Tender Detail

Tender Details

  • Company Hibret Insurance Company S.C. (ሕብረት ኢንሹራንስ አ.ማ)
  • Address ቴዎድሮስ አደባባይ በሚገኘው ሕብረት ኢንሹራንስ ሕንፃ ዋና መ/ቤት 9ኛ ፎቅ : አዲስ አበባ ፡ ኢትዮጵያ, Phone: +251111263434
  • Websitehttps://www.hibretinsurance.com/
  • Deadline22 Aug 2025, 12:00 AM
  • magazineሪፖርተር
  • Bid Document PriceNot stated in the notice
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening date2025-08-22 00:00:00
  • Categories Land, House, Building And Warehouse Rent

ሕብረት ኢንሹራንስ ኩባንያ አደጋ ደርሶባቸው ለደንበኛቹ ካሣ ከፍሎ ለተረከባቸው የተለያዩ መኪናዎች፣ የመኪና ቅሪት አካሎች እና ሌሎችን ብረቶች ለማስቀመጥ የሚውል መጋዘን ያለው ቦታ በጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።

Hibret Insurance Company S.C. (ሕብረት ኢንሹራንስ አ.ማ)


 

ሕብረት ኢንሹራንስ

HIBRET INSURANCE

HIBR/BID/25-26-010

የመጋዘን ግዥ ጨረታ

 

ሕብረት ኢንሹራንስ ኩባንያ አደጋ ደርሶባቸው ለደንበኛቹ ካሣ ከፍሎ ለተረከባቸው የተለያዩ መኪናዎች፣ የመኪና ቅሪት አካሎች እና ሌሎችን ብረቶች ለማስቀመጥ የሚውል መጋዘን ያለው ቦታ በጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።

በዚሁ መሰረት ከዚህ በታች የተገለፁትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾ በጨረታው እንዲሳተፉ ተጋብዘዋል።

  1. ቦታው በአዲስ አበባ መስተዳደር ውስጥ የሚገኝ መሆን ይኖርበታል።
  2. ተጫራቾች ለመሸጥ የሚያቀርቡት ቦታ ስፋቱ ከ5,000 ካ.ሜትር እና ከዛ በላይ ስፋት ያለው መሆን አለበት::
  3. ለሽያጭ የቀረበው ቦታ ለመሸጥ የሚያስችል የግንባታ ስራ የተከናወነለት መሆን አለበት።
  4. ቦታው ከባድና ቀላል ተሽከርካሪ ለማቆም የሚያስችል መሆን አለበት።
  5. ቦታው ስም ለማዛዋወር የሚያስችል በቂ ሰነድ ያለው መሆን አለበት።
  6. ቦታው ከባንክ ብድር ውጪ ከማንኛውም ዕዳና እገዳ ነፃ መሆን አለበት።
  7. ቦታው ቀላልና ይሁን ከባድ መኪና ሊያስገባ የሚችል መንገድ መሆን አለበት።
  8. የውሃና የመብራት መሰረተ ልማት የተሟላለት መሆን አለበት።

በመሆኑም ከላይ የተጠቀሱትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎች ስለጨረታው የሚያስረዳውን ሰነድ ቴዎድሮስ አደባባይ ከሚገኘው ዋና መሥሪያ ቤት ሕንፃ ዘጠነኛ ፎቅ የስው ሃብትና ንብረት አስተዳደር ቢሮ ከነሐሴ 5 ቀን 2017 ዓ.ም እስከ ነሐሴ 22 ቀን 2017 ዓ.ም ከጠዋቱ 2፡00 እስከ ቀኑ 10፡30 ድረስ በመውሰድ ለዚሁ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ በማስገባት መወዳደር ይችላሉ።

ተጫራቾች የቴክኒካል እና የመሸጫ ዋጋ የሚገልፁትን ስነዶቻቸውን ለየብቻ በተዘጋጀ ፖስታ አሽገው ማቅረብ ይኖርባቸዋል።

ጨረታው ነሐሴ 22 ቀን 2017 ዓ.ም ከጠዋቱ 3፡00 ሰዓት ተዘግቶ 4፡00 ሰዓት ላይ በኩባንያው ዋና መሥሪያ ቤት ሕንፃ ላይ 11ኛ ፎቅ በሚገኘው መሰብሰቢያ አዳራሽ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል።

ኩባንያው የጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር 0111 26 34 34 የውስጥ መስመር 207/190 መጠየቅ ይቻላል።

 

 

Save Tender