የኦሮሚያ ህብረት ሥራ ባንክ ከዚህ በታች የሚገኙትን ንብረቶችን ባሉበት ሁኔታ ሙሉ በሙሉ በጥሬ ገንዘብ በጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡
የጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር FA- 03/2025/26
የኦሮሚያ ህብረት ሥራ ባንክ ከዚህ በታች የሚገኙትን ንብረቶችን ባሉበት ሁኔታ ሙሉ በሙሉ በጥሬ ገንዘብ በጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡
|
ተ.ቁ |
የንብረቱ ዓይነት |
ንብረቱ የሚገኝበት አድራሻ |
የካርታ ቁጥር |
የቦታው ስፋት |
የመጨረሻ መነሻ ዋጋ |
||
|
ክልል |
ክ/ከተማ |
ወረዳ |
|||||
|
1 |
የመኖሪያ ቤት በባንኩ ስም የሚታወቅ |
አ/አ |
አቃቂ ቃሊቲ |
07 |
AA000070702200 |
500ካ.ሜ |
25,000,000.00 |
|
2 |
የከብት ማድለቢያ በሞገስ አሰፋ ስም የሚታወቅ |
ኦሮሚያ |
ምስራቅ ሸዋ |
ሎሜ በኩርማ ፋቶሊ |
BLEII/21-958/654 |
2 ሄክታር |
15,206,762.71 |
ስለዚህ ለመግዛት ለሚፈልጉ ተጫራቾች የሚከተሉትን መመሪያዎች መከተል ይኖርባቸዋል:
1. የንብረቶቹን ዝርዝር ሁኔታ ለማየት የሚፈልጉ ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ጊዜ ጀምሮ ከነሐሴ 18 ቀን 2017 ዓ.ም 5 እስከ ጳጉሜ 4 ቀን 2017 ዓ.ም 8፡00 ስዓት ድረስ የግብር ክፋይ ምዝገባ ሰርተፊኬት ወይም የግብር መለያ ቁጥር(TIN) ያላችሁ ተጫራቾች ቦሌ መንገድ የኦሮሚያ ህብረት ሥራ ባንክ ኢጃ ቅርንጫፍ ወይም በአቅራቢያዎ በሚገኝ የባንኩ ቅርንጫፍ በመሄድ የጨረታ ሰነድ መግዣ ብር 200.00 (ሁለት መቶ) በሂሳብ ቁጥር ETB1446500010001 በማስገባት ደረሰኙን በመያዝ የጨረታ ሰነዱን ቦሌ መንገድ ከአፍሪካ ኢንሹራንስ ፊትለፊት፣ ራንግ ህንጻ 7ኛ ፎቅ ከባንኩ ንብረት አስተዳደር ዋና ክፍል በመውሰድ መጎብኘት ይችላሉ።
2. ገዢዎች የሚገዙበትን ዋጋ በታሸገ ኤንቬሎፕ እስከ ጨረታ መዝጊያ ጳጉሜ 04 ቀን 2017 ዓ.ም 8፡00 ሰዓት ድረስ ቦሌ መንገድ ራንግ ህንጻ ንብረት አስተዳደር ዋና ክፍል በአካል ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸውን በመላክ ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሣጥን ውስጥ በማስገባት መጫረት ይችላሉ፡፡
3. ተጫራቾች የሚጫረቱበትን ንብረት የጨረታ መነሻ ዋጋ 25 % (ሃያ አምስት በመቶ)ዉን በባንክ ክፍያ ማዘዣ (CPO) የጨረታ ማስከበሪያ ማስያዝ ይኖርባቸዋል!
4. ተጫራቾች ለከብት ማድለቢያው የሚጫረቱበትን ዋጋ ተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) 15% በተጨማሪነት እንደሚከፍሉ ማወቅ አለባቸው ስለዚህ ዋጋ የሚያስገቡበት ሰነድ ላይ ተጨማሪ እሴት ታክስ 15% መኖርአለመኖሩን በግልዕ በሰነዱ ላይ በፅሁፍ መግለፅ ይኖርባችዋል::
5. የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ሳይያያዝ የሚቀርብ የጨረታ ስነድ ተቀባይነት የለውም።
6. አሸናፊ መሆናቸው የተገለፀላቸው ተጫራቾች ያሸነፉትን ንብረት ሙሉ ክፍያውን በአምስት ቀናት ውስጥ ከፍለው ከባንኩ ጋር የሽያጭ ውል ስምምነት መፈጸም እና ከንብረቱ ጋር ተያይዞ ያለውን ሰነድ መረከብ ይኖርባቸዋል፤ ንብረቱን ባንኩ በውስጡ የሚገኙትን የተለያዩ ዓይነት ንብረቶች አውጥቶ በአንድ ወር ጊዜ ውስጥ የሚያስረክብ ይሆናል፡፡
7. ጨረታው ማክሰኞ ጳጉሜ 04 ቀን 2017 ዓ.ም በ 8፡00 ሰዓት ላይ ተዘግቶ በዛው ዕለት ማክሰኞ ጳጉሜ 04 ቀን 2017 ዓ.ም ከቀኑ 8፡30 ሰዓት ላይራንግ ህንጻ 7ኛ ፎቅ የስብሰባ አዳራሽ ውስጥ ተጫራቾች በተገኙበት የጨረታ ሰነዱ የሚከፈት መሆኑን እንገልፃለን።
8. ባንኩ የተሸለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
የኦሮሚያ ኅብረት ሥራ ባንክ (አ.ማ)
ስልክ ቁጥር 0115576174 ፖ.ሣ.ቁ 16936
ማህበረሰቡን ማጎልበት፣ ህይወትን መለወጥ!
