Tender Detail

Tender Details


በሀዲያ ዞን ምሻ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት ያገለገሉ ተሽከርካሪዎች ትራክተር እና ሞተር ሳይከሎችን ባሉበት ሁኔታ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡ በመሆኑም በጨረታው ለመሳተፍ የምትፈልጉ ተጫራቾች ከዚህ በታች በተገለፀው መሠረት ቀርበው መወዳደር ይችላሉ።

በሀዲያ ዞን ምሻ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት


የ3ተኛ ዙር ጨረታ ማስታወቂያ

በሀዲያ ዞን ምሻ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት ያገለገሉ ተሽከርካሪዎች ትራክተር እና ሞተር ሳይከሎችን ባሉበት ሁኔታ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡ በመሆኑም በጨረታው ለመሳተፍ የምትፈልጉ ተጫራቾች ከዚህ በታች በተገለፀው መሠረት ቀርበው መወዳደር ይችላሉ።

ሎት - 1 ትራክተር

ሎት -2 ሞተር ሳይከሎችን

ተሽከርካሪዎቹ የሚገኙበት አድራሻ በሀዲያ ዞን ምሻ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት እና በምሻ ወረዳ ዋስገበታ ጤና ጣቢያ ቅጥር ግቢ ውስጥ ይገኛሉ፡፡

  • በተሽከርካሪዎች ጨረታ ማንኛውም ኢትዮጵያዊ የሆነ ግለሰብ _ ወይም ድርጅት መሳተፍ ይችላል፡፡
  • ተጫራቾች ስለአሻሻጡ የተዘጋጀውን ያገለገሉ ተሽከርካሪዎች የጨረታ መወዳደሪያ ሰነድና የዋጋ ማቅረቢያ ፎርም እና የተጫራቾች መመሪያ ጋዜጣው አየር ላይ ከዋለበት ቀን አንስቶ በተከታታይ 15/አስራ አምስት/ ቀናት ውስጥ በእያንዳንዱ ተሸከርካሪ በተናጠል፦ ሎት 1 ትራከተር ብር 200.00/ሁለት መቶ ብር/ ፣ ሎት 2 ሞተር ሳይክል ብር 100.00/አንድ መቶ ብር/ የማይመለስ ብር በመክፈል በሀዲያ ዞን ምሻ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት ግዥና ንብረት አስተዳደር ዋና የሥራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 16 በመቅረብ ዘወትር በሥራ ሰዓት ሰነድ መግዛት ይችላሉ፡፡
  • ተጫራቾች የሚወዳደሩትንተሽከርካሪ/ዎች በሎት በተናጠል ወይም በድምር የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና የመነሻ ዋጋ 20% በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ/CPO/ ብቻ ማስያዝ አለባቸው፡፡
  • የጨረታ መወዳደሪያ ዋጋ መሙያ መምሪያው ባዘጋጀው ፎርማት ላይ ብቻ በመሙላት ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15/አስራ አምስት/ ተከታታይ ቀናት የመወዳደሪያ ፖስታ አንድ ዋና/Original/ እና ቅጂ/Copy/ የጨረታ ሰነድ ለየብቻ በፖስታ ታሽጎና እንደገና ሁለቱም በአንድ ፖስታ ውስጥ ተካቶ በማሸግ ቢሮ ቁጥር 16 ላይ በሚገኘው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይጠበቅባቸዋል፡፡
  • ማንኛውም ተጫራች በዋጋ ማቅረቢያ ቅጽ ላይ ዋጋውን በግልጽ በአሃዝና በፊደል በመጻፍ በእያንዳንዱ በቀረበው ዋጋ ፊት ለፊት በፊርማ ማረጋገጥ አለባቸው ያልተፈረመ ሰነድ ዋጋ አይኖረውም፡፡
  • ተጫራቾች በተዘጋጀው የጨረታ ሰነድ መሠረት ከአንድ በላይ ተሽከርካሪ መጫረት ይችላሉ፡፡
  • ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በ16ኛው/አስራ ስድስተኛው/ቀን ከጠዋቱ 5፡00 ሰዓት ላይ የጨረታ ሳጥን ታሽጎ በ5፡30 ሰዓት ላይ የሚከፈት ሲሆን ቀኑ የበዓል ወይም የዕረፍት ቀን ከሆነ በቀጣይ ቀን በተመሳሳይ ሰዓትና ቦታ የሚከፈት መሆኑን እናሳውቃለን፡፡

 

 

 

  • ተጫራቾች በጨረታ ያሸነፉትን ተሸከርካሪዎች አሸናፊነታቸው በደብዳቤ በተገለጸ በ10/አስር/ የስራ ቀናት ውስጥ ማንሳት አለባቸው ሆኖም በተጠቀሱት ቀናት ውስጥ ገዢው ካላነሳ ለሚደርሰው ለማንኛውም ችግር ሻጭ ተጠያቂ አይሆንም፡፡
  • ተጫራቾች ለእያንዳንዱ ተሸከርካሪ ከመንግስት የሚፈለግ ግብርና ቀረጥ በሻጩ የሚሸፈን ይሆናል።
  • አሸናፊው ተጫራች የተሸከርካሪ ስም ማዘዋወሪያ እና ሌሎች ልዩ ልዩ ወጪዎች በሙሉ በአሸናፊው ይሸፈናል፡፡
  • ተጫራቾች የመነሻ ዋጋ እና የዋጋ ማቅረቢያ የጨረታ ሰነድ አካል ሲሆን ከጨረታ ሰነድ ጋር የተያያዘ ነው፡፡
  • መስሪያ ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

ለበለጠ መረጃ- በስልከ ቁጥር 0916168133/ 0910454656/ 0916673483/0954231528 ደውሎ መጠየቅ የሚቻል መሆኑን እንገልጻለን፡፡

በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግስት በሀዲያ ዞን ምሻ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት

Save Tender