Tender Detail

Tender Details

  • Company የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልላዊ መንግስት የአቡራሞ ወረዳ ገንዘብ ኢኮኖሚ ልማት ጽ/ቤት
  • Address ደቡብ ፡ ኢትዯጵያ, Phone: +251913514020
  • Website
  • Deadline20 Sep 2025, 12:00 AM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document Price500.00
  • Bid Securityበየ ሎቱ ይለያያል
  • opening date2025-09-19 00:00:00
  • Categories Textile, Garment & Leather , Stationery Materials , Vehicle tire

የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልላዊ መንግስት የአቡራሞ ወረዳ ገንዘብ ኢኮኖሚ ልማት ጽ/ቤት በ2018 የበጀት ዓመት ለመ/ቤቱና ለወረዳው ሴከተር መ/ቤቶች አገልግሎት የሚውል የደንብ ልብስ፤ የመኪና ጎማ ፤ የጽ/መሳሪያ በግልፅ ጨረታ የግዥ ዘዴ አወዳድሮ ለመግዛት የሚከተሉትን መስፈርቶች በጨረታ ሠነዱ ላይ የተዘረዘሩትን የተጫራቾችን መመሪያ የሚያሟሉ ድርጅቶችን አወዳድሮ ግዥ ለመፈፀም ይፈልጋል፡፡

የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልላዊ መንግስት የአቡራሞ ወረዳ ገንዘብ ኢኮኖሚ ልማት ጽ/ቤት


                                                                                   የጨረታ ማስታወቂያ

የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልላዊ መንግስት የአቡራሞ ወረዳ ገንዘብ ኢኮኖሚ ልማት ጽ/ቤት በ2018 የበጀት ዓመት ለመ/ቤቱና ለወረዳው ሴከተር መ/ቤቶች አገልግሎት የሚውል የደንብ ልብስ፤ የመኪና ጎማ ፤ የጽ/መሳሪያ በግልፅ ጨረታ የግዥ ዘዴ አወዳድሮ ለመግዛት የሚከተሉትን መስፈርቶች በጨረታ ሠነዱ ላይ የተዘረዘሩትን የተጫራቾችን መመሪያ የሚያሟሉ ድርጅቶችን አወዳድሮ ግዥ ለመፈፀም ይፈልጋል፡፡ 

  1. በዘርፍ የተሰማሩበት የአቅራቢነት ምዝገባ ምስክር ወረቀት ያለው፣ 

  2. የዘመኑ ግብር የከፈለ፣ 

  3. የተጨማሪ እሴት ታከስ ተመዝጋቢ የሆነ፣ 

  4. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ያለው፣ 

  5. የታደሰ ንግድ ፍቃድ፣ 

  6. የጨረታውን ሠነድ በፌዴራል የመንግስት ግዢ እና ንብረት ማስወገድ ኤጀንሲ 500/አምስት መቶ/ብር ጨረታው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በሥራ ሰዓት ከጠዋት 2፡30 እስከ 11፡30 ሰዓት ድረስ በአካል ቀርበው መግዛት ይችላሉ፡፡ 

  7. ተጫራቾች የተጫረቱበትን የጨረታ ማስከበሪያ ዋጋ ለደንብ ልብስ 100,000/አንድ መቶ ሺህ ብር/ ለመኪና ጎማ 40,000/አርባ ሺህ ብር/ ለጽ/መሳሪያ 25,000/ሃያ አምስት ሺ ብር/ በባንክ በተረጋገጠ CPO ከዋጋ ማቅረቢያ ሠነድ ጋር በማያያዝ ማቅረብ አለባቸው:: 

  8. የገዙትን የጨረታ ሠነድ ማስታወቂያ ከወጣበት ከ5 ቀን በኋላ ለጨረታ በተዘጋጀው የጨረታ ሣጥን ውስጥ ማስገባት ይችላሉ፡፡ 

  9. ጨረታው ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጅምሮ ለተከታታይ 15 ቀናት በአየር ላይ ውሎ በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዕለቱ 4፡30 ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በፌዴራል የመንግስት ግዢ እና ንብረት ማስወገድ ኤጀንሲ ውስጥ ይከፈታል ዕለቱ የእረፍት ቀን አሊያም የበዓል ቀን ላይ ከዋለ በቀጣዩ የሥራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ተዘግቶ የሚከፈት ይሆናል፡፡ 

  10. ተጫራቾች ጨረታውን ካሸነፉ ንብረቶቹን የሚያሰረክቡበት ቦታ በቤ/ገ/ክ/መ/የአቡራሞ ወረዳ ገ/ኢ/ል/ጽ/ ቤት ንብረት ከፍል ድረስ በማምጣት ይሆናል፡፡ 

  11. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዳቸውን ማስገባት ያለባቸው ቴከኒካል ሰነድ አንድ ኦርጅናል እና ሁለት ኮፒ በማድረግ በተለያዩ ሶስት ፖስታዎች በማሸግ እንዲሁም በተመሳሳይ የፋይናሻል ሰነዳቸውን አንድ ኦርጅናል እና ሁለት ኮፒ በማድረግ በተለያዩ ሶስት ፖስታዎች በማሸግ በድምሩ 6 በአንድ ማዘር ቦርድ ፖስታ አድርጎ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡ 

  12. ተጫራቾች ጨረታውን አሸናፊ ሊሆኑ የሚችለው በነጠላም ወይም በጥቅል ዝቅተኛ ዋጋ ያቀረበ ተወዳዳሪ የጨረታው አሸናፊ ሊያደርግ ይችላል፡፡ 

  13. ዋጋ ማቅረብ የምትችሉት በገዛችሁት ሰነድ ብቻ ይሆናል ሙሉ የጨረታ ሰነዱ ማህተም ተመትቶ አብሮ መመለስ አለበት፡፡ 

  14. ማሳሰቢያ ማንኛውም ተጫራች ለእያንዳንዱ ለሚወዳደሩበት ዕቃ ማለትም ለደንብ ልብስ እና ለጽ/ መሳሪያዎች ናሙናውን ጨረታው የሚከፈትበት ቀን ማቅረብ የሚገባው ሲሆን የመኪና ጎማና የፈርኒቸር አቃዎችን ግን መ/ቤቱ በየድርጅቶቹ በመሄድ የሚያይ ይሆናል፡፡ 

  15. መ/ቤቱ በሰነዱ ላይ ከተጠቀሰው ብዛት 20% ጨምሮ ወይም 20% ቀንሶ የመግዛት መብቱ የተጠበቀ ይሆናል፡፡ 

  16. በተጨማሪም ተጫራቾች በጨረታው ሠነዱ ላይ የተጠቀሱትን የ ይኖርባቸዋል፡፡ 

  17. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታው ሙሉ በሙሉም  ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

                   ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር +251912007671  

                           የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልላዊ መንግስት የአቡራሞ ወረዳ ገንዘብ ኢኮኖሚ ልማት ጽ/ቤት

Save Tender