Tender Detail

Tender Details

  • Deadline11 Sep 2025, 12:00 AM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document Price300.00
  • Bid Security1%
  • opening date2025-09-11 00:00:00
  • Categories Food And Beverage

በአፋር ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት የሰመራ ሴቶች አዳሪ ትምህርት ቤት በ2018 በጀት ዓመት የተማሪ የምግብ ፍጆታ የሚሆን የምግብ አቅርቦት ሎት 1፣ ሌሎች አላቂ ዕቃዎች ግዥ ሎት 2 በአገር ውስጥ ገበያ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡


                                                                 ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ 

በአፋር ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት የሰመራ ሴቶች አዳሪ ትምህርት ቤት በ2018 በጀት ዓመት የተማሪ የምግብ ፍጆታ የሚሆን የምግብ አቅርቦት ሎት 1፣ ሌሎች አላቂ ዕቃዎች ግዥ ሎት 2 በአገር ውስጥ ገበያ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡

 ስለዚህ በጨረታው ለመወዳደር የምትፈልጉ ተጫራቾች ከዚህ በታች የተገለፁትን ነጥቦች ማሟላት ይኖርባችኋል፡፡ 

  1. ተጫራቾች ግዴታ ማሟላት ያለባቸው የቅድሚያ ማወዳደሪያ መስፈርቶች ማለትም፦ 

1.1 በዘርፍ የዘመኑ የታደሰ የንግድ ፈቃድ 

1.2 የንግድ ፈቃድ ምዝገባ ሰርተፊኬት ያለው

1.3 የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ የሆነ 

1.4 ሲ.ፒ.ኦ ማስያዝ አለበት

1.5 የጨረታ ሰነድ ግዥ የፈፀመ እና

1.6 የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር TIN ያለው ሰርተፊኬት ማቅረብ የሚችሉ፡፡  

  1. በጨረታው ለመሳተፍ የምትፈልጉ ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ከወጣበት ቀን ጀምሮ የጨረታውን ሰነድ በአፋር ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት የሠመራ ሴቶች አዳሪ ት/ቤት በግዥ/ፋይ/ንብ/አስ/ድጋፊ የሥራ ሂደት 300.00 ብር (ሦስት መቶ ብር) በመክፈል መውሰድ ትችላላችሁ፡፡ 

  2. ተጫራቾች በእያንዳንዱ በሚያቀርቡት የጨረታ ሰነዶች ላይ የተጫራቾች ወይም የህጋዊ ወኪል ፊርማና ማህተም ማኖር ይኖርባቸዋል፡፡ 

  3. ተጫራቾች የጨረታ ማስረከቢያ ዋስትና /Bid Bond/ ለውድድር የሚያቀርቡት ጠቅላላ ዋጋ 1% በሲ.ፒ.ኦ (CPO) የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡ የጨረታ ተወዳዳሪዎች በውድድሩ ከተሸነፉ ለዋስትና ያስያዙት የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና የጨረታው ውጤት ታውቆ ውል ከተፈራረሙ በኋላ ወዲያውኑ የውል ማስከበሪያው ይመለስላቸዋል፡፡  

  4. ጨረታው ከተከፈተ በኋላ ማንኛውም ተጫራች የሚያቀርቡትን የውድድር ጥያቄ ትምህርት ቤቱ አይቀበልም፡፡ 

  5. ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 10 ቀናት የሚቆይ ሆኖ በ10ኛው የሥራ ቀን 10፡00 ሰዓት የጨረታ ሳጥኑ የሚዘጋ ሲሆን በአለቱ 10፡30 ሰዓት በአፋር ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት የሠመራ ሴቶች አዳሪ ት/ቤት አዳራሽ ውስጥ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል። 

  6. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡ 

  7. በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልግ ተጫራች ስለ ጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለገ  በስ.ቁ 0936738489/ 0936435491 በመደወል ማግኘት ይችላሉ፡፡ 

                                                     በአፋር ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት የሰመራ ሴቶች አዳሪ ትምህርት ቤት

Save Tender