Tender Detail

Tender Details


በባሌ ዞን ሮቤ ከተማ የዜይበላ ወለሼ ክፍለ ከተማ ገንዘብ ጽ/ቤት በ2018 በጀት በሥሩ ላሉት ሴክተር መ/ቤቶች የሚያገለግሉ የጽሕፈት መሳሪያዎች ቋሚና አላቂ እቃዎች፣ የፅዳት እቃዎች፣ የተለያዩ የኤሌክትሮኒክስ እቃዎች፣ ፈርኒቸሮች፣ የመኪና ጎማዎች፣ የሕንጻ መሳሪያዎች፣ የደንብ ልብሶች፣ የህትመት እና የተሽከርካሪዎች ጥገና ሥራዎች እንዲሁም፣ የምግብ አገልግሎቶች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡

በባሌ ዞን ሮቤ ከተማ የዘይበላ ወለሼ/ክ/ከ/ገ/ጽ/ቤት


 

ግልጽ የግዢ ጨረታ ማስታወቂያ

 

በባሌ ዞን ሮቤ ከተማ የዜይበላ ወለሼ ክፍለ ከተማ ገንዘብ ጽ/ቤት በ2018 በጀት በሥሩ ላሉት ሴክተር መ/ቤቶች የሚያገለግሉ የጽሕፈት መሳሪያዎች ቋሚና አላቂ እቃዎች፣ የፅዳት እቃዎች፣ የተለያዩ የኤሌክትሮኒክስ እቃዎች፣ ፈርኒቸሮች፣ የመኪና ጎማዎች፣ የሕንጻ መሳሪያዎች፣ የደንብ ልብሶች፣ የህትመት እና የተሽከርካሪዎች ጥገና ሥራዎች እንዲሁም፣ የምግብ አገልግሎቶች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ በመሆኑም ከዚህ በታች የተገለጹትን መመሪያዎች የምታሟሉ ተጫራቾች መጫረት ትችላላችሁ፡

