Tender Detail

Tender Details


በአራዳ ክፍለ ከተማ የወረዳ 9 አስተዳደር ጽ/ቤት በ2018 በጀት ዓመት በ1ኛ ዙር ጨረታ አገልግሎት የሚውሉ አላቂ የጽህፈት መሳሪያ፣ የጽዳት እቃዎች፣ የደንብ ልብስ፣ ልዩ ባህሪ ያላቸው የጓሮ አትክልት ፤የመስተንግዶ አገልግሎት፣ የመኪና ኪራይ፣ የደንብ ልብስ ስፌት፣ ህትመት፣ የጉልበት ሰራተኛ የኤሌክትሮኒክስ ጥገና፣ ቋሚ ዕቃዎች፣ የቁሳቁስና ተገጣጣሚ ጥገና በ1ኛው ዙር ግልፅ ጨረታ አወዳድረን መግዛትና ማሰራት እንፈልጋለን።

በአራዳ ክፍለ ከተማ የወረዳ 09 አስተዳዳር ፋይናንስ ጽ/ቤት


 

ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ ቁጥር- 01/2018

 

በአራዳ ክፍለ ከተማ የወረዳ 9 አስተዳደር ጽ/ቤት በ2018 በጀት ዓመት በ1ኛ ዙር ጨረታ አገልግሎት የሚውሉ አላቂ የጽህፈት መሳሪያ፣ የጽዳት እቃዎች፣ የደንብ ልብስ፣ ልዩ ባህሪ ያላቸው የጓሮ አትክልት፣ የመስተንግዶ አገልግሎት፣ የመኪና ኪራይ፣ የደንብ ልብስ ስፌት፣ ህትመት፣ የጉልበት ሰራተኛ የኤሌክትሮኒክስ ጥገና፣ ቋሚ ዕቃዎች፣ የቁሳቁስና ተገጣጣሚ ጥገና በ1ኛው ዙር ግልፅ ጨረታ አወዳድረን መግዛትና ማሰራት እንፈልጋለን።

በዚህ መሰረት በጨረታው መሳተፍ የምትፈልጉ ተጫራቾች:-

  1. በዘርፉ አግባብነት ያለው የታደሰ የንግድ ፈቃድ፣ የዘመኑን ግብር የከፈሉና የከፋይነት መለያ ቁጥር ቲን ነምበር፣ የንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት ያላቸው።
  2. የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ የሆኑና ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ።
  3. ተጫራቾች ለጨረታው የተዘጋጀውን ሰነድ የማይመለስ ብር 200 /ሁለት መቶ ብር/ በመክፈል የአራዳ ክፍለ ከተማ ወረዳ 9 ፋይናንስ ጽ/ቤት 4ኛ ፎቅ በመምጣት መውሰድ ይችላሉ፡፡
  4. በተጨማሪ ተጫራቾች ገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ሚኒስተር ባዘጋጀው የእቃና አገልግሎት አቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ መካተታቸውን መመዝገባቸውን/ የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ።
  5. በጨረታው ላይ ያወጣናቸውን እቃዎች በሙሉ ኦርጅናል እና ጥራቱን የጠበቁ ሆነው ማቅረብ የሚችሉ
  6. ተጫራቾች የጨረታ ፖስታ በሚያስገቡበት ጊዜ ለተወዳደሩበት እቃ ሳንፕል የሚያቀርቡ መሆን ይኖርባቸዋል።
  7. ተጫራቾች ያሸነፉባቸውን እቃዎችን በራሳቸው ትራንስፖርት መ/ቤቱ ድረስ ማምጣት የሚችሉ።
  8. ተጫራቾች በገዙት ሰነድ ብቻ የሚወዳደሩበትን ቫት በመጨመርና በእያንዳንዱ ገጽ ፊርማና የድርጅቱ ማህተም በማኖር በታሸገ ኤንቨሎፕ ጨረታ ከወጣ ቀን ጀምሮ ባሉት 10 / አስር/ ተከታታይ የስራ ቀናት በተጠቀሰው ቢሮ ለጨረታው በተዘጋጀ ውሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርበታል።
  9. የጨረታው ማስከበሪያ በየአንዳንዱ ሎት 5,000 /አምስት ሺህ ብር/ በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ ብቻ ማቅረብ አለባቸው።
  10. ተጫራቾች የጨረታ አሸናፊ ሆነው የተገኙባቸው እቃዎች አጠቃላይ ዋጋ 10% የውል ማስከበሪያ በማስያዝ ከጽ/ቤቱ ጋር የግዢ ውል ስምምነት መፈፀም ይኖርባቸዋል።
  11. ጨረታው ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ11ኛው ቀን የስራ ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ተዘግቶ የጨረታው አከፋፈት ላይ ለመገኘት ፍላጎት ያላቸው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በተመሳሳይ ቀን /በ11ኛው የስራ ቀን ከጠዋቱ 4፡30 ሰዓት በወረዳው አስተዳደር አዳራሽ ውስጥ ይከፈታል።
  12. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው። ተጫራቾች ለሳንፕል /ለናሙና/ ማቅረቢያ የሚያገለግላቸውን በተጫራቹ ድርጅት ቅጽ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል።

አድራሻ፡- አራት ኪሎ ዳብር ህንጻ ፊት ለፊት ብርሃንና ሰላም አለፍ ብሎ ቡና ባንከ አጠገብ አራዳ ክፍለ ከተማ ወረዳ 09 ፋይናንስ ጽ/ቤት 4ኛ ፎቅ ስልክ ቁጥር፡- 0118 68 47 83

 

በአራዳ ክፍለ ከተማ የወረዳ 09 አስተዳዳር ፋይናንስ ጽ/ቤት

 

Save Tender