የኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት በምዕ/ሐረርጌ ዞን በቦኬ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ለወረዳው የተለያዩ መ/ቤቶች የሚውል አላቂና ቋሚ የቢሮ እቃዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
በኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት በምዕ/ሐረርጌ ዞን የቦኬ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት
የግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር 2/08/WM/2018
የኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት በምዕ/ሐረርጌ ዞን በቦኬ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ለወረዳው የተለያዩ መ/ቤቶች የሚውል አላቂና ቋሚ የቢሮ እቃዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል ስለዚህ የሚከተለውን መስፈርት የሚያሟሉ ተጫራቾች በጨረታው እንዲሳተፉ ይጋብዛል።
- ተጫራቾች በዘርፉ የታደሰ ህጋዊ ንግድ ፍቃድ፣ የዋና ምዝገባ ምስክር ወረቀት፤ የግብረ ከፋይነት መለያ ቁጥር፣ የዘመኑን ግብር የከፈሉና የተጨማሪ እሴት ታክስ ሰርተፊኬት ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች በአቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚገልጽ ህጋዊ ማስረጃ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
- ተጫራቾች ተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) ተመዝጋቢ የሆኑና ለዚሁም ማስረጃ የሚያቀርቡ መሆን አለባቸው።
- የጨረታ ማስከበሪያ ብር 20,000 (ሃያ ሺህ ብር ብቻ) በባንክ በተረጋገጠ (CPO)ጨረታው ከመከፈቱ በፊት ማስያዝ ይኖርባቸዋል።
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን በማይመለስ ብር 200 (ሁለት መቶ ብር) በቦኬ ወረዳ ገቢዎች ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 1 በመቅረብ ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በመንግስት መ/ቤት የሥራ ሰዓት መግዛት ይችላሉ።
- ማንኛውም ተጫራቾች ጨረታው ከተከፈተ በኋላ በጨረታው ሰነድ ላይ የተገለፁትን ማንኛውም ሁኔታዎች መለወጥ ወይም ማሻሻል ወይም ጨረታውን ትቻለሁ ማለት አይችልም፡፡
- ጨረታው ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ዕለት ጀምሮ እሰከ 09/1/2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 8፡00 ሰዓት ድረስ ለተጫራቾች ክፍት ይሆናል።
- ተጫራቾች የጨረታ ሠነዱን የሚጫረቱበትን መወዳደሪያ የአንዱን ዋጋ በመጥቀስ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ ውስጥ አድርገው እስከ 09/1/2018 ዓ.ም 8፡00 ሰዓት በቦኬ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ቢሮ ቁ 2 ለዚሁ ተብሎ የተዘጋጀው ሳጥን ማስገባት ይችላሉ፤ ጨረታው በዚሁ እለት ከረፋዱ 8፡00 ሰዓት ተዘግቶ ከረፋዱ 8:30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል።
- አሸናፊ ድርጅት /ተጫራቹ/ ያሸነፈበትን ዕቃዎች በራሱ ትራንስፖርት እስከ ቦኬ ወረዳ ገ/ኢ/ት/ጽ/ቤት ዕቃ ግምጃ ቤት ድረስ ማቅረብ ይኖርበታል።
- ተጫራቾች የተፈለገውን ዕቃ ጥራትና ብዛት አሟልቶ የማቅረብ ግዴታ አለባቸው።
- በሽያጭ የቀረበው ዕቃ ጥራቱን ያልጠበቀ ከሆነ ነጋዴው /አሸናፊ ድርጅቱ/ በራሱ ወጪ ዕቃውን የመለወጥ ወይም ገንዘቡን የመመለስ ግዴታ አለበት፡፡
- የዕቃውን ማስጫኛና የማውረጃ ወጪ በተጫራቹ ይሸፈናል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነድ ኦርጅናልና ኮፒ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ ውስጥ አድርገው መቅረብ ይኖርባቸዋል።
- ጽ/ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
አድራሻችን፡- በቦኬወረዳ ገ/ጽ/ቤት
ቦኬ ጢቆ
ሞባይል - 09-21-66-18-39 / 09-11-36-98 61
በኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት በምዕ/ሐረርጌ ዞን የቦኬ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት
