Tender Detail

Tender Details


የሽመልስ ሃብቴ አንደኛና መካከለኛ ደረጃ ት/ቤት በ2018 ዓ.ም የጽህፈት እቃዎችን፣ የፅዳት እቃዎችን፣ የደንብ ልብስ፣ የስፖርት እቃዎች፣ የኤሌክትሮኒክስ እቃዎች፣ የህንፃ መሳሪያዎች፣ የህፃናት ዴኬር እቃዎች፣ ቋሚ እቃዎች፣ የህትመት ስራዎች፣ የጥገና ስራዎች፣ የሜዳ እድሳት ስራ እና የጥበቃ ቤት እድሳት ስራ በመስኩ የተሰማሩ ነጋዴዎች ባለሙያዎችን አወዳድሮ በግልፅ ጨረታ መግዛትና ማሰራት ይፈልጋል፡፡

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በቂርቆስ ክ/ከተማ የሽመልስ ሃብቴ አንደኛና መካከለኛ ደረጃ ት/ቤት


 

ብሔራዊ ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ የጨረታ ቁጥር 01/2017

 

የሽመልስ ሃብቴ አንደኛና መካከለኛ ደረጃ ት/ቤት በ2018 ዓ.ም የጽህፈት እቃዎችን፣ የፅዳት እቃዎችን፣ የደንብ ልብስ፣ የስፖርት እቃዎች፣ የኤሌክትሮኒክስ እቃዎች፣ የህንፃ መሳሪያዎች፣ የህፃናት ዴኬር እቃዎች፣ ቋሚ እቃዎች፣ የህትመት ስራዎች፣ የጥገና ስራዎች፣ የሜዳ እድሳት ስራ እና የጥበቃ ቤት እድሳት ስራ በመስኩ የተሰማሩ ነጋዴዎች ባለሙያዎችን አወዳድሮ በግልፅ ጨረታ መግዛትና ማሰራት ይፈልጋል፡፡

 

ተ.ቁ

የሎት ዓይነት

ማስያዣ (C.P.O)

1

ለሎት 1 የጽህፈት እቃዎች ፣ ለሎት 2 የጽዳት እቃዎች

1500.00

2

ለሎት 3 የደንብ ልብስ እቃዎች

1000.00

3

ለሎት 4 የስፖርት እቃዎች፣ ለሎት 5 የኤሌክትሪክ እቃዎች፣ ለሎት 6 የህንፃ መሳሪያዎች

1000.00

4

ለሎት 7 ቋሚ እቃዎች

2000.00

5

ለሎት 8 ለህጻናት ዴኬር እቃዎች

500.0

6

ለሎት 9 የጥገና ስራዎች

2500.00

7

ለሎት 10 የህትመት ስራዎች

500.00

 

ተጫራቾች ማሟላት የሚገባቸው መስፈርቶች፡-

  • ተጫራቾች ለጨረታ ሲመጡ የዘመኑን የታደሰ ንግድ ፍቃድ ያለው፣ የተሰማሩበት የስራ መስክ፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር እና በምታስገቡት ሰነድ ላይ በእያንዳንዱ ፔጅ ላይ የድርጅቱን ክብ ማህተም ማድረግ ይኖርባችኋል። ከሌላችሁ ብትወዳደሩም መስሪያ ቤቱ ውድቅ የሚያደርግ መሆኑን ከወዲሁ እናሳውቃለን።
  • በተጠቀሰው እሴት ታክስ ተመዝጋቢ መሆናቸውን የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ እና የጨረታ ሰርተፍኬት ያለው።
  • ናሙና ለሚያስፈልጋቸው እቃዎች የጨረታ ሰነድ የሚያስገቡበት ወቅት ናሙና ማቅረብ አለባቸው። ናሙና ካላቀረበ ውድቅ የምናደርግ መሆኑን እንገልጻለን፡፡
  • እቃዎቹን በመ/ቤቱ የግዥ የስራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 4 ድረስ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
  • ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ10 ተከታታይ የስራ ቀናት ዘወትር በስራ ሰዓት ብር 250.00 (ሁለት መቶ ሃምሳ ብር) በመክፈል መውሰድ ይችላሉ።
  • የጨረታ ማወዳደሪያ የአንዱ ዋጋ /ቫት/ ተጨማሪ እሴት ታክስን ያካተተ መሆን አለበት።
  • ቫትን ያላካተተ ከሆነ ቫት እንዳካተተ ይቆጠርበታል።
  • አሸናፊው ተጫራች ማሸነፉ በተረጋገጠ በ7 ቀን ውል መፈፀምና 10% የውል ማስከበሪያ በባንክ የተረጋገጠ CPO ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡

ተጫራቾች ሰነዳቸውን ዋናውንና ኮፒውን በታሸገው ኤንቨሎፕ በማድረግ ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት በ10ኛው ቀን እስከ 11፡00 ሰዓት ድረስ ለዚሁ ተብሎ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል። በዛው እለት በ11፡00 ሰዓት ተዘግቶ በሚቀጥለው ቀን በ4፡00 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡

መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

አድራሻ፡- ከላንድማርክ ሆስፒታል አጠገብ ቂ/ክ/ከ/አስ ሽመልስ ሃብቴ 1ኛ እና መካከለኛ ደረጃ ት/ቤት

ስልክ ቁጥር 011 5 57 45 36/ 011 5 51 94 13

 

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በቂርቆስ ክ/ከተማ የሽመልስ ሃብቴ አንደኛና መካከለኛ ደረጃ ት/ቤት

 

Save Tender