Tender Detail

Tender Details


በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 13 የቦሌ ኅብረተሰብ ቅድመ 1ኛ፤ 1ኛ እና መካከለኛ ደረጃ ት/ቤት ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ሎቶች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።

ቦሌ ክፍለ ከተማ ትምህርት መምሪያ የቦሌ ህብረተሰብ አጠቃላይ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት


 

1ኛ ዙር ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ ቁጥር 001/2018

 

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 13 የቦሌ ኅብረተሰብ ቅድመ 1ኛ፤ 1ኛ እና መካከለኛ ደረጃ ት/ቤት ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ሎቶች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል። በዚህ መሰረት ጨረታውን ለመሳተፍ የሚፈልጉ ሕጋዊ ተጫራቾች የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ መሆን አለባቸው።

  1. ተጫራቾች በዘርፉ የተሰማሩበትን ሕጋዊ ንግድ ፈቃድ ያላቸውና የዘመኑን ግብር ለመክፈላቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፤
  2. በገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ሚኒስቴር በአቅራቢነት የተመገቡና ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡
  3. የታደሰ ንግድ ፈቃድ ያለው፤
  4. የተጨማሪ እሴት ታክስ የምዝገባ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፤
  5. ተጫራቾች ከዚህ በታች የተጠቀሰውን የጨረታ ማስረከቢያ በባንክ የተረጋገጠ CPO ብቻ ማቅረብ አለባቸው።

 

ሎት ቁጥር

የሎት ዝርዝር

የተጠየቀው የጨረታ ማስከበሪያ በኢትዮጵያ ብር

ሎት 1

የደንብ ልብስ

ብር 40,000

ሎት 2

አላቂ የቢሮ እቃዎች

ብር 29,400

ሎት 3

አላቂ የትምህርት እቃዎች

ብር 36,000

ሎት 4

የሕትመት ሥራዎች

ብር 6,000

ሎት 5

የጽዳት እቃ

ብር 30,000

ሎት 6

ቋሚ የቢሮ እቃዎች

ብር 30,000

ሎት 7

ሕንፃና ቁሳቁስ ጥገና እቃዎች

ብር 3,000

ሎት 8

ፕላንትና ማሽነሪ እቃዎች

ብር 3,000

ሎት 9

አላቂ የሕክምና እቃዎች

ብር 2,000

 

  1. የጨረታ ሰነዱን ማስታውቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ የማይመለስ ብር 50.00 (ሃምሳ ብር) በመክፈል የተዘጋጀውን ሰነድ ከተቋሙ ቢሮ ቁጥር 04 እየቀረቡ መግዛት ይችላሉ።
  2. ተጫራቾች ጨረታው ከወጣበት ቀን አንስቶ ባሉት 10 (አስር) ተከታታይ የሥራ ቀናት ቢሮ ቁጥር 04 ድረስ በመምጣት ዋጋው የተሞላበትን የጨረታ ሰነዱን ዋናውንና ፎቶ ኮፒ ለየብቻው በማሸግ ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው።
  3. ጨረታው በ10ኛው ቀን በዕለቱ 10፡00 ታሽጎ 10፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡ የጨረታው መዝጊያና መክፈቻ የሥራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን በተጠቀሰው ተመሳሳይ ሰዓት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል።
  4. ተጫራቾች ያሸነፉበትን ዋጋ የውል ማስከበሪያ 10% ማስያዝ አለባቸው።
  5. ተጫራቾች ጨረታው ከመከፈቱ በፊት ለሚወዳደሩበት ናሙና ለሚቀርብባቸው እቃዎች ናሙና ማቅረብ አለባቸው፡፡ ናሙና ለማይቀርብባቸው ቋሚ እቃዎች መሥሪያ ቤቱ ባቀረበው እስፔስፊኬሽን መሠረት ማቅረብ አለባቸው።
  6. የጨረታው አሸናፊ ድርጅት ያሸነፈበትን እቃ በራሱ ትራንስፖርት የቦሌ ኅብረተሰብ ቅድመ 1ኛ ፣ 1ኛ እና መካከለኛ ደረጃ ት/ቤት ድረስ ማቅረብ ይኖርበታል።
  7. ት/ቤቱ ለጨረታ ከቀረበው ዕቃ እስከ 20% የመቀነስም ሆነ የመጨመር መብቱ የተጠበቀ ነው ።
  8. ት/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

አድራሻ፡- ከቦሌ ድልድይ 400 ሜትር ገባ ብሎ ቦሌ ሆምስ ፊት ለፊት ስልከ፡- 011 8 21 77 36 በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 13 የቦሌ ኅብረተሰብ ቅድመ 1ኛ፣ 1ኛ እና መካከለኛ ደረጃ ት/ቤት

 

የቦሌ ኅብረተሰብ ቅድመ 1ኛ ፣ 1ኛ እና መካከለኛ ደረጃ ት/ቤት

 

Save Tender