Tender Detail

Tender Details


በኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት በጅማ ዞን የሠቃ ጨቆርሳ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት በ 2018 ዓ.ም በወረዳው ውስጥ ላሉ ባለበጀት መስሪያ ቤቶች የሚያገለግሉ የጥራት ደረጃቸው በኢትዮጵያ ደረጃ መዳቢዎች የተረጋገጠ የምስክር ወረቀት ያላቸው በቅርብ ዓመታት ውስጥ የተመረቱ ዕቃዎችን የሰራተኞች የደንብ ልብስ፣ የጽ/ቤት አላቂ ዕቃዎች ፤ የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች ፤ የተሽከርካሪ ጎማዎችን እና የሁለት እግር የሞተር ሳይክሎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።

በኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት በጅማ ዞን የሠቃ ጨቆርሳ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት


ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

በኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት በጅማ ዞን የሠቃ ጨቆርሳ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት በ 2018 ዓ.ም በወረዳው ውስጥ ላሉ ባለበጀት መስሪያ ቤቶች የሚያገለግሉ የጥራት ደረጃቸው በኢትዮጵያ ደረጃ መዳቢዎች የተረጋገጠ የምስክር ወረቀት ያላቸው በቅርብ ዓመታት ውስጥ የተመረቱ ዕቃዎችን የሰራተኞች የደንብ ልብስ፣ የጽ/ቤት አላቂ ዕቃዎች ፤ የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች ፤ የተሽከርካሪ ጎማዎችን እና የሁለት እግር የሞተር ሳይክሎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።

በዚሁ መሰረት ማናቸውም በንግድ ስራ ዘርፍ የተሰማሩ፣ ህጋዊ የስራ ፈቃድ ያላቸውና ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የሚያሟሉ እንዲወዳደሩ እንጋብዛለን፡፡

1. ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፣ የንግድ ፈቃዳቸውን ያሳደሱ፣ የዘመኑን ግብር የከፈሉና ዋናና ቅጂ መረጃ አያይዘው ማቅረብ የሚችሉ ፡፡

2. ተወዳዳሪዎች በአቅራቢዎች ዝርዝር ላይ የተመዘገቡበትን መረጃ ማቅረብ የሚችሉ ::

3.ተወዳዳሪዎች የተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) ተመዝጋቢ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ መረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡

4. የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ በተመሰረተ ቼክ CPO 50,000 (ሀምሳ ሺህ ብር) በታሸገ ፖስታ ማቅረብ የሚችሉ ::

5. ጠቅላላ ተወዳዳሪዎች በኦሮሚያ ክልላዊ መንግስትና በፌዴራል መንግስት የተደነገገውን የግዥ ሕግ የሚያከብሩ መሆን አለባቸው፡፡

6. በኢትዮጵያ ደረጃ መዳቢዎች የተረጋገጠ ዕቃ ስለመሆኑ መረጃ ማቅረብ የሚችሉ ::

7. ተወዳዳሪዎች የጨረታ ሰነድ ከተከፈተ በኋላ በሰነዱ ላይ ባቀረቡት የመወዳደሪያ ሀሳብ ላይ ለውጥ፣ ማሻሻያ ማድረግ ወይም ከጨረታ መውጣት አይችሉም::

8. ተወዳዳሪዎች በጨረታ ላይ መግለጫ _ ወይም የማሻሻያ ጥያቄ ካላቸው በተመዘገቡ በአምስት ቀን (5) ውስጥ ማቅረብ ይችላሉ፡፡

9. ተወዳዳሪዎች ባቀረቡት መወዳደሪያ ሰነድ ላይ ስም፤ ፊርማ፤ የድርጅቱን ማህተም እና አድራሻ መጥቀስ አለባቸው::

10. የጨረታውን ሰነድ በሠቃ ጨቆርሳ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ቁጥር 7 የማይመለስ 200 (ሁለት መቶ ብር) በመከፈል መግዛት ይቻላል፡፡

11. ተወዳዳሪዎች ጨረታውን ለማሰናከል ከሞከሩ ከጨረታው ውጭ ይሆናሉ ለወደፊትም በሠቃ ጨቆርሳ ወረዳ በሚካሄደው በመንግስት የግዥ ጨረታ አይሳተፉም:: ለጨረታ ማስከበሪያ ያስያዙት ገንዘብም አይመለስም::

12. ይህ ጨረታ ለ 15 (አስራ አምስት) ተከታታይ የመንግስት የስራ ቀን በአየር ላይየሚውል ሲሆን የጨረታ ሰነዱ ሽያጭ ከ12/12/2017-3/13/2017 የሚከናወን ይሆናል፡፡

13. የጨረታ አሸናፊ ድርጅት ያሸነፈውን ዕቃ በራሱ ትራንስፖርት አጓጉዞ እስከ ጽ/ቤቱ ድረስ ማቅረብ ይኖርበታል፡፡

14. መስሪያ ቤቱ እንደአስፈላጊነቱ 20% ጨምሮ ወይም ቀንሶ መግዛት ይችላል፡፡

15. የተሰረዘ፣ የተደለዘ የተፋፋቀ ወይም በግልጽ የማይነበብ የጨረታ ሰነድ ተቀባይነት አይኖረውም፡፡

16. ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን ዋጋ መስሪያ ቤቱ ባዘጋጀው የጨረታ ሰነድ ላይበመሙላት ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡

17. የጨረታው ሰነድ አቅራቢ ድርጅቶች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በ16ኛው የመንግስት የስራ ቀን 2:30 ሰዓት ታሽጎ በዚሁ ቀን 4፡00 ሰዓት ላይይከፈታል ፡፡

18. በዚህ የጨረታ ማስታወቂያ ያልተካተቱ መስፈርቶች በዋና የጨረታ ሰነድ ላይ ያሉ መሆናቸውን እንገልፃለን ፡፡

19. የቴክኒክ እና ፋይናንሻል ሰነዶች ኦሪጅናል እና ኮፒ በተለያየ ፖስታዎች በማሸግ በአንድ ጥቅል እሽግ መቅረብ ይኖርበታል ፡፡

20. ግዥ የሚፈጽመው አካል የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በጥቅል የመሰረዝ መብት አለው፡፡

በኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት በጅማ ዞን የሠቃ ጨቆርሳ

ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት

 

Save Tender