Tender Detail

Tender Details


በጅማ ዞን የነዲ ጊቤ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ለተለያዩ ሴክተር መ/ቤቶች ለ2018 በጀት ዓመት አገልግሎት የሚውሉ ከዚህ በታች የተዘረዘሩ ዕቃዎችን በግልጽ ጨረታ አወደድሮ ለመግዛት ስለሚፈልግ የንግዱ ማኅበረሰብ መወዳደር የምትችሉ መሆኑን እንገልፃለን፡፡

በኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት በጅማ ዞን የነዲ ጊቤ ገንዘብ ጽ/ቤት


                                                                           የጨረታ ማስታወቂያ 

በጅማ ዞን የነዲ ጊቤ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ለተለያዩ ሴክተር መ/ቤቶች ለ2018 በጀት ዓመት አገልግሎት የሚውሉ ከዚህ በታች የተዘረዘሩ ዕቃዎችን በግልጽ ጨረታ አወደድሮ ለመግዛት ስለሚፈልግ የንግዱ ማኅበረሰብ መወዳደር የምትችሉ መሆኑን እንገልፃለን፡፡ የዕቃው ዓይነት፡-

  1.  ኤሌክትሮኒክስ ዕቃ 

  2. የጽሕፈት መሳሪያ 

  3. የተለያዩ ፈርኒቸሮች የቢሮ ውስጥ ዕቃዎች 

  4. የመኪና እና የሞተር ጎማ 

  5. የሠራተኞች የደንብ ልብስ 

  6. የተለያዩ ሞተር ሳይክል 

  7. የግንባታ ዕቃዎች

       መስፈርቶች፡- 

  1. የሚገዙትን ዕቃዎች እስከ ወረዳው ዋና ከተማ ማቅረብ የሚችል 

  2. የንግድ ፍቃድ በቀጥታ በተወዳደሩበት አርእስት ላይ በአቅራቢዎች የተመዘገቡበት (TIN) ያላቸው 

  3. ተወዳደሪ የVAT(15%) የተመዘገበ መሆንና የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችል 

  4. የንግድ ፊቃድ በቀጥታ በተወዳደረበት አርእስት ላይ ያለው የ2018 የሥራ ዘመን የታደሰ ፍቃድ ያለው የደረጃ ሀ አቅራቢዎች ከገቢዎች ቢሮ ደብዳቤ ማቅረብ የሚችል 

  5. ተጫራቾቾ ተወዳድረው ያለፉበትን ዕቃ ለማቅረብ ዋስ ማቅረብ የሚችሉ 

  6. ተወዳዳሪዎች የሚያቀርቡት ሰነድ ላይ የቀረበው ዋጋ ስርዝ ድልዝ የሌለበት እና የሚቀርበው ዋጋ ከታክስ ውጭ መሆን ይኖርበታል በተጨማሪ አስፈላጊውን ፎርማሊቲ ያሟሉ መሆን አለባቸው፡፡

  7. ከ100,000 ብር በላይ ለሚገዛው ዕቃ VAT ተመዝጋቢ መሆን አለበት ፡፡ 

  8. የባንክ አካውንት ቁጥር አሳውቆን ከፍያ በባንክ እንዲሆን ፍቃደኛ የሆነ፡፡ 

  9. የተዘጋጀውን ሰነድ በነዲ ግቤ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ከ14/12/2017 ቀን ጀምሮ የማይመለስ 200(ሁለት መቶ) ብር በመክፈል መግዛት የምትችሉ መሆኑን እናሳውቃለን ። 

  10. ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለı5 የሥራ ቀናት በአየር ላይ ቆይቶ በ16ኛው የሥራ ቀን ከጠዋቱ 3፡00 ሰዓት ጀምሮ ተወዳዳሪዎች እስከ 6፡00 ሰዓትድረስ ሰነዳቸውን በታሸገ ሁለት ኤንቨሎፕ ኦሪጅናልና ኮፒ በተዘጋጀ ሳጥን በማስገባት ከቀኑ 8፡00 ላይ ተወዳዳሪዎች ፣ታዛቢዎች እና የወረዳው የጨረታ ኮሚቴዎች በተገኙበት በግልጽ ይከፈታል፡፡ 

  11. የጨረታ ማስከበሪያ (CPO) 10,000(አስር ሺህ) ብር በፖስታ አሽጎ ከኦሪጅናል ሰነድ ጋር አያይዞ ማቅረብ የሚችል፣ 

  12. በተጫራች ድርጅቶች ለውድድር የሚላኩ ሰዎች የውክልና ሕጋዊ ሰነድ ያላቸው መሆን አለባቸው፡፡ 

  13. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው። ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር-0910761402 /0913125308/0917898014/ 

                                                  በኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት በጅማ ዞን የነዲ ጊቤ ገንዘብ ጽ/ቤት

Save Tender