በኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ ወረዳ 10 መሰረተ ዕድገት ቅድመ አንደኛ አንደኛና መካከለኛ ደረጃ ት/ቤት በ2018 በጀት ዓመት ለመሥሪያ ቤቱ ሥራ አገልግሎት የሚውሉ ዕቃዎችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
በኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ ወረዳ 10 መሰረተ ዕድገት ቅድመ አንደኛ አንደኛና መካከለኛ ደረጃ ት/ቤት
የጨረታ ማስታወቂያ
በኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ ወረዳ 10 መሰረተ ዕድገት ቅድመ አንደኛ አንደኛና መካከለኛ ደረጃ ት/ቤት በ2018 በጀት ዓመት ለመሥሪያ ቤቱ ሥራ አገልግሎት የሚውሉ ዕቃዎችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ በመሆኑም ከዚህ በታች የተጠቀሱትን መስፈቶች የምታሟሉ ተጫራቾች በጨረታው እንድትሳተፉ ጥሪ እናቀርባለን።
|
የሎት ቁጥር |
የአገልግሎት ዓይነት |
መያዝ ያለበት የጨረታ ማስከበሪያ |
የሎት ቁጥር |
የአገልግሎት ዓይነት |
መያዝ ያለበት የጨረታ ማስከበሪያ |
|
ሎት1 |
/6211/ የደንብ ልብስ |
8000 |
ሎት 8 |
/6313/ የኤሌክትሪክ ቋሚ ዕቃዎች |
8000 |
|
ሎት2 |
/6212/ አላቂ የትምህርት ዕቃዎች |
8000 |
ሎት 9 |
/6314/ ሌሎች ቋሚ ዕቃዎች |
8000 |
|
ሎት3 |
/6215/ አላቂ የትምህርት ዕቃዎች |
8000 |
ሎት 10 |
/6323/ መጽሐፍት |
5000 |
|
ሎት4 |
/6213/ የህትመት ሥራዎች |
4000 |
ሎት 11 |
/6323/ የላብራቶሪ ዕቃዎች |
5000 |
|
ሎት5 |
/6214/ የህክምና ዕቃዎች |
4000 |
ሎት 12 |
/6219/ ልዩ ልዩ |
5000 |
|
ሎት6 |
/6218/ አላቂ የፅዳት ዕቃዎች |
7000 |
ሎት 13 |
/6243/ የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች ጥገና |
8000 |
|
ሎት7 |
/6244/ የጥገና ዕቃዎች |
8000 |
|
|
|
- ተጫራቾች እግባብነት ያለው በመስኩ የተሰማሩበት ሕጋዊ የታደሰ ንግድ ፈቃድ ያላቸውና ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች የዘመኑን ግብር የከፈሉ እንዲሁም የገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ሚኒስቴር ባወጣው በዕቃ አቅራቢዎች ዝርዝር ለመመዝገባቸው የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉና በገቢዎችና ጉምሩክ ባለስልጣን ተጨማሪ እሴት ታክስ ከፋይነት የተመዘገቡ መሆን ይኖርባቸዋል፡፡ ቫት ተመዝጋቢ እና የቲን መለያ ቁጥር ያላቸውና ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች የተደራጁ ጥቃቅንና አነስተኛ ከሆኑ ካደራጃቸው አካል ወቅታዊና ህጋዊ የሆነ የድጋፍ ደብዳቤ በት/ቤቱ ስም በቅድሚያ ማፃፍ አለባቸው፡፡ እንዲሁም የጨረታ ማስከበሪያ የዋስትና ደብዳቤ በት/ቤቱ ስም በትክክለኛ አድራሻ ካደራጃቸው አካላት ማፃፍ አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ10 ተከታታይ የስራ ቀናት ዘወትር በሥራ ሰዓት በኮ/ቀ/ክ/ከተማ ወረዳ 10 መሰረተ ዕድገት ቅ/አ/አ/መ/ደ/ት/ቤት በአካል በመገኘት የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 200 (ሁለት መቶ ብር ብቻ) በመክፈል የጨረታውን ሰነድ መውሰድ ይችላሉ።
- ማንኛውም ተጫራች በሰነዱ ላይ ናሙና እንዲቀርብባቸው ለሚጠየቁ ዕቃዎች ጨረታው ከመከፈቱ በፊት ናሙና ማቅረብ አለበት፡፡
- ተጫራቾች እያንዳንዱን ዋጋ ከነቫቱ በመግለፅ ፊርማና ማህተም እና አድራሻቸውን በመጥቀስ በታሸገ ፖስታ ዋናውን እና ኮፒውን በ2 ፖስታ በማድረግ ሙሉ አድራሻቸውንና የጨረታውን አይነት በመጥቀስ የጨረታ ሰነዱን ከነመመሪያው በመሰረተ ዕድገት ቅ/አ/አ/መ/ደ/ት/ቤት በግዥ ቢሮ በመገኘት በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ገቢ ማድረግ አለባቸው፡፡
- እያንዳንዱ ተጫራች የመወዳደሪያ ዋጋ ሰነድ ስልጣን ባለው አካል የተፈረመበትና የተሟላ አድራሻን የሚገልፅ ማህተም ያረፈበት መሆን አለበት፡፡
- ጨረታው ጋዜጣ ላይ በወጣ በ11ኛው ተከታታይ የስራ ቀን ከቀኑ 4፡00 ሰዓት ታሽጎ በዛው ቀን 4፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸውና ታዛቢዎች በተገኙበት መሰረተ ዕድገት ቅ/አ/አ/መ/ደ/ት ቤት ይከፈታል፡፡ ይህ ቀን የበዓል ቀን ከሆነ በቀጣይ የሥራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ተዘግቶ በተመሳሳይ ሰዓት ይከፈታል፡፡
- አሸናፊው እንደታወቀ ያሸነፈበትን ጠቅላላ ዋጋ 10% የውል ማስከበሪያ በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡ አሸናፊው ከተገለፀበት ቀን ጀምሮ ባሉት 7 የስራ ቀናት በአካል ቀርቦ ውል ካልተፈራረመ ለጨረታው ያስያዘው ገንዘብ ለመንግሥት ገቢ ይሆናል፡፡
- በዚህ ጨረታ ላይ የሚቀርብ ማንኛውም የመወዳደሪያ ዋጋ ቢያንስ ለ60 ቀናት ፀንቶ የሚቆይ መሆን ይኖርበታል፡፡
- አንድ ተጫራች ሌላው በሰጠው ዋጋ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ አይችልም፡፡
- የጨረታ መዝጊያ ዕለትና ሰዓት ካለፈ በኋላ የሚቀርብ ማንኛውም ሰነድ ተቀባይነት የለውም፡፡
- ት/ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
- ለጥቃቅንና አነስተኞች የግዥ መመሪያው በሚፈቅደው መሰረት ልዩ አስተያየት ይደረግላቸዋል፡፡
አድራሻ፡- ከጦርኃይሎች ወደ ኮልፌ በሚወስደው መንገድ ከሆላንድ ኤምባሲ ከፍ ብሎ
ስልክ፡- 0913346653/0921313443
በኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ ወረዳ 10 መሰረተ ዕድገት ቅድመ አንደኛ፣ አንደኛና መካከለኛ ደረጃ ት/ቤት
