የኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥት በምሥራቅ ሐረርጌ ዞን መስተዳድር የኮምቦልቻ ወረዳ የገንዘብ ጽ/ቤት በወረዳው በስሩ ለሚገኙ መ/ቤቶች በ2018 በጀት ዓመት የጽሕፈት መሣሪያ እቃዎች፣ የፅዳት እቃዎች፣ ቋሚ ዕቃዎችን፣ የግንባታ እቃዎችን፣ የኤሌክትሮኒክስ እቃዎች፣ የመኪና እና የሞተር ሳይክል ጎማ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
የኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥት በምሥራቅ ሐረርጌ ዞን መስተዳድር የኮምቦልቻ ወረዳ የገንዘብ ጽ/ቤት
ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
ቁጥር WMAK- BMA-2018-001
የኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥት በምሥራቅ ሐረርጌ ዞን መስተዳድር የኮምቦልቻ ወረዳ የገንዘብ ጽ/ቤት በወረዳው በስሩ ለሚገኙ መ/ቤቶች በ2018 በጀት ዓመት የጽሕፈት መሣሪያ እቃዎች፣ የፅዳት እቃዎች፣ ቋሚ ዕቃዎችን፣ የግንባታ እቃዎችን፣ የኤሌክትሮኒክስ እቃዎች፣ የመኪና እና የሞተር ሳይክል ጎማ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
- ተጫራቾች በአቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ የተመዘገቡበትን ማስረጃ ማቅረብ አለባቸው።
- ተጫራቾች ዕቃዎቹን ለማቅረብ የሚያስችል ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፤ የዘመኑን ግብር የከፈሉ/ያደሱ መሆን አለባቸው።
- የተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) የተመዘገበ እና ሰርተፊኬት ማቅረብ የሚችል።
- የጨረታው ማስከበሪያ ብር 200,000 (ሁለት መቶ ሺህ ብር) በባንክ የተረጋገጠ (ሲፒኦ) በኮምቦልቻ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ስም አሠርቶ ማቅረብ የሚችል።
- ተጫራቾች ከማንኛውም የሙስና ወንጀልና ኪራይ ሰብሳቢነት ነፃ መሆን አለባቸው።
- የጨረታው አሸናፊ ያሸነፋቸውን ዕቃዎች በተባለበት ቦታ ማድረስ የሚችልና ያሸነፋቸውን ዕቃዎች በሚፈለገው አቅም ያለው መሆን አለበት።
- ተጫራቾች የጨረታውን ሠነድ ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ የሥራ ቀናት የማይመለስ ብር 500 (አምስት መቶ ብር) በመክፈል ከምስ/ሐ/መስ/የኮምቦልቻ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 8 መግዛት ይችላሉ።
- ተጫራቾች የጨረታውን ሠነድ ዋናውና ኮፒ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
- ጨረታው ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት በ16ኛው ቀን በ3፡30 ሰዓት ተዘግቶ በዕለቱ በ4፡00 ሰዓት ተጫራቾች እና ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በይፋ ይከፈታል።
- እቃዎቹ በኢትዮጵያ ማቴሪያል ስታንዳርድ የተረጋገጠ መሆን እንዳለበት ተጫራቾች ማወቅ አለባቸው፤ በዚህ ያልተረጋገጠ እቃ ካላቀረቡ መ/ቤቱ እንደማይቀበል ማወቅ አለባቸው፡፡
- መ/ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በመሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር 0915766840/0915042915 በስራ ሰአት ደውለው ወይም በአካል ቀርበው መረዳት ይችላሉ።
የኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥት በምሥራቅ ሐረርጌ ዞን መስተዳድር የኮምቦልቻ ወረዳ የገንዘብ ጽ/ቤት
