በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ወረዳ ከ አስተዳደር ሥር የሚገኝ የሶር አምባ አንደኛ እና መካከለኛ ደረጃ ት/ቤት ለ2018 በጀት ዓመት ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን - ሎት 01 የመምህራን እና የአስተዳደር ሠራተኞች የደንብ ልብስ እና የስፖርት ትጥቅ፣ሎት 02 የትምህርት ዕቃዎች፣ ሎት 3 የህትመት ሥራዎች፣ ሎት 04 ሌሎች አላቂ ዕቃዎች እና አቅርቦቶች፣ ሎት 05 ልዩ ልዩ መሳሪያዎች፣ ሎት 06 ቋሚ ዕቃዎች ለፕላንት ለማሽነሪ እና ለመሳሪያ መግዣ፣ ሎት 07 ለሕንፃ ለቁሳቁስና ለተገጣጣሚ መግዣ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት/ማሠራት ይፈልጋል፡፡
በአዲስ ከተማ ክ/ ከተማ ወረዳ 11 ትምህርት ጽ/ቤት የሶር አምባ አንደኛ እና መካከለኛ ደረጃ ት/ቤት
የግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ
በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ወረዳ ከ አስተዳደር ሥር የሚገኝ የሶር አምባ አንደኛ እና መካከለኛ ደረጃ ት/ቤት ለ2018 በጀት ዓመት ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን - ሎት 01 የመምህራን እና የአስተዳደር ሠራተኞች የደንብ ልብስ እና የስፖርት ትጥቅ፣ሎት 02 የትምህርት ዕቃዎች፣ ሎት 3 የህትመት ሥራዎች፣ ሎት 04 ሌሎች አላቂ ዕቃዎች እና አቅርቦቶች፣ ሎት 05 ልዩ ልዩ መሳሪያዎች፣ ሎት 06 ቋሚ ዕቃዎች ለፕላንት ለማሽነሪ እና ለመሳሪያ መግዣ፣ ሎት 07 ለሕንፃ ለቁሳቁስና ለተገጣጣሚ መግዣ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት/ማሠራት ይፈልጋል፡፡
የግልጽ ጨረታ መመሪያ፡-
-
* እያንዳንዱ ተጫራች የሚከተሉትን ነጥቦች በመረዳት የጨረታ ሰነዱን በዚህ መመሪያ መሠረት አሟልቶ ማቅረብ ይኖርበታል፡፡ ተጫራቾች የዘመኑ ግብር የከፈሉበትንና አግባብነት ያለው በዘመኑ የታደሰ ንግድ ፍቃድ፣ ከገንዘብ እና ኢኮኖሚ ልማት ሚኒስቴር ወይም በአዲስ አበባ ከተማ ፋይናንስና ኢኮኖሚ ልማት ቢሮ በእቃ አቅራቢነት የተመዘገቡትን የምስክር ወረቀትና የቫት ተመዝጋቢ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ መረጃ ከጨረታው ሰነድ ጋር አያይዘው ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡ ፡በተጨማሪም የኤጀንሲውን ድረ-ገጽ/ዌብሳይት/www.ppa.gov.et መጎብኘት አለባቸው፡፡
-
የጨረታ ሰነዱ በፖስታ ታሽጎ ለዚህ ተብሎ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ የጨረታ ሳጥን የሚታሸግበት ሰዓት ከመድረሱ በፊት መግባት ይኖርበታል፡፡
-
