የካ ቅድመ 1ኛ፣ አንደኛ እና መካከለኛ ደረጃ ት/ቤት ለ2018 ዓ.ም ለት/ቤቱ አገልግሎት የሚውሉ የተለያዩ ዕቃዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
የካ ቅድመ 1ኛ፣ አንደኛ እና መካከለኛ ደረጃ ት/ቤት
ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
የግዢ መለያ ቁጥር የካ/መ001/2018
የካ ቅድመ 1ኛ፣ አንደኛ እና መካከለኛ ደረጃ ት/ቤት ለ2018 ዓ.ም ለት/ቤቱ አገልግሎት የሚውሉ የተለያዩ ዕቃዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
ሎት 1/ የሠራተኛ ደንብ ልብስ
ሎት 2/ አላቂ የትምህርት ዕቃዎች
ሎት 3/ አላቂ የቢሮ ዕቃዎች
ሎት 4 አላቂ የጽዳት ዕቃዎች
ሎት 5/ ቋሚ ባህላዊና ዘመናዊ የሙዚቃ መሣሪያዎች
ሎት 6/ ቋሚ የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች
ከላይ ዝርዝራቸው የተጠቀሱትን ዕቃዎችን ለማቅረብ የምትፈልጉ ተጫራቾች ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የምታሟሉ መሳተፍ የምትችሉ መሆኑን እንገልፃለን፡፡
-
- በዘመኑ የታደሰ ንግድ ፈቃድ
- የዘመኑን ግብር የከፈለ
- የቫት ከፋይ የሆነ
- የተጨማሪ እሴት ታክስ ከፋይና የቲን ቁጥር የሚያቀርብ
- ሕጋዊ ደረሰኝ (ካሽ ሬጂስተር ደረሰኝ) ማቅረብ የምትችሉ
- ጥቃቅንና አነስተኛ ከሆነ ከጥቃቅንና አነስተኛ ተቋማት የተፃፈ የድጋፍ ደብዳቤ ማቅረብ የሚችል ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በአስር ተከታታይ የሥራ ቀናት ተጫራቾች የግዢ ጨረታ ሰነዱን ለመግዛት ብር 200.00 /ሁለት መቶ ብር/ በመክፈል ከት/ቤቱ ፋይናንስ ክፍል መውሰድ የምትችሉ መሆኑን እንገልፃለን፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ /ቢድ ቦንድ / በየሎቱ የበጀቱ 0.5% ወይም ሎት 1/ ብር 7,500 /ሰባት ሺህ አምስት መቶ ብር ብቻ/ ፣ ሎት 2/ 8,500 /ስምንት ሺህ አምስት መቶ ብር ብቻ/ ፣ ሎት 3/ 3,370 /ሦስት ሺህ ሦስት መቶ ሰባ ብር ብቻ፣ ሎት 4/ 7,900 /ሰባት ሺህ ዘጠኝ መቶ ብር ብቻ/ ፣ ሎት 5/ 8,500 /ስምንት ሺህ አምስት መቶ ብር ብቻ/ ፣ ሎት 6/ 7,500 /ሰባት ሺህ አምስት መቶ ብር ብቻ/ በባንክ በተረጋገጠ ማስረጃ ሲፒኦ ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች ውል ሲገቡ የውል ማስከበሪያ /ቢድ ቦንድ / 10% በባንክ በተረጋገጠ ማስረጃ ሲፒኦ ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡ ተጫራቶች የሚጫረቱበት ዋጋ ኦሪጅናልና ኮፒ በታሸገ ኤንቨሎፕ እስከ አስረኛው የሥራ ቀን ድረስ ማቅረብ አለባቸው፤ ከጠዋቱ 2፡30 ሰዓት ጀምሮ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- ጨረታው የጨረታ ተሳታፊዎች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በ11ኛው ቀን ከረፋዱ 3፡30 ሠዓት ታሽጎ 4፡00 ሠዓት ላይ ይከፈታል፡፡
- ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን ናሙና ማቅረብ አለባቸው።
- ጨረታው ከተከፈተ በኋላ ተጫራቾች ባቀረቡት የመወዳደሪያ ዋጋ ላይ ለውጥ ማሻሻያ ማድረግና ከጨረታው ራሳቸውን ማግለል አይችሉም እንዲሁም ከተጠየቀው ስፔስፊኬሽን ውጪ ዕቃ ማቅረብ አይፈቀድም፡፡
- ተጫራቾች በሚያቀርቡት መወዳደሪያ ሰነድ ላይ ስማቸውና ፊርማቸውን እና የድርጅታቸውን ማህተም እንዲሁም አድራሻቸውን ማስፈር አለባቸው።
- በውድድሩ አሸናፊ የሚሆኑ ተወዳዳሪዎች ማሸነፋቸው ከተገለፀበት ከ8ኛው ቀን ጀምሮ ባሉት 7 ተከታታይ የሥራ ቀናት ውስጥ ንብረቱን ት/ቤቱ ድረስ ገቢ ማድረስ አለባቸው፡፡
- ት/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
አድራሻ፡- በተለምዶ አበቤ ሱቅ ፊት ለፊት ያለውን አስፋልት ተሻግሮ እንግሊዝ ኤምባሲ ጎን ባለው አስፋልት 100 ሜትር ገባ ብሎ
-
- ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር፡- 0116-68-60-87/ 0911-83-22-42/
0932-89-86-96 መጠየቅ ይችላሉ፡፡
ማሳሰቢያ፡- ዋጋው የሚሞላው በወሰዳችሁት የጨረታ ሰነድ ላይ ነው
የካ ቅድመ 1ኛ፣ አንደኛ እና መካከለኛ ደረጃ ት/ቤት
