መ/ቤታችን የኢትዮጵያ ስታቲስቲክስ አገልግሎት በ2017 በጀት ዓመት ከዚህ በታች በሠንጠረዥ የተመለከቱትን ከመንግሥት በተፈቀደለት በጀትና የግዥ ዘዴ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
የኢትዮጵያ ስታቲስቲክስ አገልግሎት ሐረር ቅ/ጽ/ቤት
ለ2ኛ ጊዜ የወጣ ብሔራዊ ግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር፡- ማስኤ/ግጨ/002/2017
መ/ቤታችን በ2017 በጀት ዓመት ከዚህ በታች በሠንጠረዥ የተመለከቱትን ከመንግሥት በተፈቀደለት በጀትና የግዥ ዘዴ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
|
ተ.ቁ |
የግዥው ዓይነት መግለጫ |
የጨረታ ሠነድ መግዥያ ዋጋ (የማይመለስ) |
የጨረታ ማስከበሪያ ሲፒኦ ወይም የባንከ ዋስትና መጠን በብር |
|
1 |
የቢሮ ኪራይ ጨረታ |
100.00 |
5,000.00 |
በመሆኑም ተጫራቾች፡-
- የጨረታ ሰነዱን የኢትዮጵያ ስታቲስቲክስ አገልግሎት ሀረር ጽ/ቤት ግዥና ፋይናንስ አስተዳደር በመምጣት 100 ብር ከፍለው መውሰድ ይችላሉ፡፡
- ባለቤትነት ይዞታ ማረጋገጫ ሰነድ እሴት ታክስ ሰርተፊኬት ፣ የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር ሰርተፊኬት /TIN NO/ እና በጨረታ ላይ ለመሳተፍ የሚያስችል ጨረታ ከመከፈቱ በፊት የተሰጠ የታክስ ክሊራንስ ሰርተፊኬት ከመጫረቻ ሰነዳቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ፡፡
- በኢትዮጵያ ስታቲስቲክስ አገልግሎት ሀረር ቅ/ጽ/ቤት ስም የተዘጋጀ፣ በቅድመ ሁኔታ ያልተገደበ የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና የባንክ ጋራንቲ ወይም CPO ብር 5000.00 ከመጫረቻ ሠነድ ጋር ተያይዞ መቅረብ ይኖርበታል።
- ተጫራቾች የሚጫረቱበት በአገልግሎት ግዥ ለተጫራቾች በሚሸጠው የጨረታ ሰነድ ክፍል 6 ላይ ከተመለከተው የቴክኒክ ፍላጎት ጋር መጣጣም ይኖርበታል።
- ሠነዳቸውን አንድ ኦሪጅናልና አንድ ኮፒ ለየብቻው በታሸገ ኤንቨሎፕ በማድረግ እስከ ነሀሴ 26 ቀን 2017 ዓ.ም ለዚሁ ተብሎ በተዘጋጀው ሣጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው፡፡ ጨረታው በዚሁ ቀን 8፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዚሁ ዕለት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በሚገኙበት ከቀኑ 8፡30 ሰዓት በሀረር ቅጽ/ቤት ቅጽር ጊቢ ውስጥ ቢሮ ቁጥር 8 ይከፈታል፡፡
- መሥሪያ ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ ለመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
አድራሻ
ስልክ 0256660691/0913745963/0912806409
የኢትዮጵያ ስታቲስቲክስ አገልግሎት
