የጅማ ከተማ ገንዘብ ጽ/ቤት በ2018 በጀት ዓመት በጅማ ከተማ መስተዳደር ስር ለሚገኙ መሥሪያ ቤቶች እና ለጅማ ከተማ ማዘጋጃ ቤት አገልግሎት የሚውል ከዚህ በታች በዝርዝር የተቀመጡትን ዕቃዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
በኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥት የጅማ ከተማ ገንዘብ ጽ/ቤት
ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
የጅማ ከተማ ገንዘብ ጽ/ቤት በ2018 በጀት ዓመት በጅማ ከተማ መስተዳደር ስር ለሚገኙ መሥሪያ ቤቶች እና ለጅማ ከተማ ማዘጋጃ ቤት አገልግሎት የሚውል፤
- የጽሕፈት መሣሪያ፤
- የኤሌክትሮኒክስ መሣሪያ፤
- የጽዳት መሣሪያ እና
- የቢሮ እቃዎችን (Furniture) በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
ስለዚህ፡-
- በተጠቀሱት የእቃ አይነቶች ሕጋዊ ፈቃድ ያላቸው የዘመኑን ግብር የከፈሉና የንግድ ፈቃዳቸውን ያሳደሱና የታደሰውን ንግድ ፈቃድ ማቅረብ የሚችሉ
- ተጫራቾች የአቅራቢነት ምዝገባ ምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ
- የተጨማሪ እሴት ታክስ ሲፒኦ ተመዝጋቢ የሆኑና ለዚህም መረጃ ማቅረብ የሚችሉ እና ለጨረታው ማስከበሪያ 100,000 (አንድ መቶ ሺህ) ብር ሲፒኦ በጅማ ከተማ ገንዘብ ጽ/ቤት ስም አሠርተው ከጨረታው ሰነድ ጋር ማቅረብ አለባቸው (ለእያንዳንዱ)፡፡
- TIN እና VAT ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ እና TAX clearance ማቅረብ የሚችሉ
- ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ ፋይንሻልና ቴክኒካሉን ኦርጂናሉንና ኮፒውን በመለየት በኤንቨሎፕ ታሽጎ ይህ ጨረታ ከወጣበት ቀን ጀምሮ 15 የሥራ ቀናት ለጨረታው በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ዘወትር በሥራ ሰዓት ማስገባት ይችላሉ፡፡
- ጨረታው የሚከፈተው በጋዜጣ ከወጣበት ዕለት ጀምሮ በ15ተኛው ቀን ሲሆን ይህ ቀን የሥራ ቀን ካልሆነ ቀጥሎ ባለው የመንግሥት ሥራ ቀን 8፡30 ሰዓት ታሽጎ በዚሁ ቀን 9፡00 ሰዓት ላይ ይከፈታል፡፡
- የጨረታው አሸናፊ ንብረቱን በራሱ ትራንስፖርት በጅማ ከተማ ገንዘብ ጽ/ቤት መጋዘን (where house) ገቢ አድርጎ ገንዘቡን ይቀበላል፡፡
- ጽሕፈት ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
አድራሻ-
የጅማ ከተማ ገንዘብ ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 8 አባ ጂፋር አደባባይ ጅማ ከተማ መስተዳደር ቅጥር ግቢ
Jimma city Administration yard, Finance Office Building, Ground Floor
ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር 0472114408 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ፡፡
በኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥት የጅማ ከተማ ገንዘብ ጽ/ቤት
