በኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት የቡሌ ሆራ ከተማ አስተዳደር ገንዘብ ጽ/ቤት ለ2018 ዓ.ም በከተማው ስር ለሚገኙ የመንግስት መስሪያ ቤቶች ቋሚ የቢሮ እቃዎች (ኤሌክትሮኒክስ፣ ፈርኒቸር)፣ የጽሕፈት መሳሪያዎች፣ የጽዳትና ቋሚ አላቂ እቃዎችን እንዲሁም የደንብ ልብስ፣ የሞተር ሳይክሎችን፣ የመኪና መለዋወጫዎች እና የቴክኒክ እና ሙያ ማሰልጠኛ የስልጠና እቃዎች አቅራቢ ድርጅቶች አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
በኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት የምዕራብ ጉጂ ዞን ቡሌ ሆራ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት
የጨረታ ማስታወቂያ
በኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት የቡሌ ሆራ ከተማ አስተዳደር ገንዘብ ጽ/ቤት ለ2018 ዓ.ም በከተማው ስር ለሚገኙ የመንግስት መስሪያ ቤቶች ቋሚ የቢሮ እቃዎች (ኤሌክትሮኒክስ፣ ፈርኒቸር)፣ የጽሕፈት መሳሪያዎች፣ የጽዳትና ቋሚ አላቂ እቃዎችን እንዲሁም የደንብ ልብስ፣ የሞተር ሳይክሎችን፣ የመኪና መለዋወጫዎች እና የቴክኒክ እና ሙያ ማሰልጠኛ የስልጠና እቃዎች አቅራቢ ድርጅቶች አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም በጨረታ ለመወዳደር የሚፈልጉ ተጫራቾች ከዚህ በታች በተገለፀው መስፈርት መሰረት ቀርበው መወዳደር ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች በየንግዱ መስኩ ሕጋዊ የሆነ የንግድ ፈቃዳቸውን፣ አመታዊ የሁለት የ2018 ዓ.ም የሥራ ግብር የከፈሉበትን (ያሳደሱ)፣ በእቃ አቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ የተመዘገቡበትን እንዲሁም የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) የተመዘገቡበትን የሚገልጽ መረጃ ሠነዶቻቸውን ፎቶ ኮፒውን ከጨረታ ሰነድ ጋር አያይዞ ማቅረብ አለባቸው።
- With Holding መክፈል የሚችል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 15 (አስራ አምስት) የሥራ ቀናት ዘወትር በሥራ ሰዓት የማይመለስ ብር 300 (ሦስት መቶ ብር) በቡሌ ሆራ ገቢዎች ባለስልጣን በመክፈል በቡሌ ሆራ ከተማ አስተዳደር ገንዘብ ጽ/ቤት ግዥ ከፍል በማቅረብ ሰነዱን መግዛት ይችላል፡፡
- ማንኛውም ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ የሚሆን ለቋሚ ዕቃዎችና የቴክኒክና ሙያ ማሰልጠኛዎች ብር 25,000 (ሃያ አምስት ሺህ ብር) እንዲሁም ለጽህፈት መሳሪያዎች፣ የጽዳት እና ቋሚ አላቂ እቃዎችና የደንብ ልብስ 10,000 (አሥር ሺህ ብር) በቡሌ ሆራ ከተማ አስተዳደር ገንዘብ ጽ/ቤት ስም በባንኩ የተመሰከረለት (CPO) ወይም በጥሬ ገንዘብ ከጨረታው ኦርጅናል ሰነድ ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
- ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሰነድ በሰም የታሸገ ኤንቨሎፕ በማድረግ በግልጽ በመፃፍ በአንድ (1) አንድ ኮፒና (1) ኦርጂናል በመለየት ለዚህ ጨረታ በተዘጋጀ ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለበት፡፡
- በጥቃቅንና አነስተኛ የተደራጁ ማህበራት ከሆኑ በመንግስት የግዢ መመሪያ መሰረት ይበረታታል፡፡
- ጨረታው የሚከፈተው ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ16ኛው የሥራ ቀን ከጠዋቱ በ 4፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዚህ ዕለት በ4፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው እና ታዛቢዎች በተገኙበት በቡሌ ሆራ ከተማ አስተዳደር ጽ/ቤት ይከፈታል፡፡
- የጨረታ አሸናፊ ማሸነፉ በጽሁፍ ከተገለፀበት ቀን ጀምሮ በ10 ቀን ውስጥ የጨረታ ውል ማስከበሪያ ያሸነፈበትን ጠቅላላ ዋጋ 10% በባንክ በተመሰከረ በባንክ በተመሰረተ (CPO) ወይም ጥሬ ገንዘብ በማስያዝ ከመስሪያ ቤቱ ጋር መፈራረም አለበት፡፡
- አሸናፊው እንዲታወቅ ለጨረታ ማስከበሪያ ያስያዙት ገንዘብ ለተሸናፊዎች ወዲያውኑ የሚመለስ ይሆናል።
- ያሸነፉትን እቃዎች በራሱ ትራንስፖርት እስከ መስሪያ ቤቱ ግምጃ ቤት ማምጣት እና ፈርኒቸር እቃዎችን በራሱ ወጪ መገጣጠም የሚችል፡፡
- ተጫራቾቹ በጨረታ አከፋፈት ስነ-ስርዓት ላይ ካልተገኙ ፖስታው አይከፈትም፡፡
- የመልካም ስራ አፈፃፀም መረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ በሕግ የተጠበቀ ነው፡፡
ለተጨማሪ መረጃ ስልክ ቁጥር፡- 046-443-06-12 / 09-19-98-65-61/09-16-83-58-39
የቡሌ ሆራ ከተማ አስተዳደር ገንዘብ ጽ/ቤት