ተጫራቾች ከላይ ከተራ ቁጥር ከ1-7 ከተዘረዘሩት የጨረታ ዓይነቶች በሙሉ ወይም በከፊል መጫረት ይችላሉ፡፡ በተጨማሪ ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በıo ተከታታይ የሥራ ቀናት ዘወትር በሥራ ሰዓት እስከ 11፡30 የጨረታ ሰነድ በሶር አምባ አንደኛ እና መካከለኛ ደረጃ ት/ቤት ክፍያ ሂሳብ አስተዳደር ደጋፊ የሥራ ሂደት በመቅረብ የተዘጋጀውን ሰነድ የማይመስስ ብር 200.00(ሁለት መቶ ብር) ከፍለው በመውሰድ ከቀኑ 11፡30 ድረስ ማስገባት ይችላሉ፡፡
-
ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን የጨረታ ዓይነት ውስጥ የተዘረዘሩትን ዕቃዎች የአንዱን ዕቃ ዋጋ ቫትን ጨምሮ በግልፅ ማስፈር አለባቸው::
-
ተጫራቾች ሙሉ ስማቸውን አድራሻቸውንና ፊርማቸውን በእያንዳንዱ የሰነድ ገጽ ላይ በማኖር በማህተም ማረጋገጥ አለባቸው፡፡
-
በጨረታ አሸናፊ ሆኖ የተመረጠው ድርጅት ከመስሪያ ቤቱ የበላይ ኃላፊ ጋር በሚገባው ውል መሠረት ዕቃዎቹን እንዲያስገባ ሲታዘዝ በራሱ ወጪ ዕቃ ግምጃ ቤታችን ድረስ አቅርቦ ማስረከብ የሚችል መሆን አለበት፡፡
-
ተጫራቾች በጨረታ ማስከበሪያነት የሚያገለግል የገንዘብ መጠን በየጨረታ ሎት ተከፋፍሎ እንደሚከተለው ቀርቧል፡፡
ሎት 01 የመምህራን እና የአስተዳደር ሠራተኞች የደንብ ልብስ እና የስፖርት ትጥቅ በዚህ ከፍል የተጠየቀው የብር መጠን 9000.00 ብር በ 0.5% ተሰልቶ
ሎት 02 የትምህርት ዕቃዎች 8000.00 ብር በ0.5% ተሰልቶ
ሎት 03 የህትመት ሥራዎች 1750.00 ብር በ0.5% ተሰልቶ
ሎት 04 ሌሎች አላቂ ዕቃዎች እና አቅርቦቶች 7500.00 ብር በ0.5% ተሰልቶ
ሎት 05 ልዩ ልዩ መሳሪያዎች 691.00 ብር በ 0.5% ተሰልቶ
ሎት 06 ቋሚ ዕቃዎች ለፕላንት ለማሽነሪ እና ለመሳሪያ መግዣ 11,000.00 ብር በ0.5% ተሰልቶ ሎት 07 ለሕንፃ ለቁሳቁስና ለተገጣጣሚ መግዣ ሥራዎች 12,500.00 ብር በ 0.5% ተሰልቶ መሆኑን አውቃችሁ ተጫራቾች ከዚህ በላይ የተጠቀሰውን የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ ከዋጋ ማቅረቢያ ጋር በታሸገ ኤንቨሎፕ አሽጎ በጨረታ ሳጥን ውስጥ በመስሪያ ቤታችን ስም ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡ በተጨማሪም የጨረታ ሰነዱን የሚሞላ ክፍል በአገባቡ ሞልቶ ተመላሽ ያላደረገ አቅራቢ ከጨረታ እንደሚሰረዝ እናሳስባለን፡፡
-
በጥቃቅንና አነስተኛ የተደራጁ ተጫራቾች በዚህ ጨረታ እንዲወዳደሩ እየተጋበዙ እንዲሁም _ ካደራጃቸው አካል ለጨረታ ሰነድ ግዥ በጨረታ ማስከበሪያነት የሚያገለግል በመስሪያ ቤቱ ስምና ኃላፊነት መውሰድ በሚችል አካል የተፃፈ ደብዳቤ እና አምራች መሆናቸውን የሚገልፅ ማስረጃ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡ይህንን ማቅረብ ካልቻሉ እንደማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሰነድ ይገዛሉ የጨረታና የውል ማስከበሪያ ያስይዛሉ፡፡
