በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን የቤቶችና ሕንጻዎች አስተዳደር ልማት ድርጅት የቤተ ክርስቲያኗ ንብረት የሆኑትን ለቢሮ የሚሆኑ ቤቶችን በጨረታ አወዳድሮ ማከራየት ይፈልጋል።
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የቤቶችና ሕንጻዎች አስተዳደር ልማት ድርጅት
የንግድ ቤትና መጋዘን የኪራይ ጨረታ ማስታወቂያ
- በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን የቤቶችና ሕንጻዎች አስተዳደር ልማት ድርጅት የቤተ ክርስቲያኗ ንብረት የሆኑትን ለቢሮ የሚሆኑ ቤቶችን በጨረታ አወዳድሮ ማከራየት ይፈልጋል።
- በቂርቆስ ክፍለ ከተማ ወረዳ 7 የቤት ቁጥር 356 G+1 አሥራ ስምንት ክፍል የሆነ ቤት፤
- በልደታ ክፍለ ከተማ ወረዳ 10 መጋዘን ቁጥር 4፤
- መንግሥታዊ ድርጅት ካልሆነ በስተቀር ማንኛውም ተወዳዳሪ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን እምነት ተከታይ ሆኖ ከሚገለገልበት ደብር የድጋፍ ደብዳቤና የአባልነት መታወቂያ ማቅረብ የሚችል፤
- ተጫራች በጨረታው አሸናፊ ሆኖ ቤቱን ከተረከበ በኋላ የውሃና የመብራት ፍጆታ ራሱ ይከፍላል።
- ድርጅቱ ለኪራይ ያቀረበውን ቢሮ በጨረታ ተወዳድሮ ለመከራየት የሚፈልግ ማንኛውም ሰው ወይም ድርጅት ይሀ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ የሥራ ቀናት ውስጥ ከጠዋቱ 2፡30 እስከ 10፡00 ክፍሉን በአካል ቀርቦ በማየት ለዚሁ የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 500.00 (አምስት መቶ ብር) ከፍሎ ገዝቶ በሞሉት በታሸገ ኢንቨሎፕ በድርጅቱ ጽ/ቤት በተዘጋጀው ሳጥን ማስገባት አለበት።
- ተጫራቾች ነጋዴ ከሆኑ የታደሰ ንግድ ፈቃድና የዘመኑ ግብር የተከፈለበት ደረሰኝ፣ ኢንቨስተር ከሆነ የኢንቨስትመንት ፈቃድ፣ የንግድ ማኅበር ከሆነ የመመስረቻ ጽሑፍ፣ የሙያ አገልግሎት ሰጪ ከሆነ የሙያ ፈቃዱን ፎቶ ኮፒ ከዋጋ ማቅረቢያ ስነዱ ጋር ማቅረብ ይኖርበታል።
- ተጫራቾች በጥቅልም ሆነ በተናጥል ሲወዳደሩ የሚጫረቱበት ክፍል የጨረታ ማስከበሪያ ሲፒኦ ብር 5000.00 በማስያዝ የጨረታ ማስበሪያ ዋስትና ለእያንዳንዳቸው በባንክ በተረጋገጠ ቼክ (CPO) ከሚያቀርቡ የጨረታ ሰነድ ዋጋ ጋር ዋናውን በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
- ጨረታው በ10ኛው ቀን ከቀኑ 10፡00 ተዘግቶ በማግስቱ በዓል ከሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎች በተገኙበት ከጠዋቱ በ3፡00 ሰዓት በድርጅቱ ጽ/ቤት ይከፈታል፡፡
- ድርጅቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊል ወይም በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
- የጨረታ መነሻ ዋጋ እና ዝርዝር መመሪያ ከጨረታው ሰነድ ላይ ማግኘት ይቻላል።
- ቤቶቹን ከፋፍሎ ለሦስተኛ ወገን ማስተላለፍ አይቻልም።
ለበለጠ መረጃ
በስ.ቁ. 0911-78-86-98 ወይም በድርጅቱ ጽ/ቤት በአካል ቀርበው ይጠይቁ
