% ገቢ አድርገው ውል መዋዋል አለባቸው፡፡
  11. መስሪያ ቤቱ ተገቢ ነው ብሎ ካመነበት ከጨረታው አሸናፊ ድርጅት ጋር እስከ 6 ወር ድረስ ውሉን ቢያድስም ባያድስም ስራውን የማሰራት መብቱ የተጠበቀ ነው። በሎት 2 ላይ ያለውን ይመለከታል።የሚሰራው ስራ እስከ 20% ሊጨምር ወይም ሊቀንስ ይችላል። በሎት 1 እና ሎት 2 ላይ ያለውን ይመለከታል።
  12. በጨረታ ሰነድ መመሪያ ላይ በተጫራቹ የሚሞል ሁሉንም ሰነድ መሞላት አለበት። ሳይሞላ ቢቀር ጨረታው ላይ ውድቅ ቢሆኑ መስሪያ ቤቱ ኃላፊነት አይወስድም።
  13. ተጫራቾች በጨረታው ሂደት ቅሬታ ካላቸው በት/ቤቱ ገንዘብ የግዢ አ/ጠ/እ ሂሣብ (ደገፈ የሥራ ሂደት ቅሬታቸውን በጽሁፍ ማቅረብ ይችላሉ። በደጋፊ የስራ ሂደቱ የማይፈታ ከሆነ ደረጃውን ጠብቀው ለሚመለከተው አካል ማቅረብ ይችላሉ። የጨረታው ውጤት በተገለፀ በ7 ቀን (ሰባት) ቀናት ውስጥ ቅሬታውን ያላቀረበ ተጫራች በውጤቱ እንደተስማማ ተቆጥሮ ግዥው ከአሸናፊው ጋር ውል ይፈጽማል።
  14. አሸናፊው ድርጅት የግዢውን ውል ከፈረመበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 (አስር) ቀናት ውስጥ ስራውን መጀመር አለባቸው።
  15. ተጫራቹ (በሎት 1) የሰራተኛ ክበብ እና የተለያዩ ለቢሮ የሚሆኑ ክፍሎች ሙሉ በሙሉ እቃዎች በአሸናፊ ድርጅት የሚሸፈን ይሆናል።
  16. ማንኛውም ተጫራች ለሚያስገባቸው ዋጋ ቫትን ጨምሮ መሆን አለበት። እንዲሁም ያሸነፉበትን ስራ (በሎት 2) የደንብ ልብስ ስፌት፣ የልብስ መስፊያ ማሽኑን ት/ቤቱ ድርስ በማምጣት መስራት አለበት።ሲጨርስ ለግምጃ ቤት ማስረከብ አለበት።
  17. ተጫራቾች በሚያቀቡት የመወዳደሪያ ሰነድ ላይ የሚቀርቡት የስራ አይነት ዋጋ ላይ ሰርዝ ድልዝ የሌለበት ስልጣን ባለው አካል የተፈረመባቸው የተሟላ አድራሻቸውን የሚገልጽና ህጋዊ ማህተም ያረፈበት ሊሆን ይገባል።
  18. መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
  19. የአነስተኛ እና ጥቃቅን ተጫራቾች አምራች መሆናችሁን የሚገልፅ ደብዳቤ በማምጣት ሰነድ መውሰድ የምትችሉ መሆኑን እንገልፃለን።

 

አድራሻ፡- አዲስ ከተማ ክ/ከ/ ወረዳ 12 የእውቀቴ ወገኔ ቅድመ አንደኛ፣ አንደኛ እና መካካለኛ ደረጃ ት/ቤት ከአጠና ተራ ወደ አስራ ስምንት በሚወስደው መንገድ 18 (አስራ ስምንት) ሳይሻገር ድልድዩ ስር

ለበለጠ መረጃ የስልክ ቁጥር፡- 011-2-73-90-66 ወይም 011-2-79-11-29

 

የእውቀቴ ወገኔ ቅድመ አንደኛ፣ አንደኛ እና መካከለኛ ደረጃ ት/ቤት

 

Save Tender