Tender Detail

Tender Details


በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በአ/ከ/ክ/ከ በወረዳ 10 ስር የሚገኘው የብርሃን በር ቅድመ አንደኛ፣ እንደኛና መካከለኛ ደረጃ ት/ቤት ከመንግሥት ከተመደበለት መደበኛ እና ውስጥ ገቢ በጀት ለ2018 ዓ.ም አገልግሎት ላይ የሚውሉ የተለያዩ አይነት እቃዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ወረዳ 10 ብርሃን በር ቅድመ አንደኛ፤ አንደኛና መካከለኛ ደረጃ ት/ቤት


 

ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ ቁጥር 01/2018

 

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በአ/ከ/ክ/ከ በወረዳ 10 ስር የሚገኘው የብርሃን በር ቅድመ አንደኛ፣ እንደኛና መካከለኛ ደረጃ ት/ቤት ከመንግሥት ከተመደበለት መደበኛ እና ውስጥ ገቢ በጀት ለ2018 ዓ.ም አገልግሎት ላይ የሚውሉ የተለያዩ አይነት እቃዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡

ሎት 1 - የደንብ ልብስ (የልብስ ስፌትን ያካትታል) ሎት 2 አላቂ የቢሮ እቃዎች ሎት 3 አላቂ የትምህርት ዕቃዎች ሎት-4- ሌሎች አላቂ እቃዎች ሎት-5 የተለያዩ መጽሐፍት ሎት-6 ቋሚ እቃዎች ሎት 7 በፕላንት ማሽን ቋሚ እቃዎች ሎት 8 -ኤሌክትሮኒክስ ጥገና አገልግሎት ሎት-9 አላቂ የህክምና  እቃዎች ለመግዛት የሚፈልግ ሲሆን የሚከተሉትን የጨረታ መስፈርት የሚያሟሉ ተጫራቾችን እንዲወዳደሩ ይጋብዛል፡፡

  • ተጫራቾች የ2018 ዓ.ም የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፤
  • የቫት ተመዝጋቢ የሆኑ፤ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (TIN) የተሰጠው፤
  • ወቅታዊ የ2017 ዓ.ም የግብር ግዴታቸውን የተወጡና በጨረታው መሣተፍ የሚችሉ መሆኑን የሚገልጽ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ።
  • በኢፌዴሪ የመንግሥት ግዥና ንብረት አስተዳደር ኤጀንሲ በአቅራቢነት ሊስት (Supplier List) ውስጥ የተመዘገቡ፤
  • በጨረታ መሳተፍ የሚችሉ መሆኑን የሚገልጽ የጨረታ ተሳትፎ ከገቢዎችና ጉምሩክ ጽ/ቤት ቀኑ ያላለፈበት ማስረጃ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
  • ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 /አስር/ ተከታታይ የሥራ ቀናት የማይመለስ ብር 200.00 /ሁለት መቶ ብር/ በመክፈል ከብርሃን በር ቅድመ አንደኛ፣ አንደኛና መካከለኛ ደረጃ ት/ቤት ፋይናንስ ክፍል ከጠዋቱ 2:30-11፡00 ሰዓት ድረስ መግዛት የሚችሉ መሆኑን እየገለጽን፤ ተጫራቾች በገዙት የጨረታ ሰነድ በእያንዳንዱ ገጽ ላይ ሕጋዊ የድርጅት ማህተብና ፊርማ ማድረግ ይኖርባቸዋል፡፡ ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን ዋጋ በጨረታ ሰነድ ውስጥ በሚገኘው የእቃዎች ዝርዝር ላይ የእያንዳንዱን ዋጋ በመሙላት በታሸገ ኤንቨሎፕ ሰነዱን አሽገው ዋናውን እና ኮፒውን ለያይተው ጨረታው እስከሚያበቃበት 10ኛው ቀን እስከ 11፡00 ድረስ ማስገባት ይችላሉ፡፡ ጨረታው በ11ኛው የሥራ ቀን ከዋለ ከጠዋቱ 4፡00 ታሽጎ በዕለቱ 4:30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል። (ተጫራቾች ባይገኙም ጨረታውን ከመከፈት አያስተጓጉለውም)። የጨረታ መዝጊያና መክፈቻ የሥራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን በተመሣሣይ ሰዓት ይከፈታል ማንኛም ተጫራች መጫረት የሚችለው በሚመለከተው የንግድ ፍቃድ (የሥራ ዘርፍ) ብቻ ነው:: ከጥቃቅንና አነስተኛ ተደራጅታችሁ የዋስትና ደብዳቤ ለሚያመጡ ድርጅቶች በሚወዳደሩበት ዘርፍ የራሳችሁ ምርት (አምራች) መሆናችሁን የሚገልጽ መረጃ በማቅረብ በአመረታችሁት እቃ ላይ ብቻ የምትወዳደሩ መሆኑን እናሳውቃለን፡፡
  • ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ከታች በተዘረዘሩት ሎቶች በተቋሙ ስም ሲፒኦ (CPO) በማሠራት ከዋናው ሰነድ ጋር ማያያዝ ይኖባቸዋል፡፡

 

ሎት 1

ሎት 2

ሎት 3

ሎት 4

ሎት 5

 ሎት 5

ሎት 6

ሎት 7

ሎት 8

0.5%

0.5%

0.5%

1%

2%

1%

1%

0.5%

2%

7000

6600

4300

14800

1000

1700

14775

1600

3840.46

 

ማሳሰቢያ፡-

  • ተጫራቾች የተጫረቱበትን እቃዎች ናሙና /ሳምፕል/ ጨረታው ከመከፈቱ በፊት ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
  • ተጫራቾች የሚጫረቱበትን ዋጋ በገዙት ሰነድ የዋጋ ማቅረቢያ ቦታ ላይ ቫትን ጨምረው ስርዝ ድልዝ ሳይኖረው መሙላት አለባቸው።
  • አሸናፊ ተጫራቾች ውል ከመፈረማቸው በፊት የውል ማስከበሪያ የተጫረቱበትን ጠቅላላ ዋጋ 10% ማስያዝ አለባቸው
  • ብርሃን በር ቅድመ አንደኛ፣ አንደኛና መካከለኛ ደረጃ ት/ ቤት በጨረታው ከሚቀርቡት የእቃዎች ብዛት አሸናፊ ከሆነው ድርጅት እስከ 20% ድረስ መቀነስ ወይም መጨመር ይችላል፡፡
  • ትምህት ቤቱ ጨረታውን የመሰረዝ መብቱ በሕግ የተጠበቀ ነው።
  • ተጫራቾች ያስገቡትን ሳምፕል ጨረታው ከተጠናቀቀ በኋላ በጊዜው ካልወሰዱ ለሚደርሰው ጉዳት ተቋሙ ተጠያቂ አይሆንም።

አድራሻ፡- አጠና ተራ ከተቃጠለው ሕንፃ ፊት ለፊት ስልክ ቁጥር 0112739672 /0112792458

facebook.com/berhanber.ber

Addis Ketema Sub-City Woreda 10

Email:Berhanber@gmail.com

t.me/berhan

0112792458

Pobox:16481

 

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ወረዳ 10 ብርሃን በር ቅድመ አንደኛ፤ አንደኛና መካከለኛ ደረጃ ት/ቤት

 

Save Tender