  1. በጨረታው ለመካፈል የሚያስችል በሚወዳደሩበት የንግድ ዘርፍ የተሰማሩበት ወይም ተጓዳኝ ሕጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው የዘመኑን ግብር ከፍለው ያሳደሱና ክሊራንስ እንዲሁም በአቅራቢነት የተመዘገቡበትን ማስረጃ የሚያቀርቡ መሆን ይኖርባቸዋል።
  2. የተጨማሪ እሴት ታክስ ወይም ቫት ተመዝጋቢ የሆኑበትን ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ መሆን ይኖርባቸዋል፡፡
  3. ተጫራቾች ለጨረታው ማስከበሪያ የሚውል ከታወቀ መንግሥታዊ ባንክ ብር 50,000 (ሀምሳ ሺህ) በCPO ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
  4. ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ መግዣ በሮቤ ከተማ ዜይበላ ወለሼ ክፍለ ከተማ ገቢዎች ባለሥልጣን ጽ/ቤት ብር 500 (አምስት መቶ ብር) በመክፈል ሰነዱን ከሮቤ ከተማ ዜይበላ ወለሼ ክፍለ ከተማ ገንዘብ ጽ/ቤት መውሰድ ትችላላችሁ።
  5. በኢትዮጵያ ደረጃዎች ኤጀንሲ መስፈርት መሰረት እውቅና የተሰጣቸውን እቃዎች የሚያቀርብ መሆን ይኖርበታል፡፡
  6. ፈርኒቸሮች፣ ኤሌክትሮኒክሶች፣ የኮምፒተር ቀለሞች፣ ቦርሳዎች፣ ጨረታው ከመከፈቱ አንድ ቀን በፊት አስቀድሞ ውሉ ተፈጽሞ እቃው ገቢ እስከሚሆን ድረስ በመስሪያ ቤቱ ውስጥ የሚቆይ ናሙና በፎቶግራፍ የተደገፈ ማቅረብ አለበት፡፡
  7. ለሠራተኞች ደንብ ልብስ የሚሆኑ ብትን ጨርቆች የተዘጋጁ ልብሶችና የተለያዩ ቆዳ ጫማዎች ለከፋይ ምንጣፍና ለጨርቅ መጋረጃ እና ቀለሞች ናሙናዎች በሙሉ ለብቻ በፖስታ አሽገው ጨረታው ከመከፈቱ አንድ ቀን በፊት አስቀድሞ ውሉ ተፈጽሞ እቃው ገቢ እስከሚሆን ድረስ በመስሪያ ቤቱ ውስጥ የሚቆይ ናሙና እቃውን ማቅረብ አለባቸው፡፡
  8. በሰነዶቻቸው ላይ ስማቸውንና ሙሉ አድራሻቸውን በትክክል ጽፈው በመፈረም እና የድርጅታቸውን ማህተም ማድረግ አለባቸው።
  9. የሚቀርበው ሰነድ ስርዝ ድልዝ የሌለው ሆኖ በጉልህ መጻፍ አለበት፡፡
  10. በተገለጹት የእቃ ዝርዝሮች አጠገብ በተቀመጡት ባዶ ቦታዎች ላይ የእቃዎችን ብራንድና ሞዴል በመሙላት መወዳደር ይኖርባቸዋል፡፡
  11. በሚጫረቱት ሰነድ ላይ ከተገለጸው ስፔስፍኬሽን ውጪ በመሰረዝና በመደለዝ የራስን ስፔስፍኬሽን መጨመር አይቻልም፡፡ አማራጭ ካላቸው ግን የሚወዳደሩበትን የእቃ አይነት በመጥቀስ ለብቻ በሌላ ወረቀት ማያያዝ ይችላሉ።
  12. ለሁሉም እቃዎች ቴክኒካል እና ፋይናንሻል ሰነዶችን በተለያዩ ፖስታዎች አሽገው ማቅረብ አለባቸው።
  13. ማንኛውም ተጫራቶች ጨረታው ከተከፈተ በኋላ በጨረታው ሰነድ ላይ የተገለጹትን ማንኛውንም ሁኔታዎች መለወጥ ወይም ማሻሻል ወይም ጨረታውን ትቻለሁ ማለት አይቻልም፡፡
  14. አቅራቢው ድርጅት ያሸነፈባቸውን እቃዎች ማንኛውንም ወጪ በመቻል መስሪያቤቱ ንብረት ክፍል ድረስ በማምጣት ገቢ ማድረግ ይኖርበታል፡፡
  15. ከዚህ በላይ በተገለጸው መሰረት ተጫራቾች የጨረታውን ግዴታ ባይወጡ ወይም ውሉን በአግባቡ ሳይፈጽሙ ቢቀሩ ለውሉ ማስከበሪያ በዋስትና የተያዘው ገንዘብ ለመንግስት ገቢ ይሆናል፡፡
  16. የሚገዙ እቃዎች በተሰጠው ስፔስፍኬሽን መሰረት ተሟልተው ካልቀረቡና ኦሪጂናል ካልሆኑ ለሚፈጠረው ማንኛውም ችግር ኃላፊነቱ የአቅራቢው ድርጅት ይሆናል፡፡
  17. ጨረታው ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን አንስቶ ለ15 የሥራ ቀናት ክፍት ሆኖ በ16 ኛው ቀን የሚከፈት ሲሆን ጸንቶ የሚቆይበት ጊዜ በግዢ መመሪያ መሰረት የሚወሰን ይሆናል፡፡
  18. ቢሮው የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  19. ለተጨማሪ ማብራሪያ በስልክ ቁጥር 0913091660/0966667176 ደውለው ይጠይቁ፡፡

 

በባሌ ዞን ሮቤ ከተማ የዘይበላ ወለሼ/ክ/ከ/ገ/ጽ/ቤት

 

Save Tender