በኦሮሚያ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን የኩዩ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት በ2018 ዓ/ም በጀት በስሩ ላሉት ሴክተር መ/ቤቶች የጽህፈት መሣሪያ፣ የጽዳት እቃዎችን፣ ቐሚ የቢሮ ዕቃዎችን፣ የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎችን፣ የተለያዩ የመኪና ጎማዎች እና የሰራተኞች ደንብ ልብስ ዕቃዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
በሰሜን ሸዋ ዞን የኩዩ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት
የጨረታ ማስታወቂያ
በኦሮሚያ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን የኩዩ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት በ2018 ዓ/ም በጀት በስሩ ላሉት ሴክተር መ/ቤቶች የጽህፈት መሣሪያ፣ የጽዳት እቃዎችን፣ ቐሚ የቢሮ ዕቃዎችን፣ የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎችን፣ የተለያዩ የመኪና ጎማዎች እና የሰራተኞች ደንብ ልብስ ዕቃዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
ስለዚህ በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች
- በዚህ ዘርፍ የንግድ ፍቃድ ያለው የ2017/2018 የታደሰ የንግድ ፍቃድና የዘመኑን ግብር የከፈለ እና የገንዘብ ሚኒስቴር ባወጣው የዕቃ አቅራቢዎች ዝርዝር የተመዘገበበትን ማስረጃ ማቅረብ የሚችል።
- አሸናፊው ድርጅት ጨረታውን ካሸነፈበት ቀን ጀምሮ በአስር ቀን ውስጥ ያሸነፋቸውን ዕቃዎች በሙሉ ኩዩ ወረዳ ገ/ጽ/ቤት ማቅረብ የሚችል።
- ተጫራቾች ዝርዝር የጨረታ ሰነድ የያዘ ጋዜጣው ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 15ኛው ቀን በስራ ሰዓት እስከ 11፡30 ድረስ ብቻ የማይመለስ ብር 700 (ሰባት መቶ ብር ) በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ቁጥር 1000036504416 በመክፈል የባንክ ስሊፕ በማምጣት ኩዩ ወረዳ ገቢዎች ቢሮ በማወራረድ ሰነዱን ከኩዩ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 2 መግዛት ይችላሉ።
- ተጫራቾች እያንዳንዱን ዕቃ የሚሸጡበትን ዋጋ የያዘ ዝርዝር የዋጋ ሰነድ በፖስታ በማሸግ ጋዜጣ ከወጣበት በ16ኛው ቀን እስከ 8:00 ሰዓት ብቻ የጨረታ ማስከበሪያ ብር 15000/ አስራ አምስት ሺህ / ብር ወይም ሲፒኦ በባንክ የተረጋገጠ በማስያዝ ለዚሁ በተዘጋጀው ሣጥን ማስገባት አለበት።
- ጨረታው በ16ኛው ቀን በ8፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በወረዳው ገንዘብ ጽ/ቤት ይከፈታል፡፡ ተጫራቾች ባይገኙም ጨረታውን ከመክፈት አያግደውም።
- በሌላ ሰው ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ አይቻልም።
- ተጫራቾች ለሙያቸው ማረጋገጫ የስራ ልምድ እና የምስጋና ደብዳቤ ቢያቀርቡ ይመረጣል።
- መ/ቤቱ ሌላ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊል ወይም በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
- ለተጨማሪ ማብራሪያ በስልክ ቁጥር 0935 971 038 / 0911 775 600 በመደወል መጠየቅ ይቻላል
በሰሜን ሸዋ ዞን የኩዩ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት
