Tender Detail

Tender Details


በምዕ/ወለጋ ዞን የጉሊሶ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት በወረዳችን ውስጥ ለሚገኙት መንግሥታዊ መ/ቤቶች የተለያዩ ዕቃዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡

በምዕራብ ወለጋ ዞን የጉሊሶ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት


 

የጨረታ ማስታወቂያ

 

በምዕ/ወለጋ ዞን የጉሊሶ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት በወረዳችን ውስጥ ለሚገኙት መንግሥታዊ መ/ቤቶች የተለያዩ ዕቃዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡

ስለዚህ ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ዕቃዎች፡-

  1. የጽህፈት እና የንጽህና መሳሪያዎች፣
  2. የቢሮ ዕቃዎች፣
  3. የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች፣
  4. የደንብ ልብሶች፣
  5. የግንባታ ዕቃዎች፣
  6. ሞተር ብስክሌቶች ለመግዛት ይፈልጋል፡፡

የዕቃውን ዓይነትና ዝርዘር ጉሊሶ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 11 በመቅረብ ለእያንዳንዱ ሰነድ የማይመለስ ብር 1000 (አንድ ሺህ) ከፈለው መውሰድ የሚችሉ መሆኑን እናሳውቃለን፡፡

ክሬተሪያዎች /መስፈርቶች/

  1. የንግድ ፍቃድ ያላቸው፣
  2. የንግድ ፍቃዳቸውን የ2018 ያሳደሱ፣
  3. ቫት ተመዝጋቢ የሆነ፣
  4. የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር (ቲን) ቁጥር ያላቸው፣
  5. ያሸነፉበትን ዕቃ እስከ ጉሊሶ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ድረስ ማምጣትና ፋርኒቸር ዕቃዎችን በራሱ ወጪ ማገጣጠም የሚችል፣
  6. የአቅራቢነት ማረጋገጫ ከሚመለከተው አካል ማቅረብ የሚችል፣
  7. የሚያቀርቡት ዕቃ ናሙናውን በቅድሚያ ማቅረብ የሚችል፣
  8. የጨረታ ማስከበሪያ ቢድ ቦንድ (ሲፒኦ) ለእያንዳንዱ ሰነድ 25,000 (ሃያ አምስት ሺህ ብር ብቻ) ማስያዝ የሚችል፣ የምዝገባ ቀን 15/12/2017 እስከ 5/13/2017 ጨረታው የሚዘጋበት ቀን 5/13/2017 ዓ.ም ከቀኑ 11፡00 ሰዓት ይዘጋል፡፡ ጨረታው በ5/1/2018 ዓ.ም 4:00 ሰዓት ተወዳዳሪዎች ወይም ተወካዮቻቸው ባሉበት ቦታ ይከፈታል፡፡

ማሳሰቢያ መሥሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብት አለው፡፡

ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር፡- 0913370397/0921055274/0921644787 ደውለው መጠየቅ ይቻላል፡፡

 

በምዕራብ ወለጋ ዞን የጉሊሶ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት

 

Save Tender