Tender Detail

Tender Details


የኦሮሚያ ህብረት ሥራ ባንክ ሲገለገልባቸው የነበሩ ያገለገሉ የማስታወቂያ ወረቀቶች እና እንዲሁም ሳይጠቀምባቸው የቀሩ አዳዲስ የህትመት ወረቀቶች፤ የጽህፈት መሳሪያዎች፣ የመኪና ጎማዎች፤ ራክ ካቢኔቶች፣ የማስታወቂያ ቦርዶች፣ የተለያዩ አላቂ እና ቋሚ ንብረቶችን ባሉበት ሁኔታ በጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡


 

የሽያጭ ጨረታ ማስታወቂያ

(ቁጥር WS-01/2025/26)

 

የኦሮሚያ ህብረት ሥራ ባንክ ሲገለገልባቸው የነበሩ ያገለገሉ የማስታወቂያ ወረቀቶች እና እንዲሁም ሳይጠቀምባቸው የቀሩ አዳዲስ የህትመት ወረቀቶች፤ የጽህፈት መሳሪያዎች፣ የመኪና ጎማዎች፤ ራክ ካቢኔቶች፣ የማስታወቂያ ቦርዶች፣ የተለያዩ አላቂ እና ቋሚ ንብረቶችን ባሉበት ሁኔታ በጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ ለመግዛት ለሚፈልጉ ተጫራቾች፡-

  1. የዕቃዎቹ ዓይነትና ዝርዝር በጨረታው ሰነድ ላይ የሚገኝ በመሆኑ ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ነሐሴ 4 ቀን 2017 ዓ.ም ጀምሮ እስከ ነሐሴ 19 ቀን 2017 ዓ.ም 8፡00 ሰዓት ድረስ የግብር ከፋይ ምዝገባ ሰርተፊኬት ወይም የግብር መለያ ቁጥር(TIN) ያላችሁ ተጫራቾች የዊንጌት መንገድ መድሃኒአለም ት/ቤት አካባቢ የባንኩ ህንጻ ላይ በሚገኘው የኦሮሚያ ህብረት ሥራ ባንክ ጉለሌ ቅርንጫፍ ወይም በአቅራቢያዎ በሚገኝ የባንኩ ቅርንጫፍ በመሄድ ላገለገሉ እና አዳዲስ ዕቃዎች ጨረታ ሰነድ መግዣ ብር 200.00 (ሁለት መቶ) በሂሳብ ቁጥር ETB1446500010001 በማስገባት ደረሰኙን በመያዝ የጨረታ ሰነዱን የባንኩ ህንጻ ላይ በሚገኘው ጉለሌ ቅርንጫፍ ባለበት 1ኛ ፎቅ ላይ ከባንኩ ዋና የዕቃ አቅርቦት ቢሮ መውሰድ ይችላሉ፡፡
  2. የዕቃዎቹን ዓይነትና ዝርዝር ሁኔታ በአካል ማየት ለሚፈልጉ ተጫራቾች የከፈሉበትን ስሊፕ እና የጨረታ ሰነዱን በመያዝ ፣ የኦሮሚያ ህብረት ሥራ ባንክ ከጉለሌ ቅርንጫፍ ጀርባ የባንኩ ቅጥር ግቢ ውስጥ በሚገኘው ግምጃ ቤት ውስጥ በመገኘት የጨረታ ሰነዱን የገዙ ተጫራቾች ብቻ በተቀመጠው ፕሮግራም መሠረት ነሐሴ 12 እስከ ነሐሴ 16 ቀን 2017 ዓ.ም ከጧቱ 3፡00 ሰዓት እስከ 10፡00 ሰዓት ድረስ እንዲሁም ነሐሴ 19 ቀን 2017 ዓ.ም ከጧቱ 3፡00 ሰዓት እስከ 6፡00 ሰዓት ድረስ መጎብኘት ይችላሉ፡፡
  3. ገዢዎች የሚገዙበትን ዋጋ በታሸገ ኤንቬሎፕ እስከ ጨረታ መዝጊያ ነሃሴ 19 ቀን 2017 ዓ.ም 8፡00 ሰዓት ድረስ በጉለሌ በሚገኘው ሰነድ የገዙበት ዋና የዕቃ አቅርቦት ቢሮ በአካል ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸውን በመላክ ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሣጥን ውስጥ በማስገባት መጫረት ይችላሉ፡፡
  4. የሚጫረቱበትን ንብረት የጠቅላላ መነሻ ዋጋ 10% (አስር በመቶ) ውን በባንክ ክፍያ ማዘዣ (CPO) የጨረታ ማስከበሪያ ማስያዝ ይኖርባችኋል፤ በተጨማሪም የጨረታ መነሻ ዋጋ ለሌላቸው የሚገዙበትን ጠቅላላ ዋጋ 10% ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
  5. ተጫራቾች የሚጫረቱበትን ዋጋ ተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) 15% በተጨማሪነት መኖር አለመኖሩን በግልፅ በሰነዱ ላይ በፅሁፍ መግለፅ ይኖርባችዋል። ካልሆነ ተጫራቾች ያቀረቡት ዋጋ ባንኩ ከነ ተጨማሪ እሴት ታክስ ጋር እንደቀረበ ታሳቢ ያደርጋል።
  6. የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ሳይያያዝ የሚቀርብ የጨረታ ሰነድ ተቀባይነት የለውም።
  7. አሸናፊ መሆናቸው የተገለፀላቸው ተጫራቾች ያሸነፉትን ንብረት አሽናፊነታቸው ከተገለጸበት ቀን ጀምሮ ሙሉ ክፍያውን በአምስት ቀናት ውስጥ ከፍለው ማንሳት ይኖርባቸዋል፤ ካልሆነ ግን ለጨረታ ማስከበሪያ ያስያዙት ሲፒኦ ውርስ ይደረጋል።
  8. ጨረታው ሰኞ ነሐሴ 19 ቀን 2017 ዓ.ም በ8፡00 ሰዓት ላይ ተዘግቶ በዛው ዕለት ከቀኑ 8፡30 ሰዓት ላይ ጉለሌ በሚገኘው የባንኩ ህንጻ 1ኛ ፎቅ ዋና የዕቃ አቅርቦት ቢሮ ውስጥ ተጫራቾች በተገኙበት የጨረታ ሰነዱ የሚከፈት መሆኑን እንገልፃለን።
  9. ባንኩ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

የኦሮሚያ ኅብረት ሥራ ባንክ (አ.ማ)

ስልክ ቁጥር +251115542352

ፖ.ሣ.ቁ 16936

ማህበረሰብን ማጎልበት፣ ህይወትን መለወጥ!

 

Save Tender