-
የጨረታ ሳጥኑ ከተዘጋ በኋላ የሚቀርብ የመጫረቻ ሰነድ ተቀባይነት አይኖረውም ::
-
ጨረታው ለ10 ተከታታይ የሥራ ቀናት ቆይቶ በሚቀጥለው በ11 ኛው የሥራ ቀን ከጠዋቱ 2፡30 ላይ ታሽጎ ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ከጠዋቱ 3፡00 ሰዓት ላይ የሚከፈት ሲሆን ጨረታው የሚከፈትበት ቀን የበዓል ቀን ከሆነ በቀጣዩ የሥራ ቀን በተገለፀው ሰዓት ይከፈታል፡፡ ተጫራቾች ለሚጫረቱባቸው ለእያንዳንዱ ዕቃ ከጨረታው መዝጊያ ሰዓት ከሁለት ቀን በፊት ናሙናዎችን ማቅረብና ለግዥ (ለተወከለው) ሠራተኛ ማስረከብ ይኖርባቸዋል፡ ፡ ናሙና ማቅረብ የማይቻልባቸው ቋሚ ዕቃዎችን በፎቶ በማስደገፍና ስለ ዕቃው አስፈላጊ የሆኑ መረጃዎችን ማቅረብ አለባቸው፡፡
-
የመ/ቤቱ የዕቃ ጥራት ተቆጣጣሪ ኮሚቴ (የቴክኒክ ኮሚቴ) ያቀረቡትን የዕቃዎቹን ጥራት አይቶ ከመስሪያ ቤቱ ፍላጎት ጋር የማይጣጣም ነው ብሎ ካመነ እንዲመለስ ማድረግ ይችላል፡፡
-
የጨረታው አሸናፊ ድርጅት/ድርጅቶች ማሸነፉ እንደተገለፀለት በተሰጠው የጊዜ ገደብ ከ7ኛ-15ኛው ቀን ውስጥ ቀርቦ ውል ካልፈፀመ በጨረታ ማስከበሪያነት ያስያዘው ገንዘብ ለመንግስት ገቢ ሆኖ መ/ቤቱ እንደ ምርጫው ሁለተኛ ወይም ሦስተኛ የወጣውን ተወዳዳሪ ሊጋብዝ ይችላል፡፡
-
የግዥ ውል በሚፈፀምበት ጊዜ ለውል ማስከበሪያነት የሚውል ያሸነፉትን ዕቃ ጠቅላላ ዋጋ 10% ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
-
የግዥ ውል በሚፈፀምበት ጊዜ መ/ቤቱ በጨረታ ሰነድ ላይ የተመለከተውን የዕቃ ብዛትና ተያያዥ አገልግሎቶች እስከ 20 በመቶ ሊጨምር ወይም ሊቀንስ ይችላል፡፡
-
ለቋሚ ዕቃዎች እና የማሽን ቀለሞች ትክክለኛ ለመሆናቸው አሸናፊ ተጫራቾች ለአንድ ዓመት ዋስትና ይሰጣል፡፡
-
መ/ቤቱ አስፈላጊ ሆኖ ሲያገኘው በድርጅቱ የሥራ ቦታ በመገኘት የዕቃዎችን ጥራትና የድርጅቱን አቅም ለመገምገም ቢፈልግ ድርጅቱ የመተባበር ግዴታ አለበት፡፡
-
ለውድድር የሚቀርበው የጨረታ ሰነድ ኮፒ ከኦርጅናል ሰነድ ጋር ለየብቻ መቅረብ ይኖርበታል፡፡ በተጨማሪም ተጫራቹ የገዛው ሙሉ ሰነድ ኮፒ እና ኦርጅናል ሙሉ በሙሉ ተመላሽ ካላደረገ ከጨረታ ውጭ ይሆናል፡፡
-
በመ/ቤታችን ለዕቃ ጥራት ከፍተኛ ትኩረት የሚሰጥ በመሆኑ ተወዳዳሪዎች የተሻለ ጥራት ያላቸውን ዕቃዎች እንዲያቀርቡ ይበረታታሉ፡፡
-
ለማጭበርበር የሞከረ ተጫራች ከጨረታው ይሰረዛል፡፡
-
የዕቃውን ዋጋ ማቅረብ የምትችሉት ት/ቤቱ በሸጠላችሁ ሰነድ ብቻ ሞልታችሁ ማቅረብ አለባችሁ፡፡
-
መ/ቤቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
አድራሻ፡- ከአጠና ተራ ሎሚ ሜዳ ሲደርሱ ወደ ግራ 200 ሜትር ገባ ብሎ ኢንዱስትሪ መንደር አካባቢ የሚገኘው የሶር አምባ የመ/ደ/ት/ቤት፡፡ ስልክ ቁጥር፡- 011-8-27-78-01
በአዲስ ከተማ ክ/ ከተማ ወረዳ 11 ትምህርት ጽ/ቤት የሶር አምባ አንደኛ እና መካከለኛ ደረጃ ት/ቤት
