በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ወረዳ 11 የፈልጶስ ቅድመ አንደኛ እና የመጀመሪያና መካከለኛ ደረጃ ት/ቤት የተለያዩ ዕቃዎች እና ተያያዥ አገልግሎቶች በጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ወረዳ 11 የፊልጶስ አፀደ ሕፃናትና የመጀመሪያ ደረጃ ት/ቤት
የጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር 01/2018
በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ወረዳ 11 የፈልጶስ ቅድመ አንደኛ እና የመጀመሪያና መካከለኛ ደረጃ ት/ቤት የተለያዩ ዕቃዎች እና ተያያዥ አገልግሎቶች በጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
- የደንብ ልብስ
- የአላቂ የፅዳት ዕቃዎች
- አላቂ የጽሕፈት ዕቃዎች
- የቋሚ ዕቃዎች
- የሠራተኛ መታወቂያና የደረት ባጅ
- የጠረጴዛ ባጅ ተንሸራታች
በዚህ መሠረት ከዚህ በታች የተጠቀሱትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ድርጅቶችና ግለሰቦች በጨረታው እንዲሳተፉ ይጋብዛል፡፡ ከላይ ከተራ ቁጥር 1-6 ለተጠቀሱት የተለያዩ ዕቃዎችና ተያያዥ አገልግሎች በዘርፉ ህጋዊ የሆነና የተጫራቹን የሥራ ዘርፍ የሚያሳይ የታደሰ የንግድ ፍቃድና የንግድ ምዝገባ ሰርተፍኬት በታክስ ባለሥልጣን የተሰጠ ወቅታዊ የታክስ ክፍያ ሰርተፍኬት እንዲሁም በገንዘብና ኢኮኖሚ ሚኒስቴር ወይም በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፋይናስና ኢኮኖሚ ልማት ቢሮ ከላይ ከ1-6 በተጠቀሰው ዘርፍ አቅራቢዎች ዝርዝር ለመመዝገባቸው የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉና ከ50,000 ብር በላይ የሚያቀርቡ ድርጅቶች (ግለሰቦች) የቫት ተመዝጋቢና ሰርተፍኬት የሚያቀርቡ መሆን አለባቸው፡፡
- በጨረታ ሂደት ምንም አይነት አድሎ አይፈፀምም፡፡
- ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ10 ተከታታይ የሥራ ቀናት ዘወትር በሥራ ሰዓት አዲስ ክፍለ ከተማ የወረዳ 11 የፊልጶስ ቅድመ አንደኛ እና የመጀመሪያና መካከለኛ ደረጃ ት/ቤት በመገኘት ብር 200 /ሁለት መቶ ብር/ በመክፈል የጨረታውን ሠነድ መግዛት ይችላል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና በየሎቱ በተጠቀሰው መሠረት ይሆናል፡፡
- የደንብ ልብስ ተጫራች በብር 2,000.00 (ሁለት ሺህ ብር)
- ለአላቂ የፅዳት ዕቃዎች ተጫራች በብር 3,000 .00 (ሶስት ሺህ ብር)
- አላቂ የጽህፈት ዕቃዎች ተጫራች በብር 5,000.00 (አምስት ሺህ ብር)
- የቋሚ ዕቃዎች ተጫራች በብር 3,000 .00 (ሶስት ሺህ) በባንክ በሚሰጥ የተረጋገጠ ሲፒኦ
ወይም በጥሬ ገንዘብ ከዋጋ ማቅረቢያ ሰነዱ ጋር በታሸገ ኤንቨሎፕ በማድረግ ጨረታው ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 10ኛ ቀን 11፡30 ሰዓት ድረስ ማቅረብ አለባቸው። ተጫራቾች እያንዳንዱን የሚሸጥበትን ነጠላ ዋጋና የጠቅላላ ዋጋ ከነቫቱ በመግለጽ በታሸገ ኤንቨሎፕ በማድረግ ሙሉ አድራሻቸውን እና የጨረታውን አይነት መግለጽ ይኖርባቸዋል፡፡
- ሁሉም ተጫራቾች ሰነዱን ሞልተው ሲያስገቡ አላቂ የቢሮ ዕቃዎች፣ የሠራተኛ የሥራ ልብሶችና የፅዳትና ሌሎች አላቂ ዕቃዎችና ናሙና የማቅረብ ግዴታ አለባቸው፡፡ ናሙና ካላቀረቡ ተቀባይነት የላቸውም፡፡
- የጨረታ ሰነድ ማስረከቢያ የመጨረሻው ቀን በ10ኛው ቀን እስከ ቀኑ 11፡30 ሰዓት የሚያበቃ ሲሆን ጨረታው በ11ኛው የሥራ ቀን ከጠዋቱ 3፡30 ሰዓት ታሽጎ 4፡30 ሰዓት ይከፈታል። ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻችው በተገኙበት በት/ቤቱ አዳራሽ ውስጥ ይሆናል፡፡
- አንድ ተጫራች ሌላው በሰጠው ዋጋ ላይ ተንተርሶ ማቅረብ አይችልም፡፡
- ጨረታው ከተዘጋ በኋላ የሚመጣ የጨረታ ሰነድ ተቀባይነት አይኖረውም፡፡
- በጥቃቅን የተደራጁ አካላት ከሆኑ ሰነድ ለመውሰድ በሚመጡበት ጊዜ ከሚመለከተው አካል ወቅታዊ የሆነ በጽ/ቤቱ ስም የጨረታ ቁጥሩንና ከላይ በተራ ቁጥር ከ1-6 በተገለጸው መሰረት የዕቃውን ወይም የአገልግሎቱን አይነት የሚገልጽ የዋስትና ደብዳቤ ማቅረብ አለባቸው፡፡ በተባለው መሰረት ካላቀረቡ የማናስተናግድ መሆኑንን ከወዲሁ እናሳውቃለን፡፡
- መሥሪያ ቤቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- ሁሉም የሚቀርቡ ሰነዶችና ሌሎች በአማርኛ የተፃፉ መሆን አለባቸው።
ለበለጠ መረጃ አዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ወረዳ 11 የፊልጶስ ቅድመ አንደኛ እና የመጀመሪያና መካከለኛ ደረጃ ት/ቤት የሙስሊም መቃበር ፊት ለፊት
ስልክ ቁጥር፡- 0112-73-86-32
በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ወረዳ 11 የፊልጶስ አፀደ ሕፃናትና የመጀመሪያ ደረጃ ት/ቤት
