Tender Detail

Tender Details


በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የለሚኩራ ከ/ከተማ ወረዳ 09 ጎሮ ጤና ጣቢያ ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ሎት1. ጽዳት እቃዎች፣ ሎት 2 ህትመት እና ባነር ሥራዎች፣ ሎት 3 ደንብ ልብስ ፣ ሎት 4 ለጭነት አገልግሎት የሚሆን ደብል ጋቢና ቢክ የአገልግሎት ዘመኑ ቅርብ የሆነ አፕ፣ ሎት 5 ቋሚና አላቂ እቃዎች ፣ ሎት 6. ስቴሽነሪ እቃዎች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የለሚ ኩራ ክ/ከተማ ወረዳ 9 ጎሮ ጤና ጣቢያ


 

የግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ

የግዥ ጨረታ መለያ ቁጥር 01/2018

 

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የለሚኩራ ከ/ከተማ ወረዳ 09 ጎሮ ጤና ጣቢያ ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ሎት1. ጽዳት እቃዎች፣ ሎት 2 ህትመት እና ባነር ሥራዎች፣ ሎት 3 ደንብ ልብስ ፣ ሎት 4 ለጭነት አገልግሎት የሚሆን ደብል ጋቢና ቢክ የአገልግሎት ዘመኑ ቅርብ የሆነ አፕ፣ ሎት 5 ቋሚና አላቂ እቃዎች ፣ ሎት 6. ስቴሽነሪ እቃዎች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡ በዚህ መሰረት ጨረታውን ለመሳተፍ የሚፈልጉ ሕጋዊ ተጫራቾች የሚከተሉትን የሚያሟሉ መሆን አለባቸው፡፡

  1. የጨረታ ሰነዱ ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ በየሎቱ የማይመለስ ብር 200.00 /ሁለት መቶ ብር/ በመክፈል የተዘጋጀውን ሰነድ ከተቋሙ ቢሮ ቁጥር 403 እየቀረቡ መግዛት ይቻላል፡፡
  2. ተጫራቾች በዘርፉ የተሰማሩበት ሕጋዊ ፈቃድ ያላቸው እና የዘመኑን ግብር ለመክፈላቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ

 

ሎት

ሎት ዝርዝር

የተጠቀሰው የጨረታ ማስከበሪያ

1

የጽዳት እቃዎች ሎት

6000

2

ህትመት እና የባነር ሥራዎች ሎት

6000

3

ደንብ ልብስ ሎት

6000

4

ለጭነት አገልግሎት የሚሆን ደብል ጋቢና ቢክ አፕ ሎት

10000

5

ቋሚ አላቂ ሎት

7000

6

ስቴሽነሪ እቃዎች በግልፅ ጨረታ

6000

7

ኦክስጂን አቅራቢ

6000

 

  1. በገንዘብና ኢኮኖሚ ሚኒስቴር በአቅራቢነት የተመዘገቡ እና ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ
  2. የታደሰ ንግድ ፍቃድ ያለው
  3. የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ የምስከር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ
  4. ተጫራቾች ጨረታው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ የሥራ ቀናት ቢሮ ቁጥር 403 በመምጣት ዋጋው የተሞላበትን የጨረታ ሰነድ ዋናውንና ፎቶ ኮፒውን ለየብቻው በማስገባት ለዚሁ በተዘጋጀው ጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው።
  5. ጨረታው በአስረኛው ቀን 11፡00 ሰዓት ታሽጎ በቀጣዩ የሥራ ቀን 4፡00 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡ የጨረታው መዝጊያ መክፈቻ የሥራ ቀን ካልሆነ በቀጣዩ የሥራ ቀን በተጠቀሰው ተመሳሳይ ሰዓት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡
  6. ተጫራቾች ያሸነፉበትን ዋጋ የውል ማስከበሪያ 10% ሲፒኦ ማስያዝ አለባቸው፡፡
  7. ተጫራቾች ጨረታው ከመክፈቱ በፊት ለሚወዳደሩባቸው እቃዎች ናሙና ማቅረብ አለባቸው። ማሳሰቢያ ናሙና የማያቀርቡባቸው ዕቃዎች ውድቅ ይሆናሉ፡፡
  8. የጨረታው አሸናፊ ድርጅት ያሸነፈበትን እቃ በራሱ ትራንስፖርት እስከ መስሪያ ቤቱ መጋዘን ድረስ ማቅረብ ይኖርበታል፡፡
  9. መስሪያ ቤቱ ለጨረታው ለቀረው እቃ እስከ 20% የመጨመርም ሆነ መቀነስ መብቱ የተጠበቀ ነው።
  10. መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
  11. ተጫራቾች የሚያቀርቡት ዋጋ ተጨማሪ እሴት ታክስ ያካተተ መሆን አለበት፡፡
  12. ጥቃቅንና አነስተኛ ተጫራቾች በሚያመርቱት ምርት ካልሆነ በስተቀር የጨረታ ሰነድ መግዛትና የጨረታ ማስከበሪያ ሲፒኦ ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
  13. የጨረታ ማስከበሪያ ሲፒኦ ብቻ በየሎቱ ለተጠቀሰው ገንዘብ መጠን ማስያዝ አለባቸው።

አድራሻ፡- ጎሮ ቅዱስ ሚካኤል ቤተክርስቲያን ፊት ለፊት ያለው ሕንፃ

 

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የለሚ ኩራ ክ/ከተማ ወረዳ 9 ጎሮ ጤና ጣቢያ

 

Save Tender