Tender Detail

Tender Details


የጥበብ እድገት ቅ/አ/አ/መ/ደ/ት/ቤት የ2018 ዓ/ም ቋሚ እና አላቂ እቃዎችን፣ የፕላንት ማሸነሪ ጥገና እና እድሳት፣ የቢሮ አድሳት እና ጥገና በ1ኛ ዙር ግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ማሰራት ይፈልጋል፡፡

የጥበብ እድገት ቅ/አ/አ/መ/ደ/ ት/ቤት


 

የጨረታ ማስታወቂያ

 

የጥበብ እድገት ቅ/አ/አ/መ/ደ/ት/ቤት የ2018 ዓ/ም ቋሚ እና አላቂ እቃዎችን፣ የፕላንት ማሸነሪ ጥገና እና እድሳት፣ የቢሮ አድሳት እና ጥገና በ1ኛ ዙር ግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ማሰራት ይፈልጋል፡፡

ስለሆንም ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የምታሟሉ ተጫራቾች ጨረታውን መወዳደር ትችላላችሁ።

  1. የታደሰ ንግድ ፈቃድ የዘመኑን ግብር የከፈሉ የተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) ተመዝጋቢ የሆኑ እንዲሁም በአቅራቢነት ዝርዝር ውስጥ የተመዘገቡ መሆን አለባቸው።
  2. ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት ተከታታይ 10 የስራ ቀናት በት/ቤቱ ግ/ፋ/ን/አስ በመገኘት የማይመለስ 200 (ሁለት መቶ ብር ብቻ) በመክፈል የጨረታ ሰነድ በት/ቤቱ ግቢ ቢሮ ቁጥር G+1/008 በመምጣት መግዛት ትችላላችሁ። ተጫራቾች የሚጫረቱበትን ዋጋ ስርዝ ድልዝ ሳይኖርበት ግልፅ በሆነ መንገድ ቫትን አካቶ በመሙላት ት/ቤቱ ባዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ቢሮ ቁጥር G+1/005 ኦርጅናል እና ኮፒውን ማስገባት አለበት።
  3. ጨረታው ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ10 ተከታታይ የስራ ቀናት ክፍት ሆኖ የሚቆይ ሲሆን በ11ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ላይ ታሽጎ በዚያው ቀን ከጠዋቱ 4፡30 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ቢሮ ቁጥር G+1/005 ይከፈታል ፡፡
  4. የጨረታ ማስከበሪያ 10,000 (አስር ሺ ብር ብቻ) በባንክ የተረጋገጠ /CPO/ ማስያዝ ይኖርባቸዋል።
  5. ት/ቤቱ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  6. ተጫራቾች ለሚወዳደሩበት እቃዎች ናሙና ማቅረብ ይኖርባቸዋል ነገር ግን ቋሚ እቃ በፎቶ ማቅረብ አለባቸው።
  7. ተጫራቾች ዋጋ መሙላት ያለባቸው ት/ቤቱ ባዘጋጀው ሰነድ ብቻ ነው።

አድራሻ፡- በአራዳ ክ/ከተማ ወረዳ 04 ከወ/ሮ ቀለም ወርቅ መሰናዶ ት/ቤት ከፍብሎ ፊውቸር ሆፕስ ት/ቤት ፊት ለፊት 100 ሜትር ገባ ብሎ

ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር፡- 0111 11 93 06 / 0913 43 66 12 / 0904 23 76 85

 

የጥበብ እድገት ቅ/አ/አ/መ/ደ/ ት/ቤት

 

Save Tender