ጎሮ ቅድመ አንደኛ ፤ አንደኛና እና መካከለኛ ደረጃ ት/ቤት ከዚህ በታች ለተዘረዘሩት ዕቃዎች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ
የግልፅ ጨረታ መለያ ቁጥር 001/2018/ዓ.ም
ከዚህ በታች ለተዘረዘሩት ሎት 1. የደንብ ልብስ፤ ሎት 2. አላቂ የቢሮ እቃዎች ፤ ሎት 3. አላቂ የትምህርት እቃዎች፤ ሎት 4. አላቂ የፅዳት እቃዎች ፤ ሎት 5 የልዩ ልዩ መሳሪያዎች ፤ ሎት 6. የህንፃ ቁሳቁስና ለተገጣጣሚ ዕቃዎች፤ ሎት 7. ቋሚ እቃዎች እና ኤሌክትሮኒክስ ፤ ሎት 8. የህንፃ ቁሳቁስና ለተገጣጣሚ ዕቃዎች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡ በዚህ መሰረት በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ህጋዊ ተጫራቾች የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ መሆን አለባቸው።
- ተጫራቾች በዘርፉ የተሰማሩበትን ህጋዊ ፈቃድ ያላቸውና የዘመኑን ግብር ለመክፈላቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- በገንዘብና የኢኮኖሚ ልማት ሚ/ር በአቅራቢነት የተመዘገቡና ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ
- የታደሰ የንግድ ፍቃድ ያለው።
- የተጨማሪ እሴት ታከስ የምዝገባ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ ፡፡
- ተጫራቾች ከዚህ በታች የተጠቀሰውን የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ የተረጋገጠ ኦርጂናል የባንክ ሲፒኦ/ ማቅረብ አለባቸው። ሎት1. የደንብ ልብስ ብር 52,000 (ሃምሳ ሁለት ሺህ ብር) ፤ ሎት2. አላቂ የቢሮ እቃዎች ብር 52,000 (ሃምሳ ሁለት ሺህ ብር) ፤ ሎት3. አላቂ የትምህርት እቃዎች ብር 52,000 (ሃምሳ ሁለት ሺህ ብር) ፤ ሎት 4. አላቂ የፅዳት እቃዎች ብር 60,000 (ስልሳ ሺህ ብር)፤ ሎት 5. የልዩ ልዩ መሳሪያዎች ብር 30,000 (ሰላሳ ሺህ ብር)፤ ሎት 6. የህንፃ ቁሳቁሶችና ለተገጣጣሚ ዕቃዎች 22,500 (ሃያ ሁለት ሺህ አምስት መቶ ብር )፤ ሎት 7. ቋሚ እቃዎች እና ኤሌክትሮኒክስ ብር 195,000 (አንድ መቶ ዘጠና አምስት ሺህ ብር)፤ ሎት 8. የህንፃ ቁሳቁስና ለተገጣጣሚ ዕቃዎች ብር 90,000 (ዘጠና ሺህ ብር)
- የጨረታ ሰነዱን ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ የማይመለስ ብር 500 (አምስት መቶ ብር) በመክፈል የተዘጋጀውን ሰነድ ከት/ቤት ቢሮ ቁጥር 3 እየቀረቡ መግዛት ይችላሉ ፡፡
- ተጫራቾች ጨረታ ከወጣበት ቀን አንስቶ ባሉት 10 (አስር) ተከታታይ የስራ ቀናት ጎሮ ቅድመ አንደኛ ፤አንደኛ እና መካከለኛ ደረጃ ት/ቤት ቢሮ ቁጥር 5 ድረስ በመምጣት ዋጋው የተሞላበት የጨረታ ሰነዱን ዋናውንና ፎቶ ኮፒ ለየብቻ በማሸግ ለዚህ በተዘጋጀውን የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው።
- ጨረታው በ11ኛው (በአስራ አንደኛው) ቀን 4፡00 ሰዓት ታሽጎ በዕለቱ 4፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡ የጨረታው መዝጊያና መክፈቻ ቀን የሥራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን በተጠቀሰው ተመሳሳይ ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡
- ተጫራቾች ጨረታው ከመከፈቱ በፊት ለሚወዳደሩበት ናሙና ለሚቀርብባቸው ዕቃዎች ናሙና ማቅረብ አለባቸው። ናሙናም ሲያቀርቡ በእያንዳንዱ ዕቃ ላይ የድርጅታቸውን ማህተም እና ሙሉ አድራሻ በመለጠፍ ማቅረብ ይኖርባቸዋል ናሙና የማይቀርብባቸው ቋሚ ዕቃዎች መሥሪያ ቤቱ ባቀረበው ስፔስፊኬሽን መሠረት ማቅረብ አለባቸው።
- የጨረታው አሸናፊ ድርጅት ያሸነፈበትን ዕቃ በራሱ ትራንስፖርት ት/ቤት ድረስ ማቅረብ ይኖርበታል፡፡
- አሸናፊ ድርጅት ያሸነፈበትን ዋጋ 10% የውል ማስከበሪያ ማስያዝ ይኖርበታል።
- ለጥቃቅንና አነስተኛ ተጫራቾች ባመረቱት ምርት ብቻ መወዳደር ይችላሉ ነገር ግን ባላመርቱት ምርት ከሆነ እንደማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሰነድ ገዝተው እንዲሁም ሲፒኦ አስይዘው መወዳደር ይችላሉ፡፡ የዋስትና ደብዳቤ ተቀባይነት የለውም ፡፡
- ት/ቤት የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው።
አድራሻ፡- ጎሮ ቅድመ አንደኛ ፤አንደኛ እና መካከለኛ ደረጃ ት/ቤት ወደ ፊጋ በሚወስደው መንገድ 100 ሜትር እንደሄዱ
ጎሮ ቅድመ አንደኛ ፤ አንደኛና እና መካከለኛ ደረጃ ት/ቤት
