Tender Detail

Tender Details


በጅማ ዞን የመንቾ ወረዳ ገ/ጽ/ቤት በ2018 የበጀት ዓመት የመኪና ጎማዎች፣ የቢሮ ቋሚ እቃዎች፣ የኤሌከትሮኒከስ መሳሪያዎች፣ የጽሕፈት እና ንጽህና መሳሪያዎች፣ የግንባታ እቃዎች፣ የሞተር ሳይከል እና ደንብ ልብስ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ግዢ ለመፈፀም ይፈልጋል፡፡

በጅማ ዞን የመንቾ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት


የጨረታ ማስታወቂያ

በጅማ ዞን የመንቾ ወረዳ ገ/ጽ/ቤት በ2018 የበጀት ዓመት የመኪና ጎማዎች፣ የቢሮ ቋሚ እቃዎች፣ የኤሌከትሮኒከስ መሳሪያዎች፣ የጽሕፈት እና ንጽህና መሳሪያዎች፣ የግንባታ እቃዎች፣ የሞተር ሳይከል እና ደንብ ልብስ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ግዢ ለመፈፀም ይፈልጋል፡፡ በዚህ መሠረት የመወዳደሪያ መስፈርቶች፡-

1. በዘርፉ የዘመኑ የታደሰ ንግድ ፈቃድ ማቅረብ የሚችሉ፤

2. የዘመኑ ግብር የከፈሉበትን ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፤

3. በንግድና ከተማ ልማት ጽ/ቤት በስነ-ስርዓት ጉድለት ያልተከሠሡ፤

4. የግብር መለያ ቁጥር (TIN NO.) ማቅረብ የሚችሉ፤

5. የፌዴራል እና የክልል ግዢ ስርዓት አስተዳዳር የሚያከብሩ፤

6. ተጫራቾች የተጨማሪ እሴት ታከስ (VAT) ተመዝጋቢ የሆኑና ለዚሀ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፤

7. ተወዳዳሪዎች የአቅራቢነት ዝርዝር ውስጥ መመዝገባቸውን የሚገልጽ መረጃ ማቅረብ አለባቸው፡፡

8. ተወዳዳሪዎች በሰነዱ ላይ ትክክለኛ አድራሻ፣ ስም እና ፊርማ ማሳረፍ አለባቸው፡፡

9. የጨረታው ማስከበሪያ ማረጋገጫ የሚሆን 15,000 (አስራ አምስት ሺህ) ብር በጥሬ ገንዘብ ወይም በባንክ የተረጋገጠ CPO ማስያዝ የሚችሉ፡፡

10. ጨረታውን ያሸነፈው አካል ህጉ በሚፈቅደው መሠረት 2% (ሁለት ፐርሰንት) የመከፈል ግዴታ አለበት፡፡

11. ጨረታው ላይ የሚሳተፉ ተጫራቾች ከሙስና እና ከመሰል ነገሮች ነጻ መሆን አለባቸው፡፡

12. ጨረታው የሚከናወነው ሰነዱ በወጣበት ቋንቋ መሠረት ይሆናል፡፡

13. ሁሉም ተወዳዳሪዎች ከጨረታው ሰነድ አንድም ገጽ ሳያጎሉ ሞልተው መመለስ አለባቸው፡፡

14. የተጠቀሱ እቃዎች በጥራት እና ደረጃውን በጠበቀ ማቅረብ የሚችሉ፤

15. የጨረታው ሰነድ ቴክኒክ እና ፋይናንሻል ኦሪጅናል እና ኮፒ ለየብቻ (4 ፖስታ) በአንድ ፖስታ አሽገው ማቅረብ አለባቸው፡፡

16. ከላይ የተዘረዘሩትነወ ነጥቦች ማሟላት የሚችሉ ተጫራቾች ከመንቾ ወረዳ ገቢዎች ጽ/ቤት ቀርበው የማይመለስ የኢትዮጵያ 500 (አምስት መቶ) ብር ከፍለው የጨረታውን ሰነድ መግዛት ይችላሉ፡፡

17. ተወዳዳሪዎች የጨረታ ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ በተከታታይ 25 (ሀያ አምስት) የስራ ቀናት ውስጥ ሰነድ መግዛት ትችላላችሁ፡፡

18. የጨረታው ሰነድ ሳጥን በቀን 4/13/2017 ዓ.ም በ4:00 ሰዓት የሚዘጋ ሆኖ የሚከፈተው በማግስቱ ተወዳዳሪዎች ወይም ህጋዊ ውከልና ያላቸው ተወካዮች በተገኙበት በ5/13/2017 ዓ.ም በ4:30 ሰዓት ይሆናል፡፡

19. የጨረታው መከፈቻ ቅዳሜ እና እሁድ ወይም በበዓል ቀን ላይ ከዋለ በሚቀጠለው የስራ ቀን ይሆናል፡፡

20.መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር፡-09-02-16-25-76/ 09-35-08-19-63

በጅማ ዞን የመንቾ ወረዳ ገ/ጽ/ቤት

Save Tender