በአራዳ ክፍለ ከተማ የወረዳ 05 አስተዳደር ኒው ኤራ 1ኛና መካከለኛ/ት/ቤት በ2018 ዓ/ም በ1ኛ ዙር ግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ከዚህ በታች በሎት የተዘረዘሩትን መግዛት ይፈልጋል፡፡
በአራዳ ክፍለ ከተማ የወረዳ 05 አስተዳደር ኒው ኤራ 1ኛና መ/ደ/ት/ቤት
የጨረታ ማስታወቂያ
በአራዳ ክፍለ ከተማ የወረዳ 05 አስተዳደር ኒው ኤራ 1ኛና መካከለኛ/ት/ቤት በ2018 ዓ/ም በ1ኛ ዙር ግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ከዚህ በታች በሎት የተዘረዘሩትን መግዛት ይፈልጋል፡፡
|
የሎት አይነት |
የCPO መጠን |
|
ለሎት 1 የደንብ ልብስ እቃዎች |
3000 /ሶስት ሺህ/ብር |
|
ለሎት 2 አላቂ የቢሮ እቃዎች |
3000 /ሶስት ሺህ/ብር |
|
ለሎት 3 የሕትመት ስራዎች |
3000 /ሶስት ሺህ/ብር |
|
ለሎት 4 አላቂ የሕክምና እቃዎች |
3000 /ሶስት ሺህ/ብር |
|
ለሎት 5 አላቂ የትምህርት እቃዎች |
3000 /ሶስት ሺህ/ብር |
|
ለሎት 6 አላቂ የጽዳት እቃዎች |
3000 /ሶስት ሺህ/ብር |
|
ለሎት 7 ልዩ ልዩ መሳሪያዎች |
3000 /ሶስት ሺህ/ብር |
|
ለሎት 8 የፕላንት ማሽነሪንግ ጥገና |
3000 /ሶስት ሺህ/ብር |
|
ለሎት 9 የህንጻ ቁሳቁስና ልዩ ልዩ የጥገና ስራዎች |
3000 /ሶስት ሺህ/ብር |
|
ለሎት 10 ቋሚ እቃዎችን |
3000 /ሶስት ሺህ/ብር |
|
ለሎት 11 የመስተንግዶ አገልግሎት |
3000 /ሶስት ሺህ/ ብር |
ስለዚህ በጨረታው መሳተፍ የምትፈልጉ አቅራቢ ድርጅቶች የሚከተሉትን መስፈርቶች ማሟላት ይጠበቅባችኋል፡፡
- ህጋዊና የታደሰ የንግድ ፍቃድ ያላቸውና የዘመኑን ግብር የከፈሉ፡፡
- የመንግስት ግዥ እና ንብረት አስተዳደር ኤጀንሲ ባዘጋጀው የእቃና አገልግሎት አቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ የተካተቱ።
- ግብር የመክፈል ግዴታቸውን የተወጡ መሆኑን የሚያረጋግጥ በግብር አስገቢው ባለስልጣን የተሰጠ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- ለተጨማሪ እሴት ታክስ ከፋይነት የተመዘገቡ መሆኑን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ።
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ብር ለእያንዳንዱ ሎት 3000 /ሶስት ሺህ/ ከባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ማዘዣ (CPO) ብቻ በት/ቤቱ ስም ማሰራትና ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- የጨረታ አሸናፊ ከሆኑ ላሸነፉበት እቃ ዋስትና በካሽ ወይም የውል ማስከበሪያ (BID BOND) 10% ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
- ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 200 ብር በመክፈል ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ10 የስራ ቀናት ውስጥ በአራዳ ክፍለ ከተማ ወረዳ 05 አስተዳደር ኒው ኤራ 1ኛና መ/ት/ቤት ፋይናንስና ግ/ን/አስ/ቢሮ ቁ.5 ዘወትር በስራ ሰዓት መጥቶ መውሰድ ይኖርበታል፡፡
- ተጫራች የጨረታ ሰነዱ ላይ የተጠቀሱትን እቃዎች የሚሸጡበትን ዋጋና ሌሎች መረጃዎችንም በሁለት በታሸገ ኤንቨሎፕ ኮፒና ኦርጅናል በማለት እንዲሁም CPO ውን ከኦርጅናሉ ጋር በማያያዝ ለዚሁ ተብሎ በተዘጋጀው የጨረታ ሣጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራች ናሙና ለሚያስፈልጋቸው እቃዎች ጨረታው ከመከፈቱ በፊት ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- ጨረታው ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ10 የስራ ቀናት ቆይቶ በ11 ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ታሽጎ 4፡30 ይከፈታል፡፡
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው። በተጨማሪም መስሪያ ቤቱ የጨረታውን 20% መቀነስ ወይም መጨመር መብቱ የተጠበቀ ነው።
በጨረታው መሳተፍ የምትፈልጉ ተጫራቾች ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ በመ/ቤቱ ግ/ፋ/ንብ/አስ/የስራ ሂደት ክፍል ድረስ በአካል በመምጣት ወይም በስልክ ቁጥር፡- 0111 26 75 10 በመደወል ማግኘት ይችላሉ፡፡
አድራሻ ፡- ፒያሳ ጊዮርጊስ ቤ/ክ አጠገብ ቴሌ ፊት ለፊት
በአራዳ ክፍለ ከተማ የወረዳ 05 አስተዳደር ኒው ኤራ 1ኛና መ/ደ/ት/ቤት
