Tender Detail

Tender Details


በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት የዋግ ኽምራ ብሔረሰብ አስተዳደር ገንዘብ መምሪያ ለብሔረሰብ አስተዳደሩ የተለያዩ ሴክተር መ/ቤቶች አገልግሎት የሚውሉ የተለያዩ አይነትና መጠን ያላቸውን የጽሕፈት መሣሪያዎች፣ የኤሌክትሮኒክስ እቃዎች፣ የሠራተኞች የደንብ ልብስ፣ የመኪና ጎማዎች፣ የስፖርት ትጥቆች፣ የፅዳት እቃዎች፣ የቀላልና ከባድ ተሽከርካሪ መለዋወጫዎች እና ፈርኒቸርና የፈርኒቸር ውጤቶች እንዲሁም የተሽከርካሪ ጥገና አገልግሎት ግዥን በሃገር አቀፍ ግልጽ የጨረታ ግዥ ዘዴ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡

በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት የዋግ ኽምራ ብሔረሰብ አስተዳደር ገንዘብ መምሪያ


                       የቋሚ እና አላቂ እቃዎች እንዲሁም የመኪና ጥገና አገልግሎት ግዥ

                                    ሃገር አቀፍ ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

                                      የጨረታ ቁጥር፡- ጨ-1/0544/2017


 

በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት የዋግ ኽምራ ብሔረሰብ አስተዳደር ገንዘብ መምሪያ ለብሔረሰብ አስተዳደሩ የተለያዩ ሴክተር መ/ቤቶች አገልግሎት የሚውሉ የተለያዩ አይነትና መጠን ያላቸውን የጽሕፈት መሣሪያዎች፣ የኤሌክትሮኒክስ እቃዎች፣ የሠራተኞች የደንብ ልብስ፣ የመኪና ጎማዎች፣ የስፖርት ትጥቆች፣ የፅዳት እቃዎች፣ የቀላልና ከባድ ተሽከርካሪ መለዋወጫዎች እና ፈርኒቸርና የፈርኒቸር ውጤቶች እንዲሁም የተሽከርካሪ ጥገና አገልግሎት ግዥን በሃገር አቀፍ ግልጽ የጨረታ ግዥ ዘዴ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡

ስለሆነም የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር የሚችሉ መሆኑን ይጋብዛል፡፡

  1. ከሚወዳደሩት አቅርቦት ወይንም አገልግሎት ግዥ ጋር የተዛመደ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ማቅረብ የሚችሉ ሆኖ የተሰጣቸው ፈቃድ አንድ ዓመት የሞላው ከሆነ የታደሰ የንግድ ፈቃድ ማቅረብ የሚችሉ፤

  2. የግብር ከፋይነት ምስክር ወረቀት (Tax Payer Identification Number) ያላቸው፤

  3. በግዥ አፈጻጸም መመሪያው የተጨማሪ እሴት ታክስ (Value Added Tax Certificate) ተመዝጋቢዎች ብቻ እንዲወዳደሩ ከተፈቀዱ የንግድ ዘርፎች ውጪ የግዥው መጠን ከ200,000 (ሁለት መቶ ሺህ) ብር በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ (value Added Tax Certificate) ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፤

  4. ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ ከላይ ከተራ ቁጥር 1-3 የተጠቀሱትንና ሌሎች የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡

  5. የሚዝዙትን እቃ እና አገልግሎት አይነት ዝርዝር መግለጫ (Specification) ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይችላሉ፡፡

  6. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ለእያንዳንዱ ሎት /ምድብ/ የማይመለስ ብር 50 /ሀምሳ/ በመክፈል የፋይናንስ ቡድን ቢሮ ቁጥር 6 ማግኘት ይችላሉ፡፡

  7. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (Bid Bond) ለሚወዳደሩበት ለእያንዳንዱ ሎት /ምድብ/ ጠቅላላ ዋጋ 1% (አንድ በመቶ) በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ (የማይሻርና ያለተጨማሪ ስነ-ስርዓት በመጠየቅ ብቻ ተከፋይ የሚሆን የባንከ ዋስትና) ወይም በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ /CPO/ ወይም በጥሬ ገንዘብ /ዋናውን የገቢ ደረሰኝ/ ማስያዝ አለባቸው።

  8. ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሰነዱ የጨረታ ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን አንስቶ እስከ ተከታታይ አስራ አምስተኛው ቀን ድረስ ዘወትር በሥራ ሰዓት ሠነዱን በመግዛት የጨረታ ሃሳቡን በጥንቃቄ በታሸገ አንድ ወጥ ፖስታ ዋናውን በዋ/ኽ/ብ/አስ/ር/ገ/መምሪያ ግ/ን/አስ/ርቡድን ቢሮ ቁጥር 9 በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን እስከ አስራ ስድስተኛው ቀን 3:00 ሰዓት ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡

  9. ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በዋ/ኽ/ብ/አስ/ር/ገ/መምሪያ ግ/ን/አስ/ርቡድን ቢሮ ቁጥር 9 የጨረታ ማስታወቂያው ከወጣበት ጊዜ አንስቶ በአስራ ስድስተኛው ቀን በ3፡00 ሰዓት ታሽጎ በ3፡30 ሰዓት ይከፈታል፡፡ ሆኖም ጨረታው የሚከፈትበት ቀንና ሰዓት ከመንግስት የሥራ ቀን ውጪ ከሆነ በተመሳሳይ ሰዓት በሚቀጥለው የመንግሥት የስራ ቀን ይከፈታል፡፡

  10. መምሪያው የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው። ይህም ሲባል ጨረታ በመሰረዙ ተጫራቾች በጨረታው ለመወዳደር ላወጡት ወጪ መ/ቤቱ ኃላፊነት የማይወስድ መሆኑን መገንዘብ ይኖርባቸዋል፡፡

  11. ተጫራቾች ስለ ጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ በዋ/ኽ/ብ/አስ/ር/ገ/መምሪያ ግ/ን/አስ/ር/ደ/የስ/ሂደት ቢሮ ቁጥር 9 በአካል በመገኘት ወይንም በስልክ ቁጥር 033-4-40-12-30/ 02-49/00-62 በመደወል ማግኘት ይችላሉ፡፡


 

                 በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት የዋግ ኽምራ ብሔረሰብ አስተዳደር ገንዘብ መምሪያ


 


 

Save Tender