በአራዳ ክ/ከተማ ወረዳ 01 ስር የሚገኘው የአፍሪካ አንድነት ቁ.1 አጸደ ህጻናትና የመጀ/ደ/ት/ቤት ልዩ ቦታው አትክልት ተራ ሲሆን በ2018 ዓ.ም የደንብ ልብስ አላቂ የት/ት እቃ፡ የህክምና እቃ፤ አላቂ የት/ት እቃ፣ የጽዳት እቃ፤ ዝቅተኛ ቋሚ እቃ፤ ፕላንትና ማሽነሪ፣ ህንጻና ቁሳቁስ እና የተለያዩ የጥገና ስራዎች በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳዳር ትምህርት ቢሮ የአፍሪካ አንድነት ቁ1 አፀደ ሕፃናት የመጀመሪያ ደረጃ ት/ቤት
ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር 01
በአራዳ ክ/ከተማ ወረዳ 01 ስር የሚገኘው የአፍሪካ አንድነት ቁ.1 አጸደ ህጻናትና የመጀ/ደ/ት/ቤት ልዩ ቦታው አትክልት ተራ ሲሆን በ2018 ዓ.ም የደንብ ልብስ አላቂ የት/ት እቃ፣ የህክምና እቃ፤ አላቂ የት/ት እቃ፣ የጽዳት እቃ፤ ዝቅተኛ ቋሚ እቃ፤ ፕላንትና ማሽነሪ፣ ህንጻና ቁሳቁስ እና የተለያዩ የጥገና ስራዎች በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡ በዚህም መሰረት በጨረታዉ መካፈል የምትፈልጉ ተጫራቾች የሚከተሉትን ሁኔታዎች በቅድሚያ ማሟላት ይኖርባችኋል፡፡
- በተሰማሩበት የስራ መስክ ንግድ ፍቃድ ያላቸውን የዘመኑን ግብር የከፈሉ መሆናቸውን በተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ ለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡
- የመንግስት ግዢ ኤጀንሲ የንግድ ምዝገባ ያላቸውና በአቅራቢነት ዝርዝር ውስጥ የተመዘገቡ፡፡
- የመንግስት ጨረታ ላይ ለመሳተፍ ጊዜው ያላለፈበት ማስረጃ በ2018 ዓ./ም የታደሰ የንግድ ፈቃድ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- ከላይ የተጠቀሱትን የእቃዎች ዝርዝር የሚያሳውቅና የግዢ መመሪያ የያዘ ሰነድ የማይመለስ ብር 100 (አንድ መቶ) በመክፈል ይህ ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በአፍሪካ አንድነት ቁ.1 አጸደ ህጻናትና የመጀ/ደ/ት/ቤት በስራ ሰአት በመገኘት የጨረታ ሰነዱን መግዛት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዶቻቸውን ዝርዝር የያዘ ሰነድ ከነዋጋው ጋዜጣው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ በት/ቤቱ ፋ/ግ/ን/አስ/ደ/የስ/ሂደት ቢሮ ቁጥር 01 በስራ ሰአት ማቅረብ አለባቸው።
- ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ የሚያገለግል የሚጫረቱበት የእቃ ዋጋዎች 2% በት/ቤቱ ስም የተዘጋጀ ሲፒኦ ወይም በት/ቤቱ ፋይናንስ በጥሬ ገንዘብ በማሲያዝ ማረጋገጫዉን ከመወዳደሪያ ሰነዶቻቸዉ ጋር ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች አንዱ ባስገባው ዋጋ ተንተርሶ መስጠት አይችልም፡፡
- ተጫራቾች ናሙና ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ11ኛዉ ቀን በ 4:00 ሰአት ታሽጎ በዛዉ እለት 4፡30 ሰዓት ላይ በአፍሪካ አንድነት ቁ.1 አጸደ ህጻናትና የመጀ/ደ/ት/ቤት ቤተ መጽሀፍት ውስጥ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ባሉበት ይከፈታል፡፡
- ተጫራቾች የገዙትን ሰነድ ኦሪጅናል እና ኮፒ ማህተም በማድረግ በሰም በታሸገ ካኪ ፖስታ ማቅረብ አለባቸው።
- ት/ቤቱ የተሻለ የግዥ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል መሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ለተጨማሪ ማብራሪያ በስልክ ቁጥር 0110570295/96 መደወል ይችላሉ።
በአራዳ ክ/ከተማ ት/ቢሮ አፍሪካ አንድነት ቁ.1 አፀደ ሕፃናትና የመ/ደ/ት/ቤት
