ስኬት ባንክ አ.ማ በባንኩ ውስጥ ለሚገኙ ቋሚና አላቂ ዕቃዎች እንዲሁም ለተለያዩ ተሽከርካሪዎች ማከማቻ አገልግሎት የሚውል በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ውስጥ የሚገኝ የመጋዘን ኪራይ አገልግሎት ግዥ በውል ለተገደበ ጊዜ አወዳድሮ በግልፅ ጨረታ መከራየት ይፈልጋል፡፡
Siket Bank (ስኬት ባንክ አ.ማ)
ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታው መለያ ቁጥር SB/OT/NCB/04/12/2017
ስኬት ባንክ አ.ማ በባንኩ ውስጥ ለሚገኙ ቋሚና አላቂ ዕቃዎች እንዲሁም ለተለያዩ ተሽከርካሪዎች ማከማቻ አገልግሎት የሚውል በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ውስጥ የሚገኝ የመጋዘን ኪራይ አገልግሎት ግዥ በውል ለተገደበ ጊዜ አወዳድሮ በግልፅ ጨረታ መከራየት ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም ተጫራቾች ማሟላት ያለባቸው፡-
- ተጫራቾች በዘርፉ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸውና የዘመኑን ግብር የከፈሉ የታደሰ የንግድ ፈቃድ እና ለተጨማሪ እሴት ታከስ (VAT) ከፋይነት የተመዘገቡ መሆኑን የሚያረጋግጥ የምስከር ወረቀት ማቅረብ አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 ተከታታይ ቀናት በማናቸውም የስራ ሰዓት /ከሰኞ እስከ ቅዳሜ / ከባንኩ ዋና መስሪያ ቤት 4ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 410 የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 500 /አምስት መቶ ብር /በመከፈል ሰነድ ገዝታችሁ በ16ኛው የስራ ቀን በባንኩ ዋ/መቤት ቢሮ ቁጥር 406 ለዚሁ ጉዳይ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ እስከ 4፡00 ሰዓት ድረስ ማስገባት ይኖርባችኋል፡፡ጨረታው በዚሁ እለት በ4፡00 ሰዓት ተዘግቶ በ4፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ባሉበት ወይም ባይገኙም የጨረታ ኮሚቴው እና ጨረታው የተሟላ ከሆነ የቴከኒካል ሰነድ ብቻ የሚከፈት ሲሆን የፋይናንሻል ሰነድ የሚከፈተው የቴከኒካል እና ሳይት ምልከታ ውጤታቸው ብቁ የሆኑ ተሳታፊዎች ብቻ ይሆናል፡፡
- ተጫራቾች አንድ ቴክኒካል ኦርጅናል ሰነድ አንድ ቴከኒካል ኮፒ ሰነድ እና አንድ ኦርጅናል ፋይናንሻል ሰነድ አንድ ኮፒ ፋይናንሻል ሰነድ በፖስታ ታሽጎ ማቅረብ አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች ለብቻው የጨረታ ማስከበሪያ በማሸግ ማቅረብ አለባቸው፡፡
- ጨረታው ከተከፈተ በኋላ አሸናፊ ተጫራቾች ከውድድሩ በራሳቸው ፈቃድ ቢወጡ ያስያዙት የጨረታ ማስከበሪያ ለባንኩ ገቢ ይሆናል፡፡
- ለመጋዘን ኪራይ አገልግሎት ሞልተው የሚያቀርቡት ዋጋ ተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ማካተት ይኖርበታል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታው ሰነድ በሚመልሱበት ጊዜ በሰነዱ ላይ በተጠቀሰው መሰረት መጋዘኑ የሚገኝበት ሙሉ አድራሻ ማስቀመጥ ይኖርባቸዋል፡፡ መጋዘኑ የሚገኝበትን አድራሻ ያላቀረበ ተጫራች ከጨረታ ውድድር ውድቅ ይደረጋል፡፡
- ተጫራቶች የሚያቀርቡት ዝርዝር ዋጋ በሚመለከት ከባንኩ በወሰዱት ሰነድ ላይየፋይናንሻል ዋጋ ማቅረቢያ ፎርማት ቅጽ መሰረት ሞልተው መመለስ ይኖርባቸዋል፡፡
- ስርዝ ድልዝ ኖሮት ካልተፈረመ፣ በፍሉድ የጠፋ ሰነድ፣ያልታሸገ ሰነድ፣የድርጅቱ ማህተም እና ፊርማ ያልተደረገበት ሰነድ ከጨረታ ውድድር ያሰርዛል፡፡
- አሸናፊው ከተለየ በኋላ ለተሸነፉ ተወዳዳሪዎች ለጨረታ ማስከበሪያ ያስያዙት ሲ.ፒ.ኦ ወይም ቢድ ቦንድ ይመለስላቸዋል፡፡
- ባንኩ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- ተጫራቹ የጨረታ ሰነዱን በሚመልሱበት ጊዜ ተጫራቹ ወይንም ህጋዊ ወኪሉ የጨረታ ሰነዱን ሞልቶ ስለመላኩ የሚገልፅ ቅፅ ከጨረታ ሰነዱ ጋር ሞልተው በፊርማና ማህተም በማረጋገጥ ማቅረብ አለባቸው፡፡
- የጨረታ መከፈቻው ቀን በስራ ቀን ካልዋለ የጨረታው መዝጊያውም ሆነ የመክፈቻው ቀን በሚቀጥለው የስራ ቀን በሚውልበት ቀን እና ሰዓት መሰረት ከላይ በተገለጸው የመዝጊያና የመከፈቻ ስነ-ስርዓት መሰረት የሚከናወን ይሆናል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነድ ሞልተው ሲመልሱ ፊርማና ማህተም በማድረግ ማቅረብ አለባቸው፡፡
|
ተ.ቁ |
የሚገዛው የአገልግሎት ዓይነት |
Cpo ወይም ባንከ ጋራንቲ |
|
1 |
የመጋዘን ኪራይ አገልግሎት |
40,000.00 |
ማሳሰቢያ፦ ተወዳዳሪዎች የሚያቀርቡት የኪራይ መጋዘን በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደርውስጥ የሚገኝ መሆን አለበት፡፡
- የባንኩ የስራ ቀናት ከሰኞ እስከ ቅዳሜ 2፡30 -11፡30 ብቻ ነው፡፡
አድራሻ፡- ቸርችል ጎዳና ከቴዎድሮስ አደባባይ ከፍ ብሎ ሃሮን ታወር ፊት ለፊት ስልክ ቁጥር፡ 011 1 27 55 85
ስኬት ባንክ አ.ማ
