Tender Detail

Tender Details


የአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ወረዳ 12 አስተዳደር ፋይናንስ ጽ/ቤት ከዚህ በታች በዝርዝር የተቀመጡትን ነገሮች በጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።

አዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ወረዳ 12 ፋይናንስ ፅ/ቤት


 

1ኛ ዙር የግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር፡-

አ/ከ/ክ/ከ/ወረዳ 12 ፋይናንስ ግዢ ዋ/ስ/ሂ/የጨ/ቁ-001/2018

 

የአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ወረዳ 12 አስተዳደር ፋይናንስ ጽ/ቤት በ2018 በጀት አመት 1ኛ ዙር ለሚያከናውነው አጠቃላይ የአላቂ እቃ እንዲሁም አገልግሎት ግዥ የዝግጅት ምእራፉን አጠናቆ ከዚህ በታች በተዘረዘሩት የእቃና አገልግሎት ግዥ መደቦች ላይ ተቋሙ ያስቀመጠውን መስፈርት የሚያሟሉ ተጫራቾችን ለውድድር ይጋብዛል፡፡

ሎት 1 የፅህፈት መሳሪያና አላቂ እቃዎች                                       СРО (2%)

ሎት 2 የፅዳት እቃዎች                                                                СРО (2%)

ሎት 3 የደንብ ልብስ                                                                   СРО (2%)

ሎት 4. ቋሚ እቃዎች                                                                  СРО (2%)

ሎት 5. የዲኮር ስራ                                                СРО 5000.00 ብር

ሎት 6. የትራንስፖርት አገልግሎት                                СРО 5000.00 ብር

ሎት 7. የህትመት ስራዎች                                        СРО 5000.00 ብር

ሎት 8. የስፖርት መገልገያ እቃዎች                                              СРО 5000.00 ብር

ሎት 9. ኤሌክትሮኒክስ ጥገና                                      СРО 5000.00 ብር

ሎት 10. ፈርኒቸር ጥገና                                          СРО 5000.00 ብር

ሎት 1. የግብርና ግብአት እቃዎች                                 СРО 5000.00 ብር

ሎት 12 መስተንግዶ አገልግሎት                                  СРО 5000.00 ብር

መስሪያ ቤታችን ከላይ በተገለፀው የግዥ መደብ መጫረት የሚፈልግ ማንኛውም ህጋዊ ተጫራች ወይም አቅራቢን አወዳድሮ ግዥውን ለመፈፀም ይፈልጋል፡፡ በመሆኑም ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የምታሟሉ ተጫራቾች መወዳደር የምትችሉ መሆኑን እናሳውቃለን፡፡

  1. ህጋዊ የታደሰ የንግድ ስራ ፈቃድና የንግድ ምዝገባ ሰርተፊኬት ያለው፤
  2. የቫት ተመዝጋቢነት ማስረጃና የአቅራቢነት ምዝገባ ሰርተፊኬት ያለው፤
  3. የዘመኑን ግብር የከፈለበት ክሊራንስና ህጋዊ የግብር ከፋይነት ምዝገባ ሰርተፊኬት ያለው፤
  4. የጨረታ ሰነዱ ሙሉ እያንዳንዱ ገፅ ተሞልቶ ተፈርሞ ማህተም ተደርጎበት ስርዝ ድልዝ ሳይኖረው መመለስ አለበት /ይህን ሳያደርግ የጨረታ ሰነዱን የሚመልስ ነጋዴ ከጨረታው ውድድር ውጪ እንደሚሆኑ እናሳውቃለን።

ከላይ ከተራ ቁጥር 1-4 የተጠቀሱትን መስፈርቶች የምታሟሉ አቅራቢዎች ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ የስራ ቀናት ኮልፌ አጠና ተራ መናፈሻ ፊት ለፊት የተቋሙ ህንፃ 1ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 101 በሚገኘው ፋይናንስ ፅ/ቤት በግንባር በመቅረብ የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ 200.00 ብር (ለአንድ ሎት) በመክፈል መግዛት የምትችሉ መሆኑን እየገለፅን ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያነት የሚያገለግል ከላይ በተገለፀው መሰረት ከሎት 1-4 የሚያቀርቡትን እቃ ጠቅላላ ዋጋ 2% እንዲሁም ከሎት 5-11 ደግሞ 5000.00 /አምስት ሺ ብር/ ህጋዊ CPO በተቋማችን ስም አሰርተው ከጨረታው ሰነድ ጋር ማቅረብ አለባቸው እንዲሁም አሸናፊ ተጫራቾች ውል ከመዋዋላቸው በፊት ያሸነፉትን እቃ ጠቅላላ ዋጋ 10% በድርጅታችን ስም ህጋዊ CPO በማሰራት ለጨረታ ውል ማስከበሪያነት ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡ ተጫራቾች ለሚወዳደሩበት እቃዎች ሳምፕል ማቅረብ ይኖርባቸዋል፤ እንዲሁም የጨረታ ሰነዱን ሙሉውን በታሸገ ፖስታ ኦሪጅናልና ኮፒ ብለው በጨረታ ሰነዱ ላይ በተጫራች የሚሞላውን ክፍል በጠቅላላ ሞልተው ፈርመው ማህተም አድርገው የጨረታ መቀበያ ቀነ ገደቡ ሳያልፍ ለዚሁ ስራ ተብሎ በፅ/ቤቱ ግዥ ክፍል በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡ ተጫራቾች ያሸነፉትን ንብረት የመጠቀሚያ ግዜው ቢያንስ 1 አመትና ከዛ በላይ የሆነ እና በሳምፕሉ መሰረት አድርገው ወረዳው ንብረት ክፍል ድረስ በራሳቸው ወጪ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡

በተጨማሪም ለጥቃቅንና አነስተኛ ተወዳዳሪዎች የጨረታ ማስከበሪያ አስተያየት የምናደርገው ለሚያመርቱት ምርት ብቻ እሱንም በደብዳቤ የምናስተናግድ መሆኑን እንገልፃለን፡፡ ጨረታው ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ የስራ ቀናት አየር ላይ ውሎ በ11ኛው ቀን ከጠዋቱ በ4፡00 ሰአት ታሽጎ በዛው ቀን ከጠዋቱ 4፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት የሚከፈት መሆኑን በትህትና እንገልፃለን፡፡

ማሳሰቢያ ፡- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡ ጨረታው የሚከፈትበት ቀን በዓል ወይም እረፍት ከሆነ በተከታዩ የስራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት የሚከፈት መሆኑን በትህትና እንገልፃለን፡፡

አድራሻ፡- ኮልፌ አጠና ተራ ኮልፌ ፓርክ ፊት ለፊት ወይም ቁጠባ ሰፈር ጀርባ ወደ ፊሊጶስ ቤተክርስቲያን/ሎሚ ሜዳ በሚወስደው መንገድ 200ሜ ወደ ግራ ገባ ብሎ ለበለጠ መረጃ በ0118278077/0910584301 ደውሎ መጠየቅ ይቻላል፡፡

 

አዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ወረዳ 12 ፋይናንስ ፅ/ቤት

 

Save Tender