Tender Detail

Tender Details


በሀዲያ ዞን ሌሞ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት ያገለገሉ ሞተር ሳይክሎችን ባሉበት ሁኔታ በድጋሚ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡


የጨረታ ማስታወቂያ

በሀዲያ ዞን ሌሞ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት ያገለገሉ ሞተር ሳይክሎችን ባሉበት ሁኔታ በድጋሚ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡

በመሆኑም በጨረታው ለመሳተፍ የምትፈልጉ ተጫራቾች፡-

1. ሞተር ሳይክሎች የሚገኙበት አድራሻ በሀዲያ ዞን ሌሞ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት ቅጥር ግቢ ውስጥ ይገኛሉ፡፡

2. በጨረታው ማንኛውም ኢትዮጵያዊ የሆነ ግለሰብ ወይም ድርጅት መሳተፍ ይችላል።

3. ተጫራቾች ስለአሻሻጡ የተዘጋጀውን የጨረታ መወዳደሪያ ሰነድና የዋጋ ማቅረቢያ ፎርም እና የተጫራቾች መመሪያ ጋዜጣ ከወጣበት ቀን አንስቶ በተከታታይ 15 /አስራ አምስት/ ቀናት ውስጥ በእያንዳንዱ ሞተርሳይከል ብር 100.00/አንድ መቶ ብር/ የማይመለስ በመከፈል በሀዲያ ዞን ሌሞ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት ግዥና ንብረት አስተዳደር ዋና የሥራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 14 በመቅረብ ዘወትር በሥራ ሰዓት ሰነድ መግዛት ይችላሉ፡፡

4. ተጫራቾች የሚወዳደሩትን ሞተር ሳይክል በተናጠል ወይም በድምር የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና የመነሻ ዋጋ 20% በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ /CPO/ ብቻ ማስያዝ አለባቸው፡፡

5. የጨረታ መወዳደሪያ ዋጋ መሙያ ጽ/ቤቱ ባዘጋጀው ፎርማት ላይ ብቻ በመሙላት ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15/አስራ አምስት/ ተከታታይ ቀናት የመወዳደሪያ ፖስታ አንድ ዋና Original እና Copy የጨረታ ሰነድ ለየብቻ በፖስታ ታሽጎና እንደገና ሁለቱም በአንድ ፖስታ ውስጥ ተካቶ በማሸግ ቢሮ ቁጥር 14 ላይ በሚገኘው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይጠበቅባቸዋል፡፡

6. ማንኛውም ተጫራች በዋጋ ማቅረቢያ ቅጽ ላይ ዋጋውን በግልጽ በአሃዝና በፊደል በመፃፍ በእያንዳንዱ በቀረበው ዋጋ ፊት ለፊት በፊርማ ማረጋገጥ አለባቸው ያልተፈረመ ሰነድ ዋጋ አይኖረውም፡፡

7. ተጫራቾች በተዘጋጀው የጨረታ ሰነድ መሠረት ከአንድ በላይ ሞተር ሳይክል መጫረት ይችላሉ፡፡

8. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በ16ኛው /አስራ ስድስተኛው/ ቀን በ4፡00 ሰዓት ላይ የጨረታ ሳጥን ታሽጎ በ4፡30 ሰዓት ላይ የሚከፈት ሲሆን ቀኑ የበዓል ወይም የዕረፍት ቀን ከሆነ በቀጣይ ቀን በተመሳሳይ ሰዓትና ቦታ የሚከፈት መሆኑን እናሳውቃለን፡፡

9. ተጫራቾች በጨረታ ያሸነፉትን ንብረት አሸናፊነታቸው በደብዳቤ በተገለጸ በ10 /አስር/ የስራ ቀናት ውስጥ ማንሳት አለባቸው ሆኖም በተጠቀሰው ቀናት ውስጥ ገዢው ካላነሳ ለሚደርሰው ለማንኛውም ችግር ሻጭተጠያቂ አይሆንም፡፡

10. ተጫራቾች ለእያንዳንዱ ተሽከርካሪ ከመንግስት የሚፈለግ ግብርና ቀረጥ በሻጭ የሚሸፈን ይሆናል።

 

11. አሸናፊው ተጫራች የሞተር ሳይከሎች ስም ማዘዋወሪያ እና ሌሎች ልዩ ልዩ ወጪዎችን በሙሉ በአሸናፊው ይሸፈናል፡፡

12. ተጫራቾች የመነሻ ዋጋ እና የዋጋ ማቅረቢያ የጨረታ ሰነድ አካል ሲሆን ከጨረታ ሰነድ ጋር የተያያዘ ነው::

13. መስሪያ ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

ለበለጠ መረጃ፡- በስልከ ቁጥር 0913609885 / 0916729418 / 0910512670 ደውሎ መጠየቅ የሚቻል መሆኑን እንገልጻለን፡፡

በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግሥት በሀዲያ ዞን የሴሞ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት

Save Tender