የባሌ ሮቤ ፖሊ ቴክኒክ ሥልጠና ኮሌጅ ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ዕቃዎች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
የባሌ ሮቤ ፖሊ ቴክኒክ
የጨረታ ማስታወቂያ
የባሌ ሮቤ ፖሊ ቴክኒክ ሥልጠና ኮሌጅ ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ዕቃዎች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ በመሆኑም
- አላቂ የትምርት ዕቃዎችና, ቋሚ አላቂ ዕቃዎች
- ቋሚ ዕቃዎች
- የፅዳት ዕቃዎች
- የፅህፈት ዕቃዎች
- ቋሚ አላቂ ዕቃዎች
- የሠራተኛ የደንብ ልብስ እና
- አላቂ የምርት ዕቃዎች
- የመኪና ጎማ (Goma)
- የመኪና ጭነት አገልግሎት ማቅረብ የሚችል
- Infrastructure ዕቃዎችና Computer Printer, photocopy, lap Top እና የማሽን ጥገና በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ከዚህ በላይ የተጠቀሱትን ዕቃዎች ለመግዛት፤ ለማስጠገን፤ መኪና ለመከራየት ስለሚፈልግ የሚከተሉትን የጨረታ መስፈርት የሚያሟሉ ተጫራቾችን እንዲወዳደሩ ይጋብዛል።
- ዕቃዎችን በጥራት ለማቅረብ የሚያስችል ህጋዊ ንግድ ፍቃድ እና የ2018 ዓ.ም ፍቃዳቸውን ያደሱ
- ለጨረታ ማስከበሪያ ጠቅላላ ካቀረቡት ብር 50,000 (ሃምሳ ሺህ) በባንክ በተረጋገጠ (CPO) ከጨረታ ሰነድ ጋር ማቅረብ የሚችል
- ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ የሥራ ቀናት የማይመለስ ብር 400(አራት መቶ ብር) በመክፈል ሰነዱን ከሮቤ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ቢሮ ቁጥር 3 የዕቃ አቅርቦትና ፋይናንስ አስተዳደር የሥራ ሂደት ቀርበው መግዛት ይችላሉ።
- ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ ዋናውን እና ፎቶ ኮፒውን በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- የጨረታ ማስታወቂያው ከወጣበት በ16ኛው የስራ ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ለጨረታው በተዘጋጀው ሳጥን ገብቶ በዚሁ ቀን በ4፡30 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል::
- አሸናፊዎች ያሸነፉባቸውን ዕቃዎች ሙሉ በሙሉ በባሌ ሮቤ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ንብረት ክፍል ገቢ ማድረግ እና የማስጫኛና የማውረጃ ወጪዎችን ተጫራቾች ይሸፍናሉ፡፡ እቃውን በተጠየቀው ስፔስፊኬሽን ካላቀረበ ኪሳራው የአቅራቢው ድርጅት ነው:: ኮሌጁ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
- ተጫራቾች የቫት ተመዝጋቢ መሆን አለባቸው
ማሳሰቢያ፦ ተጫራቾች ዕቃዎችን በተባለው ጊዜ ውስጥ አጠናቆ ማቅረብ እና ሰነድ ከቫት በፊት መሞላት ይኖርበታል።
ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 022 665 1505/ 09 39 81 7640
የባሌ ሮቤ ፓሊ ቴክኒክ ሥልጠና ኮሌጅ
