በም/ሸዋ ዞን የኖኖ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ለ2018 ሙሉ በጀት በወረዳ ደረጃ ለሚገኙት የመንግሥት መ/ቤቶች አገልግሎት የሚውል የተለያዩ አላቂ የጽሕፈት መሣሪያዎችን፤ የተለያዩ አላቂ የጽዳት ዕቃዎችን፣ ቋሚ የቢሮ ዕቃዎችን፣ የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎችን፣ ሞተር ሣይክል፤ የደንብ አልባሳትን፣ የመኪና እና የሞተር ሳይክል ጉማዎችን እና ከመነዳሪዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
በም/ሸዋ ዞን የኖኖ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት
የጨረታ ማስታወቂያ
በም/ሸዋ ዞን የኖኖ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ለ2018 ሙሉ በጀት በወረዳ ደረጃ ለሚገኙት የመንግሥት መ/ቤቶች አገልግሎት የሚውል የተለያዩ አላቂ የጽሕፈት መሣሪያዎችን፤ የተለያዩ አላቂ የጽዳት ዕቃዎችን፣ ቋሚ የቢሮ ዕቃዎችን፣ የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎችን፣ ሞተር ሣይክል፤ የደንብ አልባሳትን፣ የመኪና እና የሞተር ሳይክል ጉማዎችን እና ከመነዳሪዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
ስለሆነም ይህ ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ስለ ዕቃዎቹ የሚገልጽ ሰነድ/ዶክመንት ለእያንዳንዱ የጨረታ ሰነዶች የማይመለስ ብር 200 (ሁለት መቶ ብር) ብቻ በመክፈል ዘወትር በስራ ሰዓት ም/ሸዋ ዞን የኖኖ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ግዥ ቢሮ ቁጥር 8 ድረስ በመምጣት የጨረታ ሰነዱን መግዛት ይችላሉ፡፡
የተጫራች ግዴታዎች
- ከግዥው ጋር ተያያዥነት ያለውን የታደሰ የንግድ ፍቃድ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡ በዚህም የሚጠበቅባቸውን የመንግስት ግብር ስለመክፈላቸው የሚገልጽ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡-
- በአቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ የተመዘገቡ፤ ሕጋዊ የአቅራቢዎች ምዝገባ ፈቃድ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ
- የተጨማሪ እሴት ታክስ ወይም ቫት ተመዝጋቢ ስለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ ና የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (TIN) ያላቸው።
- ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ የሚውል ከጠቅላላ ዋጋ 2% በባንክ የተመሰከረ ሲፒኦ በኖኖ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ስም ማስያዝ የሚችሉ እንዲሁም ያሸነፉበትን ዕቃዎች ገቢ ለድርጅቱ ሳያደርጉ በፊት የዕቃዎቹን ናሙና ውሉን በወሰዱ 05 ቀን ውስጥ ገቢ ማድረግ የሚችሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ዋጋ በመሙላት ኦርጅናል እና ኮፒ ለብቻ በታሽገ ኤንቨሎፕ በማሸግ ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- አሸናፊ ተጫራቾች ለመልካም ስራ አፈጻጸም የሚውል ወይም የውል ማስከበሪያ ከጠቅላላው አቅርቦት 10% በሲፒኦ ማቅረብ የሚችሉ እና ተጫራቾች አሸናፊነታቸው በተገለጸላቸዉ በ5 ተከታታይ ቀናት ውስጥ በኖኖ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ቀርበው ውል መፈጸም ይጠበቅባቸዋል።
- አሸናፊ ድርጅት ባሸነፋቸው ዕቃዎች ያሸነፉበትን ዋጋ ከጨረታው በኋላ ሳይጨምር ወይም ሳይቀንስ እስከ ሁለት (2) ወር መቆየት ይኖርበታል፡፡
- ዕቃውን እስከ ወረዳው ጽ/ቤት ድረስ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- ከአቅራቢዎች ስም ዝርዝር ውስጥ በተለያዩ ጥፋቶች ያልተሰረዙ ወይም የቅጣት ጊዜያቸው ያልተጠናቀቀ በዚህ ጨረታ መሳተፍ አይችሉም፡፡
- ተጫራቾች ከነሐሴ 16/12/2017 ጀምሮ እስከ መስከረም 5/1/2018 ድረስ ከላይ በተጠቀሰው አድራሻ ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሣጥን ውስጥ ማስገባት ይችላሉ፡፡ ጨረታው 15 የሥራ ቀናት ቆይቶ በዚያው ቀን ይከፈታል፡፡ ጨረታ መክፈቻ ቀኑ ቅዳሜና እሁድ ወይም በዓል ላይ ከዋለ በቀጣዩ የሥራ ቀን ይከፈታል። በዚህ ቀን 3:00 ሰዓት ተዘግቶ በዚሁ ዕለት 3:30 ላይ ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ኖኖ ወረዳ ግቢ ውስጥ የሚከፈት ሆኖ ተጫራቾች በጨረታው መክፈቻ ሥነ-ሥርዓት ባይገኙ የጨረታውን ሂደት እያስተኋጉልም፡፡
- ጽ/ቤቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ማሳሰቢያ፡- ኖኖ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ከአዲስ አበባ 214 ኪ.ሜ ላይ የምትገኝ ሲሆን፤ በወልቂጤ መንገድ 216 ኪ.ሜ. ርቀት ላይ ትገኛለች፡፡
ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር፡- 0912836006/ 0910154327 ደውለው መጠየቅ ይቻላል።
የኖኖ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት
ስልክ-አምባ
