በደቡብ ኢ/ክ መንግሥት የጋርዱላ ዞን ፋይናንስ መምሪያ በ2018 በጀት ዓመት ከደን ሽያጭ በተገኘ ገንዘብ በጋርዱላ ደን ውስጥ ለውስጥ መንገድ ለማስከፈት የግሬደር ጎማ ግዥ እና የዶዘር ማሸን ኪራይ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት የጋርዱላ ዞን ፋይናንስ መምሪያ
የጨረታ ማስታወቂያ
በደቡብ ኢ/ክ መንግሥት የጋርዱላ ዞን ፋይናንስ መምሪያ በ2018 በጀት ዓመት ከደን ሽያጭ በተገኘ ገንዘብ በጋርዱላ ደን ውስጥ ለውስጥ መንገድ ለማስከፈት፡-
- የግሬደር ጎማ ግዥ እና
- የዶዘር ማሸን ኪራይ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
ስለዚህ
- በዘርፉ የታደሰ የንግድ ስራ ፍቃድና የንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት ያላቸው።
- የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ተመዝጋቢ የሆነ፣
- የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር Tin No ያላቸው፤
- የአቅራቢነት ምዝገባ የምስክር ወረቀት ያላቸው፤
- የጨረታ ማስከበሪያ የግሬደር ጎማ ግዥ 16,000 /አስራ ስድስት ሺህ ብር/ የዶዘር ማሽን ኪራይ 30,000 /ሰላሳ ሺህ ብር/ ከታወቀ ባንክ የሚሰጥ የተረጋገጠ ሲፒኦ ወይም የባንክ ዋስትና ለ90 /ዘጠና ቀናት የሚቆይ ማቅረብ የሚችሉ፤
- ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ ከጋርዱላ ዞን ገቢዎች ጽ/ቤት በመቅረብ የማይመለስ 200 /ሁለት መቶ ብር/ በመክፈል መግዛት አለባቸው።
- ተጫራቾች የገዙትን ሰነድ ኦርጅናልና ኮፒ በማዘጋጀት በሁለት የተለያዩ ፖስታ በማሸግ ኦርጅናሉ ላይ አርጅናል ኮፒው ላይ ኮፒ ብሎ በመፃፍ ፊርማና ማህተም በማሳረፍ በዚህ ጋዜጣ ከታወጀበት ቀን ጀምሮ በ16 ተከታታይ ቀናት ወስጥ ለዚሁ ጨረታ በተዘጋጀ የጨረታ ሣጥን ውስጥ እስከ 16ኛው ቀን ከረፋዱ 4፡00 ሰዓት ማስገባት አለባቸው። 16ኛው ቀን መደበኛ የሥራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ይገባል፡፡
- ጨረታው በዕለቱ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በጋርዱላ ዞን ፋይናንስ መምሪያ ግዥ ከፍል ከረፋዱ 4፡30 ሰዓት ላይ ይከፈታል፡፡
- ተጫራቾች ወይም ወኪሎቻቸው በሰዓቱ ያለመገኘት የጨረውን አከፋፈት እያስተጓጉልም፤
- ጨረታዎቹ አሸናፊዎች ተለይተው ከተገለፀላቸው ከ7 ተከታታይ የሥራ ቀናት በኋላ ከባድ ችግር ካልተፈጠረ በስተቀር በ5 ተከታታይ ቀናት ውስጥ አሸናፊዎች የውል ማስከበሪያ በማስያዝ ውል መግባት አለባቸው፡፡ ተሸናፊዎች ደግሞ ያስያዙትን የጨረታ ማስከበሪያ መውሰድ ይችላሉ፡፡
- የግሬደር ጎማ ግዥ አሸናፊ የሚያቀርቡትን ጎማ እስከ ጋርዱላ ዞን ፋይናንስ መምሪያ መጋዘን ድረስ ማቅረብ አለበት የዶዘር ማሽን ኪራይ አሸናፊ እስከ መንገድ ከፈታ ቦታ ድረስ ዶዘሩን ማድረስና ሥራውን በገባው ውል መሠረት መሥራት አለበት፤
- የዶዘር ማሽን ኪራይ አሸናፊ የዶዘሩን የዘይት ሰርቪስና ጥገና ወጭ በራሱ ይሸፈናል፡፡
- መምሪያው የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ለበለጠ መረጃ ስልክ ቁጥር፡- 0467740344 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ።
በደቡብ ኢ/ክ መንግሥት የጋርዱላ ዞን ፋይናንስ መምሪያ
