Tender Detail

Tender Details


በአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ የወረዳ 12 ፋይናንስ ጽ/ቤት በጨረታ ቁጥር 01/218 መሰረት ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን እቃዎች አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡

በአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ወረዳ 12 ፋይናንስ ጽ/ቤት


                                                       ግልጽ  ጨረታ ማስታወቂያ

በአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ የወረዳ 12 ፋይናንስ ጽ/ቤት በጨረታ ቁጥር 01/218 መሰረት ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን እቃዎች አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡

 ሎት 1.የደንብ ልብሶች 

 ሎት 2.የጽዳት እቃዎች  

ሎት 3.አላቂ የጽህፈት መሳሪያዎች 

ሎት 4.አላቂ የቢሮ እቃዎች 

ሎት 5. የመኪና ጎማ

 ሎት 6. የሰራተኞች ካፍቴሪያ አገልግሎት

 በዚህም መሰረት መወዳደር የሚፈልግ ማንኛውም ህጋዊ ተጫራች ከዚህ በታቶ የተዘረዘሩትን መስፈርቶች ማሟላት ይኖርበታል። 

  1.  በዘርፉ የተሰማራችሁ ተጫራቾች የዘመኑን የታደሰ ህጋዊ ንግድ ስራ ፍቃድ ፧ የአቅራቢነት የምስክር ወረቀት የተጨማሪ እሴት ታክስ ክፍያ ሰርተፍኬት ፤የቲን መለያ ቁጥር ሰርተፍኬት ኮፒ ከዋጋ ማቅረቢያ ጋር ማያያዝ ይኖርባቸዋል። 

  2. የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 200፡00 /ሁለት መቶ ብር/ በመክፈል ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ የስራ ቀናት ከ2፡30 ሰዓት -1፡30 በአቃቂ ቃሊቲ ክ/ከተማ በወረዳ 12 ፋይናንስ ጽ/ቤት 3ኛ ፎቅ ላይ ቢሮ ቁጥር 3-03 የጨረታ ሰነድ መግዛት ይቻላል፡፡

  3. .የጨረታ ማስከበሪያ ከሚጫረቱበት ጠቅላላ ዋጋ 2% (ሁለት ፐርሰንት) በባንክ የተመሰከረለት ቼክ /ሲፒኦ/ ማስያዝ አለባቸው።እንዲሁም የጨረታ አሸናፊ ማስታወቂያ መሆናቸው ሲታወቅ 10% የውለታ ማስከበሪያ ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡ 

  4. ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን ዋጋ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ ኮፒና ዋናውን ጨረታው ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 10 ቀን ድረስ ባሉት የስራ ቀናት በቢሮው በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡ 

  5. ተጫራቾች የሚያቀርቡትን ዕቃ ናሙና ጨረታው ከመከፈቱ በፊት ማቅረብ ግዴታ ይኖርባቸዋል፡፡ 

  6.  ጨረታው በ10ኛው ቀን ከቀኑ 11፡30 ተዘግቶ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ወይም ባልተገኙበት በጠኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ይከፈታል፡፡ 

  7. ተጫራቾች አሸናፊ መሆናቸው እንደተገለጸላቸው በሰባት /7/ ቀናት ውስጥ ቀርቦ ውል _ __ መፈጸም እና ውለታ ከፈጸመበት እለት አንስቶ በአምስት/5/ቀናት ውስጥ እቃዎችን በሙሉ ማስረከብ ይኖርባቸዋል። 

  8. በዚህ ጨረታ መመሪያ ያልተካተቱ ሌሎች ሁኔታዎች በሀገሪቱ ህግና ደንብ እንዲሁም በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የእቃ ግዥ አፈጻጸም መመሪያ ቁጥር 3/2002 መሰረት የሚታይ ይሆናል። መስሪያ ቤቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡                                           አድራሻ፡- አቃቂ ቃሊቲ ገላን ኮንደሚኒየም ባስ እስቴሽን ወረድ ብሎ ዳዊት ህንፃ                                                                                               ለተጨማሪ መረጃ ፡-በስልክ ቁጥር 0900046299/0910887122 በመደወል ማግኘት ይቻላል። 

                                                                 በአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ወረዳ 12 ፋይናንስ ጽ/ቤት

Save Tender