በኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት የአዳማ ከተማ አስተዳደር ገንዘብ ጽ/ቤት በከተማው መስተዳድር _ ሥር _ ለሚገኙ ሴክተር መ/ቤቶች የጽሕፈት መሣሪያዎች፣ የጽዳት እቃዎች፣ መጋረጃዎች፣ የኤሌክትሮኒክስ እቃዎች፣ ቋሚ የቢሮ እቃዎች፣ ለተለያዩ ተሽከርካሪዎች ጎማዎች እና የተለያዩ ችግኞችን በ2018 በጀት ዓመት በዘርፉ ከተሰማሩ አቅራቢዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
ጨረታ ማስታወቂያ
በኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት የአዳማ ከተማ አስተዳደር ገንዘብ ጽ/ቤት በከተማው መስተዳድር _ ሥር _ ለሚገኙ ሴክተር መ/ቤቶች የጽሕፈት መሣሪያዎች፣ የጽዳት እቃዎች፣ መጋረጃዎች፣ የኤሌክትሮኒክስ እቃዎች፣ ቋሚ የቢሮ እቃዎች፣ ለተለያዩ ተሽከርካሪዎች ጎማዎች እና የተለያዩ ችግኞችን በ2018 በጀት ዓመት በዘርፉ ከተሰማሩ አቅራቢዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
በመሆኑም በጨረታው ስመሳተፍ፡-
-
ተጫራቾች በዘርፉ ሕጋዊ የንግድ ሥራ ፍቃድ ያላቸው፣ የዘመኑን ግብር የከፈሉና፣ የዘመኑን ግብር ከፍለው ማጠናቀቃቸውንና፤ ጨረታ ላይ እንዲሳተፉ የሚል ማስረጃ ከሀገር ውስጥ ገቢ ባለሥልጣን ጽ/ቤት ማቅረብ አለባቸው፡፡
-
የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT ) ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፤
-
ተጫራቾች ለእያንዳንዱ የጨረታ ሰነድ የማይመለስ 500.00 (አምስት መቶ ብር) በጽ/ቤቱ ስም ሲንቄ ባንክ በሂሳብ ቁጥር 1054551161211 ላይ ገቢ በማድረግ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ዕለት ጀምሮ ለı5 ተከታታይ የሥራ ቀናት በጽ/ቤቱ የግዢ የሥራ ሂደት ቢሮ ድረስ በመቅረብ ሰነዱን መግዛት ይችላሉ፡፡
-
የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (TIN No.) የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፤
-
በአቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ የተመዘገቡና የምስክር ወረቀት ያላቸው፤
-
ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ የተጠቀሱትን ማስረጃዎች ኦሪጅናልና ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
-
ተጫራቾች ለሚያቀርቡት የጨረታ ዋጋ ለእያንዳንዱ ማስከበሪያ CPO ብር 50,000.00 (ሃምሳ ሺ ብር) ሲሆን በጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዝ ለተደራጁ የትኛውንም የዋስትና ደብዳቤ የማንቀበል መሆኑን በጥብቅ እናሳስባለን፡፡
-
ተጫራቾች ሰነዳቸውን ቴከኒካል እና ፋይናንሻል ኮፒና ኦርጂናሉን ለየብቻው አለበት፡፡ ቴክኒካሉን ያለፉት ተወዳዳሪዎች ፋይናንሻላቸው ይከፈታል፡፡
-
ጨረታው የሚከፈተው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት በ16ኛው የሥራ ቀን ከሆነ በ4፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዛው ቀን በ4:30 ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው ቢገኙም ባይገኙም በአዳማ ከተማ ገንዘብ/ጽ/ቤት ሦስተኛ ፎቅ ግዢ ክፍል ውስጥ ይከፈታል፡፡ ዕለቱ በዓል ወይም መ/ቤቱ ዝግ ከሆነ በቀጣዩ የሥራ ቀን በተጠቀሰው ሰዓት ጨረታው ይከፈታል፡፡
-
ማንኛውም የጽሕፈት መሣሪያዎች የፅዳት እቃዎችና መጋረጃ ተወዳዳሪዎች ሳንፕል ወይም ናሙና ማቅረብ አለባቸው፡፡ ቋሚ የቢሮ እቃዎችን ተወዳዳሪዎች መሸጫ ቦታችሁ የሚታይ ሲሆን የተለያዩ ችግኞችን ለማቅረብ የምትወዳደሩ ተወዳዳሪዎች የችግኝ ማፊያ ቦታ ያላችሁ እና ከአዳማ ከተማ ርቀቱ ከ200 ኪ.ሜ ያልበለጠ መሆኑን እና የማፊያ ቦታውን በአካል ተገኝተን የምናይ መሆኑን እናሳውቃለን፡፡
-
የጨረታው አሸናፊ ዕቃዎቹን እስከ አዳማ ከተማ ገንዘብ ጽ/ቤት መጋዘን ድረስ በራሱ ወጪ አጓጉዘው ማቅረብ አለበት፡፡
-
የጨረታው አሸናፊ በጨረታ መመሪያ በተሰጠው መሠረት የጨረታ አሸናፊነቱ በውስጥ ማስታወቂያና በስልክ እንደተገለፀ በio ተከታታይ ቀናት ውስጥ አስፈላጊውን የጨረታ ውል ከአዳማ ከተማ ገንዘብ ጽ/ቤት ጋር መፈራረም አለበት:: ይህ ባይፈፀም የጨረታ አሸናፊነቱን በመሰረዝ ለጨረታ ማስከበሪያ ያስያዘው ገንዘብ ገቢ ይሆናል፡፡
-
ማንኛውም ተጫራች ለውድድር የሚቀርበው ቫት ተጠቃሚ ሲሆን ፣ 7.5 % በክፍያ ጊዜ የሚቀነስ ይሆናል፡፡
-
መስሪያ ቤቱ ከሚያደርገው የግዢ ውል 20 ፐርሰንት መጨመር ወይም መቀነስ የሚችል መሆኑን ተጫራቹ መገንዘብ አለበት፤
-
መሥሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡ ሰበስጠ መረጃ ስልክ ቁጥር 022-211-14-42 ደውሎ መጠየቅ ይቻላል፡፡
በኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የአዳማ ከተማ አስተዳደር ገንዘብ ጽ/ቤት
