Tender Detail

Tender Details


የአራዳ ክ/ከተማ ወ01 ፋይናንስ ጽ/ቤት ብቁ ድርጅቶችን በማወዳደር ለ2018 ዓ/ም ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ከሎት 1-4 በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት እና ከሎት 05-13 በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ማሠራት ይፈልጋል፡፡

የአራዳ ክ/ከተማ ወ01 ፋይናንስ ጽ/ቤት


 

ግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር 01/2018 ዓ.ም

 

በዚሁ መሠረት ተጫራቾች ማሟላት ያለባችሁ መስፈርቶች በአራዳ ክ/ከተማ ወረዳ 01 ፋይናንስ ጽ/ቤት በግልፅ ጨረታ ለሚሳተፉ ብቁ ድርጅቶችን በማወዳደር ለ2018 ዓ/ም

    • ሎት 1 የፅዳት ዕቃዎች ፤
    • ሎት 2 ስቴሽነሪ ዕቃዎች ፤
    • ሎት 3 የደንብ ልብስ
    • ሎት 4 ቋሚ እቃ
    • ሎት 5 የተለያዩ ህትመቶች
    • ሎት 6 የተለያዩ መስተንግዶዎች
    • ሎት 7 የኤሌክትሮኒክስ ጥገና
    • ሎት 8 የፈርኒቸር ጥገና
    • ሎት 9 የዕቃ ጭነት መኪና ኪራይ በብያጆ
    • ሎት 10 የጉዞ መኪና በኪሎ ሜትር
    • ሎት 11 የዲኮር ሥራ
    • ሎት 12 የልብስ ስፌት
    • ሎት 13 ድንኳን ኪራይ

ከሎት 1-4 በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት እና ከሎት 05-13 በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ማሠራት ይፈልጋል፡፡ በዚሁ መሠረት

1ኛ. በዘርፍ የታደሰ ንግድ ፍቃድ ያላቸው

2ኛ. የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ለተጫረቱበት ሎት ላይ 1.5% በባንክ በተረጋገጠ (cpo) ብቻ ማቅረብ አለባቸው

3ኛ. ተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ የሆኑ

4ኛ. ቫት ከፋይ የሆኑ

5ኛ. ሰነዱ የማይመለስ ዋጋ 300 ብር በመግዛት ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በወረዳው ፋ/ጽ/ቤት ከግዥ ቢሮ መውሰድ ይችላሉ፡፡

6ኛ. ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ የሥራ ቀናት ውስጥ በተዘጋጀው ቅፅ ላይ በመሙላት የድርጅታችሁን ክብ ማህተም ኦርጅናል እና ኮፒ ላይ በማድረግ በታሸገ ፖስታ ወረዳው ባዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው

7ኛ. የጨረታ ሳጥኑ በአስራ አንደኛ ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ታሽጎ በ4፡30 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል።

8ኛ. ሞልታችሁ ለምታስገቡት የጨረታ ሰነዱ ላይ ቀን ገድባቹ ካስገባቹ የማንቀበል መሆኑ

9ኛ. ወረዳው የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ መሆኑን እንገልፃለን፡፡

ማሳሰቢያ፡- ከሎት 5-13 ያለው ሎት (cpo) የማያቀርቡ መሆኑን እንገልፃለን፡፡

አድራሻ፡- በአ/ክ/ከ ወ01/ፋ/ጽ/ቤት ከጣይቱ ሆቴል ዝቅ ብሎ

 

ስልክ፡- 0970257122

 

የአራዳ ክ/ከተማ ወ01 ፋይናንስ ጽ/ቤት

 

Save Tender